>

ዘ — ውዳሴ በረከት (ቾምቤ ተሾመ)

ዘ — ውዳሴ በረከት

ቾምቤ ተሾመ

ምንም እንኳን ሴይጣን ዲያብሎስን ሲያሞካሽ ብንሰማ ብዙም ባይገርመንም ነገር ግን ሴይጣን ቅዱስ የሆነ ስም ተጠቅሞ ዲያብሎስን ሲያቆለጰላጥስ ብንሰማ ዝግንን የሚል ስሜት
ይፈጥርብናል፤ ለዚህ ነው የእኩዩ  ፖለቲከኛ በረከት የሞተውን የቀን አራጅ መለሰን፤
በሚገርም ሁኔታ የኢትዮጵያ ቁንጮ ሆኖ እያለ እንኳን ስሟን እንዳይጠራ ይህች ሀገር እያለ
የሚመጻደቅባትን ኢትዮጵያን፤   በ “ትንሳኤ ዘ-ኢትዮጵያ “ በሚል ለመጸዳጃ መጠቀምያ
እንኳን ብቃት በሌለው መጽሃፉ መለሰን እንደገና ሊያስተዋውቀን የሚሞክረው::

ደግሞም በረከተ መለሰ በሰራቸው ግፎች፤ ዘራዊ ዓድሎዎች ፤ ሀገርን የመክዳት ፤ስራዎች
በረከት የሃሰት  እምቢልታዉን እየነፋ ሲያስተጋባ የነበረ የወንጀል አጋፋሪና አስፈጻሚ ስለነበር አሁንም አይኑን በጨው አጥቦ  የተለመደውን የሃሰት ጋጋታ በመደርደር
በሟቹ መለስ የእባብ ተፈጥሮ ላይ የመልአክ ክንፍ በሙጫ ሊያጣብቅ ስፍጨረጨር ማየቱ ብዙም አይገርምም፤ ምክንያቱም በረከትና መለሰም በኖረበት ዘመናቱ  ሀሰትን በማሳ ላይ መውቋትን እንደሳይንስ አብረው የተካኑት ሙያ ስለነበር ነው::

በረከትን አሁን ትንሽ ያሰከፋው ጉዳይ ቢኖር መለሰ ሲሞት የተከፈተውን የሃሰት
ጉድጓድ ሞልቼ (ሰሚ ባገኝ ኖሮ) ወያኔ በፕሮፓጋንዳ ተሸፍኖ እየጨፈጨፈ መቀጠል
አስችለው ነበር የሚል ጸጸት ነው። ለዚያም ነው ‹በየመድረኩ እንደ ተቀናቃኝ  ሳይሆን እንደ
ሐሳብ ቋት (Resource Person) እንድታይ ያቀረብኩት ተማጽኖ በተደፈኑ ጆሮዎች ላይ መውደቁን እያረጋገጥኩ መጣሁ ብሎ የሚያላዝነው። ኢትዮጵያዊያን  በረከትን የሀሰት ቋት እንጂ የሀሳብ ቋት ሆኖ አያውቁትም::

በረከት ስምኦን ካሸለበው እንቅልፉ ትንሽ ቢነቃና ትንሳኤ ዘ-ኢትዮጵያ ምን እንደሚመስል
ማወቅ ከፈለገ ከ60 ምናምን እድሜው  እንዲሁም 27 ዓመት ተንኮል ሲገምድ ከቆየበት የስልጣን አመቱ ይበልጥ  በአራት ወር ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ መሀመድ የሰራው ግሩም ድንቅ ስራ ቢመለከት ይበቃዎል :: አራት ሜትር ሰር የተቀበረው ጓደኛው መለሰ  እንደዚህ አይነት ሀገሩንና  ህዝቡን አክባሪ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያ መሃጸን ውስጥ አለ ብሎ እንኳን የሚጠረጥር አይመስልም፡: ኢትዮጵያ ላይ ጥሎት ሄዶል በረከት የሚለው  አሻራ በበረኪና ተፍቆ መልቀቅ ያለበት ጉዱፍ ነው፡: ይህ ጉድፍ አምስትም ይሁን አስር አመት ይፍጅ ድራሹ የኢትዮጵያ ህዝብ ያጠፋዋል።

የትኛውን የማናውቀውን መለስ ይሆን በረከት ዘ ቁስሉ ላልዳነው የኢትዮጵያ ሊያስተዋውቀን የሚዳክረው:- 

1. የአይናቸው ቀለም ካላማረን ማባረር እንችላለን ብሎ ስንት ኢትዮጵያ የኖሩ ኢርትራዊያንን ከነጨቅላ ልጆቻቸው በረሃ ላይ እያራገፈ የጣውን የሰው አውሬ ነው::
2.  የኢትዮጵያን የባህር መደብ እኛ ካልተጠቀምንበት የግመል መጠጫ ይሆናል  ብሎ
ያለምን መደራደር ባህር በሯን ያስረከበ ሃገር ሽያጭ ነው::
3. ለሱዳን ወግኖ ኢትዮጵያን የሚያንቋሽሽ የኢትዮጵያን መሬት በውስጥ ተፈራርሞ
የሚስጠውን መለስን ነው
4.  አጋዚ ወታደሮችን የግንባር መተህ ግደል ትዛዝ ሰጥቶ አዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፈኞችን
ያስጨፈጨፈውን  መለሰን ነው (220 በላይ ተረሽነዋል 800 በላይ አካለ ስንኩላን ሆነዋል)
5. የኢትዮጵያን ባንዲራ  ቁራጭ ጨርቅ ነው ብሎ የሰደበን መለሰን ነው
6.  በጋንቤላ ለመአድን ዘረፋ ብሎ 400 በላይ ያስጨፈጨፈውን መለስን ነው
7.  ወይስ ኢትዮጵያኖች ከየቦታው በራሱ ተላላኪዎች ሲፈናቀሉ የ enviromental ጉዳይ ነው ብሎ  የሚመጻደቀቅን እኩይ ነው።

እውነተኛ የኢትዮጵያውያን ታሪክ ተማራማሪዎች የዚህን እኩይ ስራ በማስረጃ  የሚያወጡበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም። አብሮት ወያኔን የመሰረተው አርአያ እንዳለው
ኢትዮጵያ በእኩዩ— መለሰ መሞት ተገላግላለች። ጨለማው ገጽ ተዘግቷል። ያንን ጨለማ የታሪክ ገጽ የምንከፍተው ተመሳሳይ ስህተት እንዳንሰራ ለመማር ብቻ ነው።

Filed in: Amharic