>

የመደመሩ ፖለቲካ ብዙ በተወራለት ሸገር ላይ  ገደል ሊከቱት ነው!!! (ጌታቸው ሽፈራው)

የመደመሩ ፖለቲካ ብዙ በተወራለት ሸገር ላይ  ገደል ሊከቱት ነው!!! 
ጌታቸው ሽፈራው
ለእቴጌ ጣይቱ እውቅና ያልሰጠች  አዲስ አበባ ተደመረች ልትባል አትችልም።  ሀገር በገነቡት ላይ የጥላቻ አንጎበሩ ያልለቀቀው ሀገር እገነባለሁ ሊል አይችልም። ሀሰት ነው!

እቴጌ ጣይቱ በቆረቆሯት አዲስ አበባ ከተማ አድዋ ድልድይ አቅራቢያ ሐውልታቸውን ለማሰራት ሰሞኑን የተጣለው የመሰረት ድንጋይ ተነስቷል።በከተማዋ ሩሲያዊው ፑሽኪንን ጨምሮ የተለያዩ ሐውልቶች ቆመዋል።የተቃውሞው አስተባባሪዎች ዓላማን ብቻ ለማስፈጸም የቆመ የከተማ አስተዳደር ከሆነ ብዙ ርቀት መሄድ አይቻልም።ሁሉም ወገን ቆም ብሎ ማሰብ አለበት።ብጥብጥና ሁከት ለማንገስ ካልሆነ የዚህ ተቃውሞ ዓላማ ሐውልት ብቻ አይደለም። ነገ የከተማዋ ሕዝብ የሰጠው የምርጫ ድምጽ እንዴት ይከበራል? ይህ ድርጊት ዛሬ መልስ የሚያስፈልጋቸውን ብዙ ጥያቄዎች አመላካች ነው። የሐውልቱን መሰረት ነቅሎ በመጣል ውስጥ የሌሎችን መብት ለማክበር ያለመፈለግ ብቻ ሳይሆይ የአፋኝነት ስሜትም አብሮት አለና ከወዲሁ ገደም ሊበጅለት ይገባል።

Filed in: Amharic