>

ሰበር ዜና: ሮመዳንና አስደሳቹ የሳውዲው ንጉስ የምህረት አዋጅ ![ነቢዩ ሲራክ]

ነገ የሚጀምረው ሮመዳን …

ትናንት ምሽት በመላ ሳውዲ አረቢያ ግብጽን ጨምሮ በአጎራባች መካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጨረቃ ባለመታየቷ የሮመዳን ጾም በነገው እለት እሁድ June 29,2014 ወይም ሰኔ 22, 2006 እንደሚጀምር ታውቋል።

የሳውዲ ንጉስ የምህረት አዋጅ …

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሮመዳንን ምክንያት በንጉስ አብደላ ቢን አብድልአዚዝ ትዕዛዝ በሽዎች ለሚቆጠሩ የህግ እስረኞች የምህረት አዋጅ በይፋ መውረዱ ታውቋል። የምህረቱ ተጠቃሚዊች ቁጥር በውል ባይታወቅም በምህረቱ የሚካተቱ ወደ 500 የሚደርሱት በአሁኑ ሰአት አሻራ በማጠናቀቅ በጅዳ በቀጣይ ቀናት ይሸኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። በቀጣይነትም ከ250 እስከ 300 የሚደርሱ የህግ ታሳሪዎች በየቀኑ እንደሚለቀቁ በሽክሹክታ ሲሰራጭ የነበረውን የምህረት የምስራች ይፋ ያደረጉት የመገናኛ ብዙሃን የእስር ቤቶች አስተዳደር ዳይሬክተር ጀኔራል አህመድ ሻህራኒን ጠቅሰው መረጃውን በይፋ አስታውቀዋል።

Saudi-jail-inmates

በምህረቱ አዋጁ ተጠቃሚ ከሚሆኑት መካከል ለሁለት ወራት የነበርኩበት በጅዳው የብሪማን ማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል። አብዛኛው የፍርድ ጊዜያቸው ጨርሰው በአስወታዋሽ እጦት አበሳቸውን ሲያዩ የከረሙትን በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ፍርደኞች የምህረቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ለማረጋገጥ የቻልኩ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንባሲና ቆንስል መስሪያ ቤቶች የዜጎቻቸውን ሰነድ በማቅረብ አፋጣይ ድጋፍ የወሰጧቸው ዘንድ ያነጋገርኳቸው ታሳሪዎች ተማጽነዋል !

   ለእስልምና እምነት ተከታዮች መልካም የጾምና የጸሎት ወር ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው!

                                                                 ነቢዩ ሲራክ

Filed in: Amharic