>

አምሳሉ ገ/ኪዳን ለዳግመኛ ጊዜ በማዕከላዊ ተጠራ

በዳዊት ሰለሞን የዕንቁ መጽሔት የመጋቢት ወር 2006 ዕትም ላይ ‹‹የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ ሐውልቶች ለምንስና ለማን ናቸው ››በሚል ርዕስ የመጽሔቷ አምደኛ አምሳሉ ገ/ኪዳን ያቀረቡት ጽሁፍ በጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆኖብኛል በማለት ጅማ ዩኒቨርስቲ አቤቱታ በማቅረቡ የተነሳ የመጽሔቷ ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ለአራት ቀናት በማዕከላዊ ታስሮ በዋስ መለቀቁ አይዘነጋም፡፡
ዋና አዘጋጁ ከተፈታ በኋላ የማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ሰራተኞች የጽሁፉ ባለቤት ለሆነው አምሳሉ ገ/ኪዳን ደውለው እንደሚፈልጉት ስለነገሩት በወቅቱ ወደ ተጠራበት ቢሮ አምርቶ ነበር፡፡‹‹ስንፈልግህ እንጠራሃለን››በማለትም ያለምንም ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲመለስ አድርገውት ነበር፡፡
ዛሬ ማለዳ በድጋሚ የማዕከላዊ መርማሪዎች አምሳሉ ቃሉን እንዲሰጥ በመጥራታቸው ከምሳ በኋላ ወደ ስፍራው አምርቶ ነበር፡፡በማዕከላዊ ስለ ጽሁፉ ቃሉን እንዲሰጥ የተደረገው አምሳሉ ‹‹የቤት ካርታ ወይም የመንግስት ሰራተኛ አልያም የመኪና ሊብሬ በዋስትና በማስያዝ መውጣት እንደሚችል ቢነገረውም ሰዓቱ በመግፋቱ የተነሳ የተጠየቀውን ማሟላት ባለመቻሉ በማዕከላዊ ሊያድር እንደሚችል ለአምሳሉ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ተናግረዋል፡፡

Filed in: Amharic