>
5:13 pm - Wednesday April 19, 0333

እውነት የሰቆጣ ሕዝብ ይሄንን አደረገ??? (አምሳሉ) 

እውነት የሰቆጣ ሕዝብ ይሄንን አደረገ???
አምሳሉ 
አቶ ታምራት ላይኔ ከነሚስቱ በቀደምለት በሰቆጣ የሞቀ አቀባበል ተደረገለት፡፡ ይሄ ሲገርመን በዚያው በአቀባበሉ ዕለት “ልማት በአንተ ጊዜ ቀረ!” ምንትስ ቅብርጥስ የሚሉ መፎክሮች ሰቅለው ይሄንን የወያኔ ሎሌና ባሪያ የአማራ ቀንደኛ ጠላት አወደሱት ተንከባከቡት አከበሩት፡፡
በዚህ ሳያበቁ ዛሬ ደግሞ በሻደይ ወይም በሶለል በዓል ላይ በምታዩት መልኩ እሱና ሚስቱን በካባና አክሊል ሸልመው አስጊጠው ንጉሥና ንግሥት አድርገው አንግሠዋቸው አረፉት፡፡
እውነት ግን ይሄንን እያደረገ ያለው የሰቆጣ ሕዝብ ነው ወይስ በድኑ ብአዴን ነው እንዲህ የሚጫወትብን???
የትኛውን ልማትስ ነው “ልማት በአንተ ጊዜ ቀረ!” የሚሉት???
ይህ ሰው የብአዴን ሊቀመንበር በነበረ ጊዜ ወያኔን ለማገልገል፣ የወያኔን አማራን የማጥፋት ዓላማን ለማስፈጸም በአማራ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ተነግሮ የማያልቅ ግፍና በደል ሳይበቃን መጥቶ እፊታችን እየፏለለ ቁስላችንን እየነካካ፣ ሐዘናችንን እየቀሰቀሰ እንዲያበግነን፣ እንዲያቃጥለን፣ እንዲያጨሰን ብአዴን ይሄንን ማድረጉ ለአማራ ሕዝብ ምን ያህል ንቀት ቢኖረው ነው???
ይመስለኛል ብአዴን ተአምራት ለአይኔን ወደ ፓርቲው ሊመልሰው ፈልጓል፡፡ የዚህ ዳርዳርታ ትርጉሙ ይሄው ነው ሌላ አይመስለኝም፡፡
የዚህን ያህል እንደሚንቁን ነው ማሳየት የፈለጉት??? ከታምራት ድፍረት የገረመኝ የብአዴን ጣራ የነካ ንቀት ነው!!!
ኧረ ለመሆኑ የሰቆጣ ወጣቶች ይሄንን በታላቅ ንቀት የተፈጸመብንን ስድብና ዘለፋ እንዴት በዝምታ ሊመለከቱ ቻሉ???
ሲጀመር ሰውየው መናፍቅ ነው፡፡ ይሄንን መሠረቱ የወላዲተ አምላክ በዓል የሆነውን የሻደይ ወይም የሶለል በዓል አከባበርን አያምንበትም አይቀበልም፡፡
እንዲህ በሆነበት ሁኔታ ይሄንን የመናፍቃን ፓስተር ከነሚስቱ በዚህ በዓል ላይ ካባ አልብሶ አክሊል ደፍቶ መሸላለም ከንቀትም ባለፈ በእምነታችን ላይ መሳለቅ አይደለም ወይ???
ይህ ሰው በወገኖቻችን ላይ ለፈጸመውና ላስፈጸመው አረመኔያዊ ግፍ ትክክለኛ ፍርዱን አግኝቶ መቀጣት ያለበት ቀንደኛ ወንጀለኛ እንጅ አንዳችም የሚያሸልም የሚያስወድስ በጎ ተግባር የለውም!!!
በድኖች ሆይ! እባካቹህ አንድ ቀን በዚህ ሕዝብ ፊት ዋጋቹህን እስክታገኙ ድረስ ንቀታቹህን ድፍረታቹህን በልክ አድርጉት??? በሕዝባችን ላይ ትንኮሳ አትፈጽሙብን??? ሕዝባችንን ለማስቆጣት ጥረት አታድርጉብን??? የሕዝባችንን ትዕግሥት አትፈታተኑብን??? እባካቹህ???
Filed in: Amharic