>

ለኢሳያስ ለምን ውዳሴ አላቀረባችሁም ለምትሉ (አንዷለም ቡከቶ ገዳ)

ለኢሳያስ ለምን ውዳሴ አላቀረባችሁም ለምትሉ
አንዷለም ቡከቶ ገዳ
ከጭፈራውና ከጭራ መቁላቱ ባሻገር…(በቋተ..አንዲ ማኛ…ተነሳበት ደግሞ!)
እንግዲህ አዲሱ ጠሚ ስልጣን ከያዙ በኋላ ሁላችንም ለማለት በሚያስደፍር መልኩ ለምናደርጋቸው ነገሮች የማሰላሰያ ግዜ አጥተን በደመነፍስ ስንቀሳቀስ ከርመናል፡፡….እኔማ በንዳድ በሽታ እንደተጠቃ ሰው (የጊዜው የፖለቲካ ትኩሳት የንዳድ በሽታንም ያስንቃል)  እንደማንኛውም በትኩሳት እንደተጠቃ ሰው በትክክል ማሰብ ካቃተኝ ቆየሁ፡፡…ጠሚያችን አስመራ ሄደው ያሳለፉት ነገር እና የተስማሙባቸው ነገሮች ምን እንደሆኑ አጣርተን እንደ አንድ ተራ ዜጋ አቋም ለመያዝ ስንዘጋጅ…ወዲያው ኢሳያስ ሸገር ድንገት ከች ብሎ  ትንፋሽ ያሳጣናል፡፡ ነገሮች የፈለገ ቢፈጥኑም እኛ አንዲ ማኛ  እንደምንም ተነቃቅተን እራሳችን ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ቸልሰን ለታሪክም እንዲሆን የሚከተለውን ዘግበናል፡፡
እንግዲህ ኢሳያስ ማለት… በእኔ የግል እምነት….ጠሚያችን እንደሚሉት በኢትዮጲያ ህዝብ የተወደደና የተከበረ ወንድም መሪ  ሳይሆን በተለይ በእኔ እድሜ ባሉ እኩዮቼ ዘንድ እንደ እብድ  ይቆጠር የነበረ ለብዙ ሺዎች ኢትዮጲያውያን ህልፈት ተጠያቂ የሆነ …ዛሬ እሱን ካልነካን ብለው ሲሻሙ ኮማንዶ የረጋገጣቸው አርቲስቶቻችን በአንድ ወቅት “ጤናው ተበክሎ ካበደ አንድ ውሻ…. ካልሞተ በስተቀር አይተውም ንክሻ” ብለው የአቀነቀኑለት ፡ከዜጎቹ በተለይ ከወጣቱ ክፍል አብዛኛውን ለስደት እና እንክርት እና የባህር  አሳ እራትነት የዳረገ አሁንም እየዳረገ ያለ የለየለት የምስራቅ አፍሪካ ዲክታተር ነው፡፡
አገር አማን ነው በሰላም በተቀመጥንበት በግንቦት 4/1990 ዓ.ም የኤርትራ ጦር 3 ብርጌድ ባሰለፈበት ድንገተኛ ወረራ ድንበራችንን ያዘ….ለዚህ ተጠያቂው ያው ዛሬ ጭራችንን ዊን ዊን እያደረግን የተቀበልነው የኢሳያስ አመራር ነው፡፡..እነ መሌ እጃቸውን አጣጥፈው በተቀመጡበት “ኤርትራ አትወረንም፡ ልትወረንም አትችልም” እያሉ በቲዎሪ ሲጃጃሉ ይህ ሰው  የሆዱን በሆዱ ይዞ ለወራት በትጋት ባስቆፈረው ምሽግ ወታደሩን አስገብቶ ኋላ ላይ አገራችንን ከፍል ያለ ዋጋ አስከፍሏታል፡፡በነገራችን ሰውዬው በዚሁ ምሽግ ተማምኖ  “..አበሾች ባድመን ከሚቆጣጠሩ ይልቅ ጸሃይ በምስራቅ ብትጠልቅ ይቀላል!”..ሲል መፎከሩ  ሰምተን…”ዘመቻ ጸሃይ ግብአት” ብለን በሰየምነው ጦርነት..የሰዋነውን ሰው ሰውተን ባድመን በቁጥጥራችን አውለን…. ለኢሳያስም ለጀግኖቹና አገር ወዳዶቹ ኢትዮጲውያን  አስፈላጊ ከሆነ “ጸሃይም በምስራቅ ልትጠልቀች” ሁላ እንደምትችል ስናስተምር  እነ ማዘርም ከደስታቸው ብዛት “ሰንሴትን” የሚመስሉ የመሶብወርቅ… ሰፉ …አልጋልብሱ ዳንቴሉ ወዘተ ….ሲሰራ ሲሰፋ ..…..…ዛሬም ትዝታው ትላንት እንደሆነ ሁሉ አይኔ ላይ አለ፡፡.ያኔ ጦራችን በአስመራ የተመረጡ ቦታዎችን (ሚሊታሪ ብቻ ) ሲያጠቃ ሰውዬው የለየለት እብድ ነበረና ጭራሽ የመቀሌን ህዝብ የቀጥታ ኢላማ የሚያደርጉ ጥቃቶች ን ይሰነዝር ነበር፡….