>

አዲስ አበባ ከንቲባ መሾምን ተከትሎ በፖለቲከኞች እና አክቲቪስቶች የተሰጡ አስተያየቶች....

ካመት በፊት “ነፍጠኛው ፊንፊኔን ይልቀቅ” ያለ ሰው ከንቲባ ሆኖ መጣ 
ታደሰ ሃይሉ ከበደ
ጠቅላዩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት የሀገሪቱን ህልውና የተፈታተናት የአማራው ጥያቄ ነበር
ስነ ልቦናችን የተረዱት ጠቅላዩ የመናገር እና የሚዲያ ነፃነት አወጁልን እኛም በየከተማው እየተሰበሰብን እንደፈለግነ መናገር ጀመርነ ሻል ያሉትንም ስቱዲዮ ድረስ እየጋበዙ አስተነፈሷቸው
የአማራውን ጥያቄ ከህልውና ወደ ባንዲራ ወረደ ባንዲራም ተፈቀደ በአደባባይ አውለበለበ ተቃቅፎ በፍቅር አነባ አለቀ የፌደሬሽን ምክርቤት የወልቃይት ጥያቄ አግባብ አይደለም አለ አማራው ዝም
የሱዳን ጦር ወንድሞቻችን ከርሻ መሬታቸው ድረስ መቶ እየገደላቸው ነው መከላከያ ወደ አካባቢው ይላክ ጠቅላዩም ዝም አማራውም ዝም
የራያ ህዝብ ማንነት ጥያቄ አነሳ ተሰለፈ የትግራይ ልዩ ሀይል ጋርም ተፋጧል ጠቅላዩ ትግራይ ልዩ ሀይል ብቻውን የራያን ወጣት አይቋቋመውም በትግሬ የሚመራ ጦር ስምንት ስአት ባልሞላ ጊዜ ተላከ አሁን የራያ ህዝብ በተለይ ወጣቱ ከርስት ጉልቱ በመከላከያ እየተደበደበ ከገር እንዲለቅ እየተደረገ ነው አማራው ዝም
ካመት በፊት ነፍጠኛው ፊንፊኔን ይልቀቅ ያለ ሰው ከንቲባ ሆኖ መጣ
አማራን አያሳደደ ያስጨፈጨፈው ኦነግ አገርቤት ገብቶ ሸዋና ወሎን ያካተተ የኦሮሚያ ካርታ ሰርቶ ከሊቅ እስከደቂቅ ማስቆጠር ጀመረ በአደባባይም እየነገሩን ነው አማራው …..ተደምሬያለሁ
አማራ……..ኦሮማራ
ኦሮሞ……. አሮሞ ፈርስት
ከዚሁ ሁሉ የምታመኝ አማራን ተውት ያውራ ሲያወራ ይወጣለታል ወይ ይረሳዋል ብሂል ነው::
አንዳንድ ሰዎች አይናችሁን ጨፍኑና እናሞኛችሁ ይሉናል!!
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
የአዲስ አበባ ከንቲባ ኢህአዴግ እስካለ ድረስ አማራ መሆን አይችልም።ምክንያቱም አማራ ከተሾመ ህገ መንግስቱ ተጣሰ ማለት ነው።ህገመንግስቱ በመግቢያው ላይ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ለማስከበር መጀመሪያ የነበረውን የተዛባ ግኑኝነት ማረም እንደሚያስፈልግ በግልፅ ተደንጉዋል ።ስለሆነም ከአማራ ጭቆና ለመላቀቅ ኢህአዴግ በደሙ የፃፈውን ህገመንግስት ሽሮ አዲስ አበባ ላይ አማራ ከንቲባ መሾም በተዛባ የታሪካዊ ግንኙነት አማራ አዲስ አበባ ላይ ያለውን የበላይነት ለመቀነስና የተዛባውን ግኑኝነት ለማረም የተያዘውን ህገመንግስታዊና አቢወታዊ ትግል ማደናቀፍ ስለሚሆን ፀረ ህገመንግስት ነው።ስለሆነም ኢህአዴግ እስካለ ድረስ አማራ የአዲስ አበባ ከንቲባ እንዳይሆን በህገ መንግስት ተደንጉዋል።
¤¤¤¤¤¤¤
ያ ሁሉ ትግል የተደረገው “ሃጎስ” ተሸኝቶ “ቶላ” ሁሉንም እንድያጋብስ ሳይሆን ለእኩልነት ነው!!!
ቬሮኒካ መላኩ
ዶ/ር ቬሮኒካ መላኩ የ CIA  ጆሮ ጠቢ ናት እየተባለልኝ ነው ። ሃሃሃ። ብአዴን በጀርባው አዝሎና CIA በሁለት እጆቹ  እንደ ህፃን ልጅ እፍስ አድርጎ  ወንበር ላይ ቁጭ እንዳደረጋቸው  ረስተው  🙂
እኔ ቬሮኒካ መላኩ ” ከአዲስ አበባ ሰፋሪ የሚሉትን እናስወጣለን ከሚል ከንቲባ ጋር  ፣ የአዲስአበባ ጥያቄ የማንነት ጥያቄ ነው  ከሚል እና ሁሉንም ስልጣን በስግብግበት ከሚያጋብስ መርዘኛ  አክራሪ ጋር ህብረት የለኝም። እዚህ ስቸከችክ የምውለው ሃጎስ ተሸኝቶ ቶላ ሁሉንም እንድያጋብስ ሳይሆን ለእኩልነት ነው።  የኢትዮጵያ ህዝብ ዘረኛ እንዳልሆነማ አቢይ አህመድን የመጣበትን ብሄር ሳይጠይቅ ፅንፍ የሌለው ፍቅር ሰጥቶ በተግባር አሳይቷል።  ዛሬ ግን የአማራ  የአዲስአበባና ሌላው  ህዝብ የሚፈለገው ቲሸርት ለብሶ እንደ ቺር ሊደር  የድጋፍ ዜማ ወንሴብሆ እንድያቀርብ ብቻ ነበር ።
ፍትሃዊ የስልጣን ክፍፍል በየአንዳንዷ  ቦታ እስክታረጋግጡ እንታገላለን ።
አሁንም ማስተካከያውን እየጠበቅን ነው።
<<የአዲስ አበባና የአዲስ አበባ ዙሪያ ጥያቄ የከተሞች ጥያቄ አይደለም፤ የማንነት (የኦሮሞነት) ጥያቄ ነው>>
ይህንን የተናገረው በዶ/ር አብይ አመርራ ለአዲስ አበባ ከንቲባነት የተሾመው የኦህዴድ/ኦነግ አመራር ታከለ ኡማ ነው።።
በኢትዮጵያዊነት ሰበብ አዲስ አበባን ማወረም ይቁም!!ከህወሃት/ትግሬ የበላይነት ወደ ኦህዴድ/ኦነግ/ኦሮሞ የበላይነት የሚደረግን ሽግግር አጥብቄ እቃወማለው!!

https://www.facebook.com/100003725449932/posts/1291615267639309/

Filed in: Amharic