>

እንደምነሽ ግብፅ የናስር ፣ የአንዋር ፣ የአልሲሲ አገር!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

እንደምነሽ ግብፅ የናስር ፣ የአንዋር ፣ የአልሲሲ አገር!!!
ቬሮኒካ መላኩ
 
* የአገሪቱን የመደራደር አቅም የጨመረ
 
*የቀጠናውን ጅኦፖለቲካዊ መስተጋብርና ሃገራዊ ፖለቲካ ነጽሮታዊ አቅጣጫን (paradigm shift) እንድረጋገጥ ያደረገ
 
* ወደ 7000 ሜጋ ዋት የሚጠጋ ሀይል የሚያመነጭ ሜጋ ፕሮጄት ቺፍ ኢንጅኔር ከሌሊቱ 9 ሰአት ጀምሮ ህዝብ በሚያጨናንቀው አደባባይ ላይ ተገድሎ አንድ እንኳን ተጠርጣሪ አለመያዙ አገሪቱ ምን ያክል አደጋ ላይ እንዳለች ግልፅ ነው።
ባለፉት 3 ወራት የኢትዮጵያ መግቢያ በር ተበርግዶ ያልገባ ጉድ የለም ። የፀጥታው መዋቅር ክረምብልድ ሆኗል።
እነ ክንፈ ዳኘው ከግድቡ የዘረፉትን ገንዘብ እንዳይታወቅባቸው አስገደሉት የሚለውን ተራ ሆያ ሆዬ አልሸምትም።  🙂 እስኪ መጀመሪያ ጌቶቻችን አቅም ካላቸው እነ ክንፈ ዳኘውን ከሜቴክ ለዘረፉትና ለጋጡት  50 ቢሊዮን ብር ተጠያቂ አድርጉትና ። ያ ወንጀል ብቻውን በህጉ እነክንፈ ዳኘውን በስቅላት ሊያስቀጣቸው ይችል ነበር እኮ። 🙂
እንደምነሽ ግብፅ የእነ ናስር አገር ፣ የአንዋር ሳዳት አገር ። እንደት አደርሽ ግብፅ  በ32 ጥርሱ እየተፍለቀለቀ የሚገዛሽ የጥበበኛው የአልሲሲ አገር ።
እንደዚህም ማሰብ ይቻላል በ2011 ግብፅ አደገኛ ቀውስ ውስጥ ነበረች። ኢትዮጵያ ደሞ በጣም የተረጋጋች ነበረች። የተረጋጋችው ኢትዮጵያ በቀውስ ውስጥ ባለችው ግብፅ ላይ አባይ ግድብ የሚባል ጠቃሚ ጆከር መዘዘች። ሙሉ ጥናቱ እንደሆነ በአፄ ሀይለስላሴ ትእዛዝ በአሜሪካኖች የባለሙያወች እርዳታና በአገር ውስጥ መሀንድሶቹ በእነ ሀይሉ ሻወል ተጠንቶ ቤተመንግስት ሸልፍ ተዘጋጅቶ እየጠበቀ ስለነበር  ጊዜው ሲደርስ ተመዘዘ።
በተቃራኒው በ2018 ግብፅ ስትረጋጋ ኢትዮጵያ በቀውስ መናጥ ጀመረች ።  ግብፅ በ2011 የተወሰደባትን አደገኛ አድቫንቴጅ ለማካካስ ትግል ጀመረች ። ቀን ጠበቀች ። ለአመታት ጡጦ እያጠባች ያሳደገቻቸውን ሁሉ ወደ አገር ውስጥ አስገባች።
በዚህ ወር ውስጥ ግብፅ አጥብቃ የምትጠላው የግድቡን ውሃ መሙላት ስራ ሊጀመር ሆነ ። በዚህም ምክንያት በፖለቲከኞችና በባለሙያዎች መካከል ክርክር ተጀመረ። ግድቡ ውሃ እንድሞላ ከሚፈልጉ ሙያተኞች ዋናው ኢንጅነር ስመኘው ነበር። አሁን ግብፅ መፍጠን እንዳለባት ገባት ለሌሎች ደረቅና አገር ወዳድ ሙያተኞች ትምህርትና ማስፈራሪያ ይሆን ዘንድ በተራቀቀ መልኩ ኦፕሬሽኗን አሳካች ።
በበኩሌ ሌባ በጠራራ ፀሀይ ቢሊዮን ዶላር ሰርቆ አሁንም አምባሳደርና ሚኒስትር በሚሾምበት አገር ስመኘው የበሉትን ብር ሊያጋልጣቸው ሲል የቀን ጅቦች አስገደሉት የሚል ተራ አመክንዮ ስለማይመጥነኝ ይለፈኝ።
Filed in: Amharic