>
5:13 pm - Saturday April 19, 1208

አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር ዋለ!!! (ስዩም ተሾመ)

አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ስር ዋለ!!!
ስዩም ተሾመ
በዛሬው ዕለት አብዲ ኢሌ የክልሉን ምክር ቤት ስብሰባ ጠርቶ ነበር። ጠዋት ላይ የምክር ቤቱ ስብሰባ ላይ እያለ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ውሏል። አብዲ ኢሌ ሲያዝ የተወሰኑ የምክር ቤት አባላት ነገሩን ለማደናቀፍ ሙከራ አድርገው ነበር። በመሆኑም የመከላከያ ሰራዊቱ በዚህ ተግባር የተሰማሩን ሰዎች በቁጥጥር ስር አውሎ የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ተለቅቀዋል። በተመሳሳይ በምክር ቤቱ አቅራቢያ የነበሩ የክልሉ ልዩ ፖሊስ አባላት ተኩስ ከፍተው የነበረ ሲሆን የመከላከያ ሰራዊት ጠንከር ያለ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በመውሰዱ ተበትነዋል። በዚህ መልኩ አብዲ ኢሌ በመከላከያ ቁጥጥር ስር ውሏል።
#የሶማሌ ወጣቶች ያስተላለፉት መልዕክት! “#በአብዲ_ኢሌ መውደቅ ደስታችን የላቀ ነው፡፡ የእሱ ካቢኔዎች የሚቀሰቅሱትን ሁከት ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት ከመጠን ያለፈ የሃይል እርምጃ እንዳይወስድና ደስታችን ወደ ሀዘን እንዳይቀየር አደራ…አደራ” ብለዋል!! ሊደመጥ የሚገባ መልዕክት ነው፡፡ (ለግለሰቡ ደህንነት ሲባል የተናጋሪው ምስል ተሸፍኗል) #ጅግጅጋ #አብዲ_ኢሌ
Filed in: Amharic