>
5:13 pm - Saturday April 20, 9867

" እርቁ የኔም እጅ አለበት...ዐብይ አህመድ የሚታመኑ ሰው ናቸው ብዬ  ምስክርነት ሰጥቻለሁ" (አንዳርጋቸው ፅጌ)

” እርቁ የኔም እጅ አለበት…ዐብይ አህመድ የሚታመኑ ሰው ናቸው ብዬ  ምስክርነት ሰጥቻለሁ”
አንዳርጋቸው ፅጌ
….በህይወት መኖሬ ይገርመኛል ያለፍኩበትን አልፌ ለዛሬ መብቃቴ ለኔም ድንቅ ነው።የልጆቼ ጉዳይ ትልቁ ጭንቀቴ ነበር ናፍቆት የልጆች ትዝታ ያባትነት ድባብ አለ አይደል ።
እናም የኢትዬ/ ኤርትራ እርቅ ትልቁን የስምምነት መንገድ ካበጃጁት ሰዎች አንዱ ነኝ እንደምታውቁት ከእስር ቤት ስወጣ  ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ እቢሮ ድረስ ጠርተውኝ አነጋግረውኝ ነበር ሀገራችን እንዲህ አይነት መሪ ማግኘትዋን ሳይ ቀልቤ አረፈባቸው እሳቸውም ለኤርትራ የሰላም ጥሪ አቅርበው ነበር ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ጋር ግን ከፍተኛ ጥርጥር እና ስጋት ነበር።እሳቸውም ደውለውልኝ “ይህን ሰው ታምነዋለህ ወይ አሉኝ” እኔም በሚገባ አልኮአቸው።
አያችሁ ወገኖቼ በፓለቲካ  ዐለም መታመን የሚባል ነገር አለ። ኢሳያስ አፈወርቄ እኔን በደንብ ያውቁኛል፤ ያምኑኛልም ከዚህም የተነሳ ቃለ እምነቴን ሰጠሁ ። አዎን ዐብይ አህመድ የሚታመኑ ሰው ናቸው ብዬ ይህም ማለት ለሁለቱም ሀገሮች እርቅ የኔም እጅ እንዳለበት ማሳያ ነው።
ከእስር ቤት ወጥቼ ሀገሬን  ጠቅሜያለሁ ማለት ነው። በቃ ከዚያ በኋላ ብዙም ጊዜ አልፈጀም ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ሰላም ፈጠሩ ከእስር መውጣቴ አንድ አስገራሚ ነገር ሆኖ ሳለ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መሀል ሰላም ለማቅረብ ድልድይ ሆኜ የአመኔታ ቃል መስጠቴ ለኢሳያስ አፍወርቄ ትልቅ አቅም ነበር።
 እንደ ፓለቲካ ድርጅት አመኔታን ማግኘቱም ቀላል አይደለም ይህ የድርጅታችን ካፒታል ነው። በቃ ስለ ጠ/ሚ ዐብይ ምስክርነት እንድሰጥ ምክንያት ሆኛለሁ።
ምንጭ:-በአምላክ ስሜነህ
Filed in: Amharic