>
5:13 pm - Monday April 19, 9971

ሕገ መንግሥቱ ሲተገበር ይሏል እንዲህ ነው! (አንዱአለም ቦኪቶ)

ሕገ መንግሥቱ ሲተገበር ይሏል እንዲህ ነው!
አንዱአለም ቦኪቶ
የአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማስታወቂያ ዩኒቨርሲቲው  በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላወጣው  የሕግ አስተማሪዎች የቅጥር ማስታወቂያ  በውስጥ በኩል ያወጣው ማስተካከያ ነው።  ዩኒቨርሲቲዎች የፌዴራል ተቋማናት ናቸው ፤ የማስተማሪያ ቋንቋውም እንግሊዝኛ ነው።  አዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግን ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተወልደው አድገው አዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን  ለማስተማር   የሕግ መምሕራንን ሲቀጥር የሲዳምኛ ቋንቋ ችሎታ ይጠይቃል!
ይሄ በማንኛውም መስፈርት ተቀባይነት ሊያገኝ የማይገባው ዘረኝነት ነው!!
ይህን ያየው የጅማ ዩኒቨርስቲ ነገ ኦሮምኛ ተናጋሪ ካልሆናችሁ ጅጅጋ ሶማሊኛ: ሰመራ አፋርኛ ጎንደር አማርኛ …. የሚችል ካልመጣ  እያሉ ላለመቀጠላቸው ምን ዋስትና አለ?! የህግ ት/ት የሚሰጠው በእንግሊዝኛ ነው ። የአካባቢውን ህዝብ በአንዳንድ ነገሮች ማገልገል  ደግሞ የፋካሊቲው ዋና ተልእኮ አይደለም። አመራሩ ገና ለገና ለተቀጽላ እቅዴ ይረዳኛል በሚል ስንት ምርጥ መምህራንን እንደሚያጣ እንዳያስብ በዘረኝነት ነቀርሳ የተቦረቦረ ጭንቅላት በየት ብሎ?!
ይቺ በቋንቋ አሳቦ (የአካባቢውን ህብረተሰብ ያማከለ ጂኒ ጃንካ  ሙድ) ያውም በፌዴራል ተቋማት ውስጥ ዘረኛ የሆነ የስራ ቅጥር ማካሄድ በጊዜ ካልቀጨናት ነገ:-
አየር መንገድ አክሱም ለጀመርነው በረራ ትግርኛ የሚችል ፓይለት
* ሚትሮሎጂ: ቁሉምሳ(አሰላ)  ላለው ጣቢያችን ኦሮምኛ የሚችል የአየርንብረት ባለሙያ
*ፌዴራል ፖሊስ: ጉራግኛ ተናጋሪ እና ከኮሚሽነር ዘይኑ ጋር መግባባት የሚችል
* የሶማሌ ቲቪ: ሶማልኛ የሚችል….እያሉ ቢቀጥሉስ?!
ቀልዱን ትተን ይሄን ነገር በጋራ እናውግዝ!
Filed in: Amharic