>

የትህነግ/ህወሓት የጦርነት ዝግጅት እና ብልግና በወልቃይት !!! (ጌታቸው ሽፈራው)

የትህነግ/ህወሓት የጦርነት ዝግጅት እና ብልግና በወልቃይት !!!
ጌታቸው ሽፈራው
~ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ ትህነግ/ህወሓት በሰፈራ ቦታዎች ለገበሬው ትጥቅ ማስታጠቅ ጀምሯል። ከሽራሮ ጀምሮ እስከ ወልቃይት የሚኖረው ገበሬ እንደ አዲስ  ፈቃድ እያወጣ እንዲታጠቅ ተደርጓል። ወልቃይት ውስጥ የሚገኙ የቀን ሰራተኞችን እየመለመሉ ዋልድባ አካባቢ ማይጋባ የሚባል ቦታ እንዲሁም ቃፍታ ሁመራ አካባቢ ራውያ አካባቢ የሚሊሻ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
~ምልምሎቹ “ጦርነት አለ” የተባሉ ሲሆን “ከማን ጋር ነው የምንዋጋው?” ብለው ሲጠይቁ “እንነግራችኋለን” ተብለዋል።  “ከወንድሞቻችን ጋር አንዋጋም” ያሉ የወልቃይት አማራዎች መሳርያቸውን እየተነጠቁ መሆኑም ታውቋል።
~የወልቃይት ሕዝብ የዶክተር አብይ አህመድን የድጋፍ ሰልፍ እንዳይወጣ የተከለከለ ሲሆን በአንፃሩ  ትህነግ/ህወሓት በዶክተር አብይ ላይ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ሳይገኝ ቀርቷል።  ትህነግ/ህወሓት በዶክተር አብይ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ በጠራበት ቀን ሕዝብ የስራ ማቆም አድማ ያደረገባቸው ቦታዎችም ነበሩ። በዚህም ምክንያት ትህነግ በሕዝብ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እቅድ እንዳለው የተገለፀ ሲሆን የሚሊሻ ስልጠናው  የዚሁ አፈና እቅድ ነው ተብሏል። ሕዝብም ትህነግ/ህወሓት ሶማሊ ክልል እንደተፈፀመው  ሊያደርግ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ተገልፆአል።
~በሌላ በኩል ማይካድራ ከተማ አማራዎች በጅምላ መደብደባቸው ተገልፆአል። ማይካድራ ከተማ ሶስት የትግራይ ልዩ ሀይሎች አንዲት ወጣትን ላይ በደል ሲፈፅሙ የተመለከተ የወልቃይት አማራ የልዩ ሀይል አባላቱ ላይ ጉዳት በማድረሱ የትግራይ ልዩ ሀይል አባላት አማራዎችን በጅምላ ሲደበድቡ ማደራቸው ተገልፆአል።
~ በዚሁ ወልቃይት ንፁሁን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን መያዝ ከማሳሰሩ በተጨማሪ መሬት ላይ አድርገው እንደሚያስረግጡትም ታውቋል። ማይካድራ ኬላ ላይ “I love ethiopia” የሚል የተፃፈባቸው የአንገት “ሻርፕ” እጅ ላይ የሚታሰሩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን የኬላ ማገቻው ገመድ ላይ በማሰር መኪና ሲያልፍ መሬት ላይ ገመዱ ሲወድቅ በመኪና እያስረገጡ እንደሚያሳልፉ ነዋሪዎች ገልፀዋል። ሰንደቅ አላማዎቹ  ኬላው ላይ ከወልቃይት ተወላጆች  በፍተሻ የተቀሙ እንደሆኑም ታውቋል።
Filed in: Amharic