>

ይህ ሰው ለእኔ ኢትዮጵያን በመከራዋ ሰአት የተሰጣት ጋሻዋ ይመስለኛል!!! (ጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ እይታ)

ይህ ሰው ለእኔ ኢትዮጵያን በመከራዋ ሰአት የተሰጣት ጋሻዋ ይመስለኛል!!!
ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ ፡ በጋዜጠኛ አለምነህ ዋሴ እይታ ።
ይህ ሰው የሚናገረው ሁሉ ያድናል።ኢትዮጵያን ሲጠራት ልብህን በደስታ ትርክክ ያደርገዋል።
 
እንደምታዩት ፈረንጆቹ charsmatic የሚሉት ዓይነት ነው። ኦህዴድን በዚህ ሰው አምሳል ማየት ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ በትልቁ ማክበር ጀምሪያለሁ።ብዙሀኑን የኦሮሞ ህዝብ መመጠን በሚያስችለው ደረጃ ራሱን እንዲገነባ ልንፈቅድለት እንደሚገባ የሚያሳምን ነው .።
ሰውየው–ፕሬዚደንት ለማ መገርሳ -በየትኛውም መድረኮች የሚያደርጋቸው ንግግሮች ከዛሬ ባልተናነሰ ነገም ጥልቅ ትርጉም የሚኖራቸውና አቅጣጫ ሰጪ ናቸው።
ነገረ-ስራው ከሩሲያው ፑቲን ጋር ይመሳሰልብኛል።ሰውየው በኦሮሞነቱ ይኮራል፤በኢትዮጵያዊነቱ ይመካል። ከመገላመጥ ብዛት የተነሳ አንገታቸው ወደኊላ ተሰብሮ ከቀረ ፖለቲከኞች በተለየ ዓይኑን ነገ ላይ ያነጣጠረ “ከ Do or die “መንፈስ-አልባ እልሀውያን ፍፁም በተለየ “live and let live” ባለራዕይ ነው።
ባለፉት 50 ዕመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለጠመንጃ፣ያለ መርዘኛ ፕሮፓጋንዳና ተቆጣጣሪ የድርጅት ስራ የብዙሀን ኢትዮጵያውያንን በነፃ ፍቃድ የተሰጠ ክብርና ፍቅር ለመቀዳጀት የሚችል ነው።
ለማ መገርሳ ኢትዮጵያን ከግማሽ ክፍለ-ዘመን እስር መፍታት የሚችል ጎበዝ ይመስላል።
ይህ ሰው ለእኔ ለኢትይጵያ በመከራ ሰዓት የተሰጣት ጋሻዋ ይመስለኛል።ከየአቅጣጫው የሚወረወርበት ጦርም ይታይኛል።ይሁንና ከልዩነታችንና ከጥላቻችን ባሻገር ወደምትገኘው መልካም የሚነፍስባት ኢትዮጵያ ሊወስደን የተነሳ ነውና ይህን ሰው እናዳምጠው፤እንከተለው።
ሽታህ ደስ አለን !!!
ከጥቂት ወራት በፊት ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ በአርሲ አካባቢ ለጉብኝት ሄደው ሳለ የአካባቢው ነዋሪ በከፍተኛ አቀባበል ተቀብሏቸው ሲያበቃ በኦሮሞ ባህል መሰረት የሃገር ሽማግሌዎች ፕሬዝዳንቱን ሊመርቁ ወደ መድረኩ መጡና እንዲህ አሉ ፡
አንተ ልጃችን ነህ ፡ ወደ አመራር ከመጣህ ብዙ ጊዜ ባይሆንም የቻልከውን ያህል ለኦሮሞ ህዝብ እየሰራህ እንደሆነ እያየን ነው ። ግን ከዚህ ይልቅ በቃ ሽታህ ደስ አለን ለዚህም ነው የምንወድህ ብለው መርቀውት ወረዱ ። ህዝብ ህዝብ የሚል ሽታ ። ከራሴ ይልቅ ሃገሬን የሚል ሽታ ፡ ይህ ሽታ ነበር የሃገር ሽማግሌዎቹን ያወዳቸው ።
ክቡር ፕሬዝዳንት ረጅም እድሜ እንመኝልሃለን ።
Filed in: Amharic