>

የሆነውን ሁሉ ስናይ ሁለት ሰላላ ጥያቄዎች ከፊት ለፊታችን ጅዋጁዌ ተጫወቱ!!! (በፍቃዱ ሞረዳ)

የሆነውን ሁሉ ስናይ ሁለት ሰላላ ጥያቄዎች ከፊት ለፊታችን ጅዋጁዌ ተጫወቱ!!!
በፍቃዱ ሞረዳ
 እነዚህ ሬንጀር ለባሽ ባለቀይመለዮ ወጣት ወታደሮች የማን ናቸዉ? ደረታቸዉ ላይ ያለዉን የአየር ወለድ (ዘላይ) ክንፍ (ዊንግ) ከዬት አመጡ?
  ምክንያቱም ‹‹የኢትዮጵያ ጦር›› በዘመነ ወያኔ አየር ወለድ ጦር አሰልጥኖና በፓራሹት ከአዉሮፕላን ማዘለሉን የሚነግረን መረጃ ስለአላገኘን ነዉ፡፡
የያኔዉ የአየር ወለድ አሥር አለቃ፣ የዛሬዉ በሙሉ ጄኔራል ማዕረግ የመከላከያ ዘመቻ ኃላፊ ብርሃኑ ጁላ የራሳቸዉን ዊንግ እያባዙ ለባለሥልጣናቱ አጃቢዎች ማደል ጀመሩ? ሳይዘሉ ዊንግ ማድረግ ሼም ነዉ፡፡ ስለፌክ ኒዉስ እንጂ ፌክ ኤር ቦርን አልሰምቶም፡፡  ሳናዉቀዉ የሆነ ነገር ካለም ንገሩንና እንደመር፡፡
   ሌላዉ በዚሁ ፎቶ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ (የኢሕአዴግ ሊቀመንበሩ) እንግዳቸዉን ከእነአቶ ለማ ጋር ሲያስተዋዉቁ የሀገሪቱ መንግሥት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የት እንደቆሙ ተመልከቱ፡፡ አዲሱ ለዉጥ ነባሩን የፕሮቶኮል ሥርዓት መናድን ይጨምራል? ወይስ የስቪል ደህንነቱን ሥራ አቶ ደመቀና ዶክተር ወርቅነህ ተረከቡት? እርሱም ቢሆን ጥሩ ነዉ፡፡ አንድ ቀዳዳ መሸፈን እስከቻሉ ድረስ፡፡
ብቻ አጀቡ ላይ ወታደሮች በዙ፡፡ጋዳፊ ትዝ አሉኝ፡፡ ነፍሳቸዉን ይማርና፡፡ ያ የማይገባቸዉን መለዮ የለበሱ ወታደሮች የሚርመሰመሱበት ቦታ በስቪል ደህንነቶች መሸፈን በተገባ፡፡ ግን ጅቡ ያን ያህል አስፈሪ ነዉ ማለት ነዉ?
  ትዝብታችን የአላዋቂ ዝልበዳ ከመሰላችሁ፣ ሥራችሁ ያዉጣችሁ፡፡ የድል አጥቢያ መንጋ ጀግኖችን የጭቃ ጅራፍ ባንፈራ ኖሮ ሌላም ጣት የምንቀስርበት ነገር ነበረን፡፡ እንደአቃቂር ሳይሆን ፣እንደዜጋ ምክር፡፡
    ዋናዉ ነገር ወደሠላም የሚወስደዉ ጉዞ መጀመሩ ነዉ፡፡ መንገዱ ግን እንደ ቃል እንደ ምኞት አጭር ሊሆን ስለማችል ደህና ስንቅ መሰነቅ፣ ሁነኛ ትጥቅ መታጠቅ ያስፈልጋል፡፡ Defeat hate.
Filed in: Amharic