>
5:13 pm - Thursday April 19, 7455

አብዲ ኢሌ ከስልጣን መውረዱን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አረጋገጠ - BBC|አማርኛ

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዝድንት የነበሩት አብዲ ሞሃመድ ኡመር ከስልጣናቸው መነሳታቸውን የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ሃላፊው ኢድሪስ ኢስማኤል ለቢቢሲ ሶማልኛ አረጋግጠዋል።

ከኢድሪስ ኢስማኤል መረዳት እንደተቻለው፤ አብዲ ሞሃመድ ኡመር ከክልሉ ፕሬዝደንትነታቸው ይነሱ እንጂ የኢትዮጵያ ሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሪ ሆነው ይቆያሉ ብለዋል።

ኢድሪስ ኢስማኤል ጨምረው እንደተናገሩት አህመድ አብዲ ሞሃመድ የቀድሞውን ፕሬዝደንት በመተካት ተሹመዋል።

ከቅዳሜ አንስቶ በጂግጂጋ እና በክልሉ ሌሎች ከተሞች የተከሰተውን ሁከት ተከትሎ የሃገር መከላከያ ሠራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ወደ ክልሉ ገብቶ ሰላም እንዲያስከብር መታዘዙ ከሰዓታት በፊት ይፋ ተደርጎ ነበር።

በስፋት ”አብዲ ኢሌ” በመባል የሚታወቁ አብዲ ሞሃመድ ኡምር ሰልጣን በፍቃደቸው ወይም ተገደው ስለመልቀቃቸው የታወቀ ነገር የለም።

ባለፉት ቀናት በክልሉ በተከሰተው ሁከት የሰው ህይወት ጠፍቷል እንዲሁም ንብረት ወድሟል።

 

Filed in: Amharic