በሃይደር… ህጻናት በቦምብ ሲጋዩ በለጋነት ያለቀስኩት ለቅሶ …የነበረኝ ቁጭት ..ይህን ቁጭት ለመበቀል ሁለቱ ሚጎች ሲነሱ ….ትዝ ይለኛል….በነገራችን ላይ በአንደኛው ሚግ ውስጥም በህጻናቱ ጥቃት  በቁጣ የሚንተገተገው ኮሌኔል በዛብህ ጴጥሮስ ….ነበረ…..ይህ ሰው ከዚህ ቀደም በሳህል በረሃ በሻእብያ ተማርኮ የነበረ የአገራችን የምንግዜም  የቁርጥ ቀን ልጅ ነው….ጀግናችን በቁጭት ነዷልና ተው ቢባልም አልሰማምና እስከመጨረሻው ባደረገው ተጋድሎ በድጋሚ በሻእቢያ እጅ ለመማረክ በቃ….ይህን ሰው እስከዛሬ በኢሳያስ እጅ ካለም ይሁን ከሌለ ትላንት ሰልፍ  የወጣው እውነተኛውም ይሁን “ወረዳዊ ወ ክፍለከተማዊ ዝንተ አበላዊ “ህዝብ ሊጠይቅ አልደፈረም ወይ እኔ አላጋጠመኝም፡፡
ይህ ሰው ጀግናችን ነውና ከጭፈራችን እና ከጭራ መቁላታችን ባሻገር አንድ ነገር እንዲባልልኝ እፈልጋለሁ፡፡
በኢሳያስ  ጠብ አጫሪነት በጾረና ..በአሊቴና..በቡሬ በባድመ፡ በሽራሮ…ዛላንበሳ..ወዘተ በሺዎች የሚቆጠሩ ጀግና ወጣቶቻችን ረግፈዋል፡፡…..
ከጭፈራችን መሃል ስለነዚህ ሰዎች የህሊና ጸሎትም ሆነ ከታቸለ ሁለቱም መሪዎች ይቅርታ የሚያሰሙበትን ንግግር መስማት እፈልጋለሁ፡፡
በነገራችን መሃል ..ዛሬ ዘምባባ እና ሳር ጎዝጉዘን በእልልታና በሆታ የተቀበልነው መሪ ከአመታት በፊት አገራችን ኢትዮጲያ ኤርትራን በቅኝ ግዛትነት ይዛለች ብሎ በረሃ የገባ …በየአመቱ አገሩ “ከቅኝ ግዛት የተላቀቀችበትን” ቀን ድል ባለ ድግስ የሚያከብር …ስር የሰደደ ጸረ-ኢትጲያዊነት አቋም ያለው መሪ ነው፡፡…
ብዙዎች ብታቃልሉትም…..ፈረንጆችና እና አፍሪካውያን እንኳን በማይችሉት አማርኛ ስብሰባ ሲጀመር “ቴና ኢስቲሊኝ” ብለው ሲጀምሩ …(ኮሪያዊው ባንኪሙን ሳይቀር) ..በጉርምስናው ዘመን የደሴ የወ/ሮ ስህን ተማሪ  የነበረው ይህ ሰው ግን …ተሳስቶ አማርኛ ለመናገር ሲተናነቀው አይተናል(ልበ ቅኑ እና አስተዋዩ ጠሚ ..ድምጽ ማጉያውን ነጠቅ አድርገው..”አይዟችሁ ለዛሬ ነው እንጂ ነገ ይናገራል እስከሚሉ ድረስ …”ዛሬ ጠፍቶበት ነው ነገ ይችላል ነው ወይስ ምንድነው …?!” አልገባኝም)
የሆነስ ሆነና አዲሱን ጠሚ የምንወዳቸውና የምንሳሳላቸውን ያህል….በአንዳንድ ጉዳዮች ደግሞ ከእሳቸው መለየት መብታችን መሆኑን በማመን  …ስለ ኢትዮኤርትራ ግኑኝነት ማደስ ሙሉ በሙሉ ሃሳባቸውን ብንቀበለውም ለኢሳያስ በግሉ እየተደረገለት  ያለው ክብር ከሚገባው በላይ መሆኑን እና የማንስማማበት መሆኑን (ከላይ በገለጽናቸውና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች) በራሳችን ፔጅ እንዲመዘገብልን እንጠይቃለ፡፡..በተያያዘም ለዚሁ ሰው ክብር በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው ግብዣ ላይ ለመገኘት በኢመደበኛ መልኩ አግኝተነው የነበረውን ካርድ ቀደን የጣልን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ይህ የእኛ የአንዲ ማኛ የግል እና ጥብቅ  አቋም ስለሆነ የማይስማማ ካለ የራሱ ጉዳይ እንጂ እንደሌላው ግዜ የምከራከርበት አይሆንም፡፡
ይመቻችሁ፡፡
Filed in: Amharic