>
5:13 pm - Friday April 19, 2774

የኢትዮጵያ ገበሬ ጦር ዛሬ ከሱዳን መደበኛ ጦር ጋር ግማሽ ቀን የፈጀ ከፍተኛ ውጊያ አካሂዷል!!! (አዳነ አጣነው)

የኢትዮጵያ ገበሬ ጦር ዛሬ ከሱዳን መደበኛ ጦር ጋር  ግማሽ ቀን የፈጀ  ከፍተኛ ውጊያ አካሂዷል!!!
አዳነ አጣነው
እብሪተኛው የአልበሽር መንግስት ኢትዮጵያን ከወረረ ይኸው ከ 2 ሳምንት በላይ ሆኗል፡፡ በኢትዮጵያ በኩል እንደመንግስት ዳር ድንበርን ለመከላከል የተወሰደ እርምጃ የለም፡፡በአጭሩ ኢትዮጵያ ውስጥ አሁንም ቢሆን እንደ አለፉት 27 አመታት ሁሉ፣ የኢትዮጵያን ጥቅም ችላ የማለቱ አባዜ በለውጥ ስም በሚምሉ አስመሳይ ኢትዮጵያዊ ነን ባዮች እና  ቧልተኞች በከፋ መልኩ እንደቀጠለ ነው፡፡
 ከአሁን በፊት ሱዳን የወረራውን አድማስ እያሰፋ ያለምንም ስጋት የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በስፋት እየጣሰ የጦር ካምፖች መመስረቱን በተከታታይ መግለጻችን ይታወቃል፡፡ዛሬ ከጥዋቱ (በኢትዮጵያ)  የቁርጥ ቀን ገበሬዎች “በወድ ከዉሊ”በኩል አቕርጦ የተሻገረውን መጠነ ሰፊ የሱዳን ጦር ያለ መንግስት እርዳታ በመግጠም ከ 4ሰ አት በላይ ከፍተኛ ውጊያ ተኻሂዷ፡፡
በዚህ ውጊያ እስከ አንፍጫው በዘመናዊ ከባድ መሳሪያ የታጠቀውን የሱዳን ከፍተኛ ሰራዊት በኢትዮጵያ የንብስ-ወከፍ መሳሪያ በታጠቁ  ገበሬዎች ጉዳት ደርሶበት ተሸንፎ በማፈግፈግ ወደ መጣበት ተመልሷል፡፡ የህዝብ ጦር ድል ተቀዳጅቷል፡፡ በአሁኑ ሰአት ህዝቡ በከፊል ወደ አብደራፊ እና አብርሀጅራ ከድል በኻላ በመመለስ ላይ ነው፡፡
በህዝብ እና በሱዳን ጦር ውጊያ ሲካሄድ የኢትዮጵያ ሰራዊት ነኝ የሚለው ሰራዊት አይመለከተኝም ብሎ እራሱን ከሱዳን በሚወረወር ከባድ መሳሪያ ጉዳት እንዳይደርስበት ከመሸሸት ውጭ ያሳየው ነገር የለም፡፡ አሁን ከስአት በኻላ ጦርነቱ ጋብ ማለቱን የተገነዘበው የወያኔ-ትግሬ ሰራዊት ከውጊያ የሚመለሰውን ህዝብ  ስለ ውጊያው ውሎ ወሬ ጠያቂ ሆኗል፡፡ እጅግ ያሳዝናል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሰራዊት የእርሻ ስራውን በመተው እስከ ጠገዴ ድረስ ስንቁን ሰንቆ በመምጣት በጠረፍ የሚገኘውን ብዛት ያለው የህዝብ ሰራዊት ተቀላቅሏል፡፡ አሁንም ሱዳን መጠነ ሰፊ ሰራዊት ከደለሎ እስከ ሽመለጋራ ድረስ የጙንግን ወንዝ ተሻግሮ ያለስጋት ሰፍሯል፡፡ ህዝቡ መንግስት ነኝ የሚለውን አካል የሚወስደው እርምጃ እየጠበቅ ነው፡፡ ሆኖም ባለው መረጃ፣ እነ አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ድንበር መጣስ ብዙ የሚያሳስባቸው አይደለም፡፡እነ አብይ በዋናነት የራሳቸው አጀንዳ ያላቸው ተወናዋይ ቡድኖች ናቸው፡፡ህዝብ በቅርብ ቀን የራሱን ውሳኔ በሱዳን ላይ ይወስናል፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!
Filed in: Amharic