>
5:13 pm - Saturday April 19, 8177

ሌቦቹ በቃችሁ ሊባሉ ፤ ህግም ፊት ሊቀርቡ ይገባል (ይልማ ኪዳኔ)

ሌቦቹ በቃችሁ ሊባሉ ፤ ህግም ፊት ሊቀርቡ ይገባል
ይልማ ኪዳኔ
ሜ/ጄ ክንፈ ዳኜ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ተብሎ የሚጥራውና በወታደሮች በሚመራው ትልቁ የመንግስት ኢንዱስትሪ ውስጥ ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ራሳቸውን “በፈቃደኝነት” እስከ አገለሉበት ጊዜ ድረስ ይሰሩ ነበር። ይህ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የሃገር ሓብትና ንብረት የሚዘረፍበት ቦታ እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። እዚህ ፎቶግራፍ ላይ የሚታየው ትንሽ ቤተ መንግስት የመሰለ ነገር የእሳቸው ቤት ነው። የኤርትራውን ፕሬዚዳንት የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂን አኗኗር ከተመለከት በኃላ ለእሳቸው ያለኝ ከበሬታና አድናቆት ሲጨምር የእኛዎቹ ሌቦች አኗኗር ግን ይበልጥ የሚዘገንን ከመሆንም አልፎ ምን ያህል ጨካኞች እንደሆኑ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው።
………………
ሜ/ጄ ክንፈ ዳኜ ወታደር እንጂ ነጋዴ እንዳልሆኑ እሳቸውም የሚክዱት ነገር አይመስለኝም። ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ በደሞዛቸው ቤተሰብ አስተዳድረውና ለኑሮ የሚያሰፈልገውን ወጪ ሸፋፍነው የምትቀራቸውን ትርፍ ገንዘብ ወደ ጎን በማድረግ በቁጠባ እንኳን ይሄን ቤት መስራት አይደለም የቤቱን መስኮቶችንም መግዢያ የሚሆን ገንዘብ መቆጠብ አይችሉም። በእርግጥ ሜ/ጄ ክንፈ ዳኜ ቢጠየቁ ቤቱን የሰራሁት በቀጠባ ካስቀመጥኩት ገንዘብና መንግስት በትግል ጊዜ ላደረኩት “አስተዋጾ የሰጠኝ ገንዘብ” የሚሉት ቋንቋ አላቸው ጋር በማጣመር ነው ይህን ቤት የሰራሁት እንደሚሉ ምንም ጥርጣሬ የለኝም። የሟቹ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ለመቀለ የእግር ኳስ ክለብ 30 ሚሊዮን ብር ስጦታ ስትሰጥ የተናገረችው የሚረሳ አይደለም። ወ/ሮ አዜብ ስትናገር በወር ከማገኛት ስድስት ሺህ ብር ላይ በመቆጠብ ነው ይህን የገንዘብ ስጦታ ለክለቡ የሰጠሁት ብላ ስትናገር ወይ የሚታዘበኝ የለም ብላ አሊያም ህዝቡን እንደ ደንቆሮ ቆጥራው ሊሆን ይችላል። ምንም አፍረት የሚባል ነገር የፈጠረባቸው ሰዎች አይደሉም።
………
ታግለው የመጡት የዚህን ምስኪን ድሃ ህዝብ ሃብትና ንብረት ለመዝረፍ ነው የሚመስለው። ወይስ ከትግራይ ውጭ ያለውን ህዝብና አገር እንደ ቅኝ ግዛት እያዩት ይሆን? ካልሆነስ እንዴት ለዚህ ደሃና ጨዋ ህዝብ ማዘን አቃታቸው? ሰርቀው በሚያገኙት ገንዘብ ጠግበው ሲደነፉ እንዴትስ በትግል ወቅት የተስዉት ጓደኞቻቸው አጥንት አይቆሮቁራቸውም? በጣም የማይገባኝና ፈጽሞ መልስ ላገኝለት ያልቻልኩት ጥያቄ ቢኖር፤ እንዴት እንቅልፍ ሊወስዳቸው ይችላል? የትግራይስ ህዝብ ይታዘበናል ብለው አይፈሩም ወይ? እነሱ ጮማ ሲቆርጡና ውስኪ ሲራጨው ውለው እና አድረው ከቤት ሲወጡ በየመንገዱ ላይ ቸግሮት የሚለምነውን ድሃ የእኔ ቢጤ ሲያዩ ከዚህ ድሃ ህዝብ መዝረፍ ፀያፍ ነገር እንደሆነ እንዴት ህሊናቸው አይነግራቸውም? ደንቆሮዎችና ጨካኞች ስለሆኑ ከህዝብ ሰርቀው እንዲህ ተንደላቀው በመኖር የተጠናወታቸውን የበታችነት ስሜት ለማስታገስ ይሆን እንዲህ የሚዘርፉት? አሁን ግን ሌቦቹ በቃችሁ ሊባሉ ይገባል። ህግም ፊት አቅርቦ ፍትህ እንዲያገኘ ማድረግ ተገቢ ይመስለኛል።
Filed in: Amharic