>

ድል ለዴሞክራሲ!!! ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ወድ አገርቤት ተመልሷል!!

ድል ለዴሞክራሲ!!!
ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ወድ አገርቤት ተመልሷል!!!
ጋዜጠኛ ውብሸት ሙላት
የካቲት 7ቀን 2010 ዓ.ም ከቃሊቲ ጨለማ ቤት የሰባት ዓመታት አስከፊ የእስር ቆይታ በሁዋላ ሲወጣ በእስር ቤቱ ዙርያ ተሰባስበው ይጠብቁት ለነበሩት ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ፣ አድናቂዎቹና ለሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ያስተላለፋት መልዕክት… ‘ድል ለዴሞክራሲ !’ የምትል ነበረች።
   ለዴሞክራሲ፣ ለፍትሕና ነፃነት በሚያደርገው ትግል ባመነበት አቅጣጫ በፅናት፣ በቅንነትና ባለማወላወል እየተጓዘ ነው። ተልሞ ለተነሳበት  ጎዳና አይነተኛ ድጋፍ ሲያደርግ የቆየውን በውጭ አገራት የሚኖር ወገኑን ለማመስገን እና ቤተሰቡን ለመጠየቅ ካደረገው ጉዞው እነሆ በያዝነው ሳምንት ተመልሷል። “እግዚአብሔር በሰላም ይመልስህ” ብለን የሸኘነው ልጃችን ሲመለስ ይህን ላደረገ አምላክ ምስጋናችንን አቅርበናል።
  የብዙ ሚሊዮኖች እናት የሆነችው ኢትዮጵያችን ለአንድነቷ፣ ለክብሯና ለልዕልናዋ በፅናት የሚቆሙላት ልጆቿን ከምንጊዜውም በላይ ዛሬ ትፈልጋቸዋለች። ዴሞክራሲ ድል የሚያደርገውም ሚሊዮኖች ተናብበውና ተባብረው ‘ለአንድ ዓላማ በጋራ መቆም’ ሲችሉ ብቻ ነው።
(የፎቶ መግለጫ:- እስኬ በአሜሪካ እያለ ለህትመት የበቃችውን “ኢትዮጵያዊነትን የመመለስ ተጋድሎ” የተሰኘችውን ሶስተኛ መጽሐፌን ሳበረክት። 
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ያስብ፤ ሕዝቧን ይባርክ!
ጋዜጠኛ እስክንድር የዘረኞች የጥቃት ሰለባ የሆነውን አበጥር ወርቁን ጠይቋል! !!
ናፍቆት እስክንድር
ከሁለት ወራት በፊት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሰቃቂ ጥቃት የተፈፅመበት ታዳጊ አበጥር ወርቁን ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እስክንድር ነጋ ከአሜሪካ መልስ ጎብኝቶታል።
አበጥር ወርቁ ለህክምና ወደህንድ አገር ተጉዞ የነበረ ቢሆንም አስፈላጊ ህክምናዎችን ስላልጨረሰ ቀጠሮ ተሰጥቶት ተመልሷል።
” የደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት በፊቱ ላይም በሰውነቱ ላይም በግልፅ ይታያል። በዚህ ልጅነቱ ላይ እንደዚህ አይነት ጉዳት መድረሱ ልብ የሚሰብር ጉዳት ነው” ብሏል እስክንድር።
ቤተሰቡን በቀጥታ ማግኘት የምትፈልጉ ኢትዮጵያውያን ወላጅ አባቱን አቶ ወርቁ ዘለቀ በስልክ 0946077691 ማግኘት ትችላላችሁ ።
Filed in: Amharic