>
5:13 pm - Sunday April 19, 0809

" መደመርን የማይቀበል ሸይጣን ብቻ ነዉ"  አብዲ ኢሌ 

 ” መደመርን የማይቀበል ሸይጣን ብቻ ነዉ” አብዲ ኢሌ 
በቬሮኒካ መላኩ
ከ3 ቀናት በፊት ጀምሮ እንደሰማሁት ለቅዳሜው የመቀሌና አካባቢው በሚደረገው ሰልፍ ከተዘጋጁት ቲሸርቶች ውስጥ ወደ 500 የሚደርስት ቲሸርቶች የሱማሌው ክልል ፕሬዚደንት አብዲ ኢሌ ፎቶ ያለበትና ከፎቶው ስር ” የፌደራል ስርአቱ የቁርጥ ቀን ልጅ ” እና ” ለተገፉ ደራሽ! ” የሚል ፅሁፍ ነበረበት ።
በትናትናው እለት የሱማሌ ክልል አስቸኳይ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ አብዲ ኢሌ * ጌታቸው አሰፋ እና ህውሃቶች ጣልቃ እየገቡ ሱማሌን ክልል በጥብጠዋል፣አላሰሩኝም፣የ ሱማሌ ህዝብን የገደሉት ፣የጨቆኑት እነሱ ናቸው ” * ” 20 ሚሊዮን ብር አስገድደው ከጎንደር ለተፈናቀሉ ለትግራይ ተፈናቃዮች ስጥ ተብዬ የማላምንበትን ብሩን በግዳጅ ከክልላችን ወስደዋል ” የሚልና ሌሎች የሚያሳፍሩ ወንጀሎችን ከደፈደፈባቸው በኋላ እነዚያ የአብድ ኢሌ ፎቶ ያለባቸው ቲሸርቶች ተሰብስበው በእሳት ተቃጥለዋል።
ይሄው ነው እንግድህ መርህ አልባ ፍቅርና አጋርነት መጨረሻው ። በአሸዋ ላይ እንደተገነባ ቤት ትንሽ ውሽንፍር ሲነካው ይደረመሳል።
በልጅነታችን የሰማነው ጅብ በመንገድ ሲጓዝ ስለማይተማመኑና አንዱ ሌላውን እንዳይበላው ስለሚፈራሩ ከፊትና ከኋላ አይሄዱም የሚባለው ትክክል ነው። ዛሬ አብድ ኢሌና ህውሃት የተባሉ ጅቦች አንዱ ሌላውን እየቦጨቀው ነው። በመጨረሻም አብዲ ኢሌ ለህውሃቶች ” መደመርን የማይቀበል ሸይጣን ብቻ ነዉ” በማለት ሸይጣን የምትል አዲስ ስም ጀባ ብሏቸዋል።
Filed in: Amharic