>
5:13 pm - Monday April 19, 9069

አብዲ ኢሌ ገዳይና ዘራፊ ነው የሚለው ኦብነግ በአብዲ ኢሌ ላይ በፌዴራሉ መንግስት የተወሰደውን እርምጃ አወገዘ።

ጅጅጋ አስገሪ የሞት ጥላ ያንዣበበባት ከተማ። ሆናለች!!!
አበበ ዘውዱ
* መከላከያ ሰራዊት በአየር ድብደባ በመጀመሩ ሁሉም የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ ትዛዝ ተላልፏል።
 
* ከአብዲ ኢሌ ጋር የሚደረገውን ድርድር ተከትሎ መንግስት መግለጫ እንደሚሰጥ ተሰምቷል። 
 
*  አብዲ ኢሌ ገዳይና ዘራፊ ነው የሚለው ኦብነግ በአብዲ ኢሌ ላይ በፌዴራሉ መንግስት የተወሰደውን እርምጃ አወገዘ።
 
 የህወሓት አገዛዝ የመገንጠል ውሳኔ ሊወስን ስለሚችል በሚል ከፍተኛ ወታደሮች ወደ ትግራይ ክልል ለማስጠጋት ተወስኗል ተብሏል። በህወሓት የሚመራው የአብዲ አሊ ጦር በመደምሰሱ ቀጣይ በትግራይ ክልል አመራሮች ላይ እርምጃ ይወሰዳል በማለት ከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ የገቡት የህወሓት አመራሮች  የራሳቸውን ውሳኔ ለማስተላለፍ ያለ የሌለ አቅማቸውን ለመጠቀም እያቀዱ ነው። ይህን ተከትሎ በቀጣይ ነሃሴ 13 የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ተጠርቷል።
የህወሓት ደጋፊዎች በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ መግባታቸው እየተገለፀ ነው።ከህወሓት ጎን መቆም ወይስ ከኢትዮጵያ በማለት ውዥንብር ውስጥ ገብተዋል ተብሏል።
የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግንባር ብሎ ራሱን የሚጠራው ተቃዋሚ ቡድን አብዲ ኢሌን በመደገፍ ባወጣው መግለቻ የክልሉ ሕዝቦች  አብዲ ኢሌንና ክልላቸውን ከወራሪዎች ምመጠበቅና መከላከል አለባቸው ብሏል።  ሕገመንግስቱን አልቀበልም ብሉ የትጥቅ ትግል ላይ የሆነው ኦብነግ የጅጅጋው ድርጊት ሕገመንግስቱን የጣሰ ነው ሲል መናገሩ ት ዝብት ላይ ጥሎታል
ኦብነግ በተለያዩ ጊዜያት ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት የፌዴራሉን መንግስትና የክልሉን መንግስት በማብጠልጠልና በመክሰስ ይታወቃል። በተለይ አብዲ ኢሌ እብድ መሪ ነው ኢሰብዓዊ ነው ወዘተ የሚሉ ስሞችን በመስጠት ለዓለም ዐቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ሲከሰው ከርሟል። አባሎቼን አፈነብኝ ሲልም ሲያማርር ከርሟል። ዛሬ የተከሰተውን የጅጅጋ ችግር ተገን አድርጎ ድርጅቱ እንዳለው መሪውንና ክልሉን ሕዝቡ እንዲጠብቅ ጥሪውን አስተላልፏል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደራዊ እርምጃዎችን እንዲያስቆሙ የጠየቀው ኦብነግ ሕዝቡ መብቱን እንዲያስከብርና ጉዳዩን ካለማንም ጣልቃ ገብነት እንዲፈታ አሳስቧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌዴራል መንግስቱ ከአብዲ ኢሌ ጋር ስምምነት ላይ እንዲደርስ ሽምግልና መጀመሩንና ድርድር ተደርጎ መግባባት እንዲፈጠር የሕወሃት ሰዎችና የሶማሌላንድ ባለስልጣናት እየተሯሯጡ መሆኑ ተነግሯል። አቶ አብዲ ኢሌን በተመለከተ በሚዲያ ምንም አይነት ጉዳይ እንዳይነሳና በጂጂጋ ሁከት ከመነሳቱ ውጪ ለላ ዜና እንዳይቀርብ የተደረገ ሲሆን ከአብዲ ኢሌ ጋር የሚደረገውን ድርድር ተከትሎ መንግስት መግለጫ እንደሚሰጥ ተሰምቷል።
Filed in: Amharic