>
5:13 pm - Tuesday April 18, 3054

የሶ/ክ/ፕ አብዲ ኤሊ ያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር ዋሉ!!!

የሶ/ክ/ፕ አብዲ ኤሊ ያለ መከሰስ መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ስር ዋሉ!!!

ፋና ብሮድካስቲንግ


እሁድ ነሐሴ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ያለመከሰስ መብታቸው በሶማሌ ክልል ምክር ቤት የተነሳባቸው የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ ሙሐመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ)፣ ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡

ከአቶ አብዲ ጋር ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳባቸው የክልሉ የሴቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ራህማ ሐይባ፣ የክልሉ የፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲ ጀማል አህመድ፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አድን ሳባ፣ የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ አቶ ኢብራሂም መሐመድ ሙባረክ፣ የክልሉ ምክር አባላት አቶ ዴክ አህመድ ቡራሌና አቶ ዑመር መሐመድ ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለመጀመርያ ጊዜ ቅዳሜ ነሐሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፕሬዚዳንቱ ጉዳይ በሕግ የሚታይ እንደሆነ  አስታውቀ ነበር፡፡ በሶማሌ ክልል ይፈጸም የነበረው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በፊልም የሚታይ ልብ ወለድ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረግ አይመስልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ታሳሪዎች የሚጠበቅባቸውን ብቻ ሳይሆን ከሚጠበቅባቸው በላይ እንዲናዘዙ  ከአንበሳ፣ ከጅብና ከነብር ጋር እንደሚታሰሩ ገልጸዋል፡፡ ይህ ድርጊት በታሳሪዎቹ ላይ ይፈጽም የነበረው ለማስፈራራት እንደነበረም ተናግረዋል

Filed in: Amharic