>

"የኢንጅነር ስመኘውን አስክሬን ለመሰናበት የተገኘው ህዝብ በፓሊስ ጥይትና በአስለቃሽ ጭስ ተበትኗል!

የኢንጅነር ስመኘውን አስክሬን ለመሰናበት የተገኘው ህዝብ በፓሊስ ጥይትና በአስለቃሽ ጭስ ተበትኗል!!!
ናትናኤል መኮንን
 
* የኦሮሚያ ፖሊሶች በጭስ የተጎዱትን ሲረዱ ታይተዋል
በጀግናው የአዲስ አበባ ወጣት ቀብር ለመሸኘት የወጣው ህዝብ ላይ ፌዴራል ፖሊስ አስቀላሽ ጭስ በመተኮስ ህዝቡን እያሸበረ ነው።
በርካታ አስለቃሽ ጭስ ተተኩሷል የወደቀ ህዝብ በየቦታው ይታያል።በቦታውም ቁጥራቸው እስከ 15 የሚደርሱ ሰወች ጉዳት ደርሶባቸው በዘዉዲቱ ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ነው።በመረጋገጥ ምክኒያት ቀላል የሆነ ስብራት የደረሰባቸው እንዲሁም ራሳቸውን ስተው የወደቁ ሰዎችን በቦታው መመልከት ችያለሁ።አብዩት አደባባይ በኢንጅነሩ ሞት ቁጭት ውስጥ የገባው የአዲስ አበባ ወጣትም:-
መለስ ነፍስህን አይማረው
•አባይ ፀሀየ የስኳር ሌባ
•የወያኔ ቅጥረኞች ለፍርድ ይቅረቡ
•የኢንጅነሩ ደም ፈሶ አይቀርም
•ከዚህ በኀላ እርምጃ እንወስዳለን ምን ቀረን
እያሉ መፈክር ሲያሰሙ ወጣቱ ምንም ችግር አልፈጠሩም ነበር፡፡
ነገር ግን ፌደራል ፖሊስ ጥይት መተኮስ ጀመር ከዚያ በኀላ ነገሩ ተቀየረ ወጣቱ ደንጋይ መወርወር ጀመረ፡፡ብዙ ሰውም ተጎዳ የተጎዱ ሰዎች በአንቡላንስ ወደ ህክምና እየተወሰዱ ነው፡፡
ብቻ ነገሩ በጣም ያስጠላል፡፡እኔም በአካል ነበርሁ አስከሬኑን መሸኘት አልተቻለም ወጣቱ እና ፖሊስ ጋር በተፈጠረው ግጭት:-
▪አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ
የፈሰሰው ደም የአንተ አደለሞይ....እያለ ነበር፡፡
ትግሉ ይቀጥላል..!!!”
Filed in: Amharic