>

እነርሱ እና እኛ (አርአያ ተስፋማርያም)

እነርሱ እና እኛ
አርአያ ተስፋማርያ
እነርሱ
በዲሲ ዋይት ሃውስ አካባቢ ወደሚገኘው ትልቅ ፍ/ቤት (court) ዛሬ ማለዳ አምርቼ ነበር። 126 ሰዎች የአሜሪካ ዜግነት ለመውሰድ ተገኝተዋል። ስነስርአቱን ለማስጀመር ዳኛው ወደመንበራቸው ሲመጡ ሁሉም ከመቀመጫው ተነስቶ ተቀበላቸው። አንድ አስደማሚ ነገር ተናገሩ “There are some people who says that they are a real Americans, but I’m telling you that you are not less or more than any fellow American citizens ” (.አሜሪካውያን ማለት እኛ ነን የሚሉ አሉ። እናንተ ከየትኛውም አሜሪካን አታንሱም፣ አትልበጡም!)…ከተለያየ የአለም ክፍል የመጡትና ከእንግሊዝ ሳይቀር የአሜሪካ ዜግነት ለወስዱት 126 ሰዎች “እንኳን ደስ አላችሁ” ሲሉ የሞቀ ጭብጨባ ተከተለ። ..በክብርና በፍቅር የሌላ ዜጋ ሲቀበሉ ስመለከት አንድ ጥያቄ ተመላለሰብኝ። “ይህ አገር የእኛ ቢሆን የሌላ አገር ዜጋ እንቀበል ነበር?..እስቲ እያንዳንዳችን የምር..መልስ እንስጥ!?.
እኛ
በአንድ አገር እየኖርን፣ የገዛ ወገናችንን በድንጋይ ወግረን የምንገድል፣ የህፃን ልጅ አይን አጥፍተን ብልት የምንቆርጥ፣ በቤንዚን የምናቃጥል…ከዛም ያለፈው ደግሞ የገዛ አገርህ ኢትዮጵያን ዜግነት ገፎ…የብሄር ታርጋ የሚለጥፍብህ፣ ካንተ እኔ የተመረጥኩ ኢትዮጵያዊ ነኝ..ሲል በአደባባይ የሚጀነንብህ፣ በዘረኛነት በሽታ ተለክፈን ..የጥፋት ነጋሪት የምንጎሽም..ወዘተ ሆነን ወላጆቻችን ያወረሱንን ፍቅር ንደን በሚያስደነግጥ አፋፍ ላይ እንገናኛለን። እስቲ እንጠይየቅ..???
Filed in: Amharic