>
5:13 pm - Tuesday April 19, 3036

የለማ ቲም አሰከረን !!! (ታደለ አሰፋ)

የለማ ቲም አሰከረን !!!!!
ታደለ አሰፋ
የጥላቻ ና የመለያያ ግንብ የማፈራረሱ ስራና የፍቅር ድልድይ ግንባታ በሜኔሶታ ጁላይ 30 በደማቅ ሁኔታ በታርጌትማዕከል 19ሺህ የኢትዮጵያ ልጆች በተገኙበት በተለያዩ  ባንዲራዎች ና ሙዚቃዎች ታጅቦ ተከናውንዋል።
እዚህ ያለንበት ሀገር የስፖርትፉክክር ይመስል ነበር።የተለያዩ ባንዲራዎች ይዘው ነገር ግን ተደበላልቀው መቀመጣቸውና ቢያንስ ለሶስት ሰዐት ምንም ግጥሚያ አለመታየቱ ነው ልዩነቱ።
የተለያዩ የኢትዮጵያ ባህል ዘፈኖች ሲዘፈኑየተለያዩ ባንዲራዎች ይዞጭፈራው ድንቅ ነበር ።በጉልህ የሚታዩት የኢትዮጵያ ኦነግ ናየኦጋዴንግንባር ባንዲራዎች ነበሩ ።
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አህመድ ዘግይተው ቢመጡም ህዝብ በሙዚቃ ተመስጦ የተሰላቸ አልነበረም ።
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አቶ ለማሌሎችእንግዶች ጋር ጃዋር መሀመድ መድረክ ላይ ሲታዩ በታላቅ ጭብጨባ ተቀብለዋቸው በፀሎት መርሀ ግብሩ ተጀምርዋል።
በኦሮሞ ወጣቶች በአፋር ወጣቶች ሌሎች ኢትዮጵያውያን ባህላዊ ዘፈኖችና ውዝዋዜዎች ተካሂደዋል።ተመሳሳይ የሙዚቃ ምሽት በዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጅ በአፍሪካ ምሽት የተለመደ ነው በአሜሪካን።
የመጀመሪያው  ተናጋሪ አቶ ለማመገርሣ ንግግራቸውን ሲጀምሩ ጥቂት ሰዎች በአፋንኦሮሞ ተናገሩ እያሉ ቢጮሁም አቶ ለማ በኦሮሙኛ እንዲታገሱ ጠይቀው ወደ ንግግራቸው በዕርጋታ ሄደዋል።
 የመለያየት አጥር ውጤቱ ስደትና ዉርደት በመሆኑ የተለያየ ባህልና ቛንቛ ጌጥ ሀብታችን አድርገን ኢትዮጵያ  እንገንባ ብለው አቶ ለማ አሳስበዋል።
ከኦሮሞ ክልል ለሜኔሶታ ለኦሮሞ ተወላጆች የተላከውን መልዕክትምአስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ  አህመድ በዲሲ የተጀመረው ጥላቻ ግንብ ፈረሳ ሎስ አንጅለስ ተጋምሶ የመጨረሻው ፍራሽ በጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አህመድና ጃዋር መሀመድ መተቃቀፍ ታውጆ ከዚያም ሁሉም ዘር ፆታ ሀይማኖት ሳይለይ በመተቃቀፍ የግንቡ ፍራሽ ተጠራርጎ ተጥልዋል።
የሜኔሶታም ኢትዮጵያውያን ላሳዩት ቁርጠኝነት አዲስ የቆንስላ ፅህፈት ቤት ተከፍቶላቸዋል።
በዛሬው ታሪካዊ ቀን ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አህመድ ና አቶ ለማ መገርሣ የተከሉት የአንድነት ስሜት በተለይ የወጣቱን የሀሳብ አድማስ በማስፋት ዉጤት እንደሚያመጣ በእርግጠኝነት እመሰክራለሁ።
በዕርግጥም የአቶ ለማ ቲም ባወቅነው ሶስት ቀናቶች ብዙዎቻችንን አሰከረን።ዐቢይ በኛ ፍቅር እንደ ሰከሩ መስክረዋል ።
* ዘግይቶ የደረሰን። በሜኔሶታና አካባቢ የሚገኙ  በሺ የሚቆጠሩ የኦነግ ደጋፊዎች በአቶ ለማ መገርሣ ኢትዮጵያ ሱሴ ፀበል መፈወሳቸዉን እየመሰከሩ ይገኛሉ ።
በሠላም ኢትዮጵያ ያግባችሁ እንወዳችሁአለን።
Filed in: Amharic