ዶ/ር ዓቢይ አህመድ የመጨረሻ የሰላም ጥሪ
ጆሮ ያለው ይስማ ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶችን ለሚፈጥሩ የቀን ጅቦች ወደ ሰላም እንዲገቡ የመጨረሻ የሰላም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
–
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያ ውስጥ ዛሬም በሚያሳፍር ሁኔታ ሰዎች ይሞታሉ” በማለት ንግግር ያሰሙ ሲሆን ይህ እንዲያበቃም “እባካችሁ ወደ ሰላም ግቡ፤ ይህ የመጨረሻ የሰላም ጥሪዬ ነው” ብለዋል፡፡
–
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ እና በአስመራ መካከል ያለው የጥላቻ ግንብ መናዳን አንስተው በአንዳንድ ክልል ያለው “የሳር ቀጤማ ግንቦች ይፍረሱ” በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
–
የዛሬው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ይዘው የመጡት ፍቅር በ50 ቢሊየን ብር የማይገዛ ውድ ነው ብለዋል፡፡ እንዲሁም ዛሬ የተቀደደው ጥቁር መጋረጃ ነው የሚበጀን ፍቅርና ሰላም ብቻ ነው….፡፡
–
በተጨማሪም የሰላም ዋጋው ያልገባቸው አካላት በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች እንደሚያስነሱ ጠቅሰው ዛሬ እንኳ ስለ ሰላም ተማሩ በማለት ጥሪ አቅርበውላቸዋል፡፡
–
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሰዎች ሞት ማብቃት አለበት ያሉ ሲሆን የሰላም ጥሪያቸውን አጽንዖት በመስጠት አስተላልፈዋል፡፡
–
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጨረሻም አልፎ አልፎ የምታውኩን ሰዎች ፍቅራችንን ባታበላሹት መልካም ነው ነገርግን ግጭቶች በዚህ የሚቀጥሉ ከሆነ ሰውነንና ወዳልተፈለገ ነገር እንዳታስገቡን አደራ እላለሁ ብለዋል፡፡