>

ነገራችን ውሀ ቅዳ ውሀ መልስ እንዳይሆን!?! (ወርቁ ገልግለው)

ነገራችን ውሀ ቅዳ ውሀ መልስ እንዳይሆን!?!
ወርቁ ገልግለው
 
እንዴት ነው ነገሩ ግርማ ብሩ፣ ሳሞራ የኑስ
አባዱላ ገመዳ … June 8, 2018 አልነበር እንዴ ጡረታ መውጣታቸው የተነገረን:: ታዲያ ለምንድን ነው ግርማ ብሩ የብሄራዊ ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ተደርጎ የተሾመው::
በቀጣይ ሳሞራ የኑስንም ወደ ስልጣን ልትመልሱት ነው እንዴ? ካልሆነ አንዱን መልሶ ሌላውን መተው የቤት ልጅ እና የውጭ ልጅ… ለሚል ሀሜት ይዳርጋል።
 እኔ የምለው ሰው ጠፋና ነው በዚህ ቀውጢ ስአት ለዛውም በሲስተም በጡረታ የተሽኘን ሰው ወደስልጣን መመለስ:: ጓዶች ቦታው ደግሞ እኮ ቀላል አይደለም እንኳን የብሄራዊ ባንክ የትልቁ የንግድ ባንክ ቦርድ ሰብሳቢነት እስካሁን ድረስ ለረጅም ጊዜ በረከት ስምኦን ነው የያዘው::
 ባንድ ወቅት ወያኔ አቶ አዲሱ ለገሰን ጡረታ ካወጣ በኃላ እንደገና መልሶት እስካሁን ድረስ ፈላጭ ቆራጭ እንደሆነ መዘንጋት የለበትም::
 ለማንኛውም ጠቅላያች እርፍ ተይዞ ወደ ኋላ። አይኬድም ወደፊት እንጂ።
ኢትዮጵያ ማህፀነ ለምለም ናት እያልን ሌላ ግርማ ብሩ ጠፍቶ ነው የምናውቀውን ግርማ ብሩ ያመጡብን:: ካልሆነ እንደመንግስቱ ኃይለማሪያም ራስዎት ጠቅለው ይያዙት እንጅ በትግል ያባረርናቸውን የቀን ጅቦች በመደመር አይመልሱብን:: መደመርን ብቻ ሳይሆን እንደ አስፈላጊነቱ መቀነስንም ታሳቢ ያደረገ ፍትሀዊ አሰራር ነው የምንጠብቅብዎ።
ኢትዮ ሄሮ የተባሉ ጸሀፊ ደግሞ አዲስ የተራበ ጅብ ከምናመጣ በጠበቀ ቁጥጥር ልምዳቸውን እንጠቀም ይላሉ:-
 
ዶክተሩ በኢህአዴግአዊ አሿሿም መንገድ ነው የሚሾሙት ሲቀጥል ጠቅላያችን ተቀየሩ እንጂ ኢህአዴግ በግንባርነቱ እንደ ፀና ነው።
    ነገር ግን ዶክተሩ ይሄንኑ አጋጣሚ በመጠቀም ብዙ ፓለቲካዊ ትርፍ እንደሚያስገኝላቸው አውቀው ከድርጅቱ መዋቅር ሳይወጡ የባለስልጣኑን የከፋ አገዛዝ ወደ መልካም አስተዳደር በመለወጥ ያካበተ ልምዳቸውን በመጠቀም ሃገራቸውን የሚክሱበት እድል መስጠት ቀደምቱ ባለሥልጣናት በሃብት ማማ ላይ እንዳሉ ይታወቃል ስለሆነም የመስገብገብ እድላቸው ያነሰ ነው ቀድመው የዘረፉት እንዳይነቃባቸው በታማኝነት ለማገልገል ይገደዳሉ ያሁኑ ተጠያቂነት ሲኖር ደሞ ይበልጥ ይፈራሉ ሌላው አዲስ ፊት ባለሥልጣን ቢመጣ ከልምድ ማነስ ጋ ተዳምሮ ሌላ የራበው ጅብ በህዝብ መሃል እንደመልቀቅ ነው የሚሆነው ሥልጣን የህዝብ ማገልገያ እንጂ የመበልፀጊያ መንገድ እንዳልሆነ መረዳት እስኪቻል እንዲሁ መቆየቱ ሳይሻል አይቀርም።
Filed in: Amharic