>

የቀድሞው ፕሬዚዳንት በባንዲራው ጉዳይ ምን እያሉ ነው?!?  (ዳንኤል ተስፋዬ)

ቀድሞው ፕሬዚዳንት በባንዲራው ጉዳይ ምን እያሉ ነው?!?  ዳንኤል ተስፋዬ
 ~~~
* “የባህር ዳሩ ሰልፍ ሕገ-መንግስቱን ሙሉ በመሉ ይፃረራል”
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
* “እኛ የምንፈልገው የድሮውን ፣ የነገስታቱን ፣ የእነ አፄ ኃይለ ሥላሴን ባንዲራ፣ የእነ ምንሊክን ባንዲራ ነው” የሚሉ ሰዎች ሀሳባቸውን በዲሞክራሲ መንገድ አቅርበው ሕገ-መንግስቱ የሚሻሻልበት መንገድ አለ”
 
* ” በባህርዳር ስታዲየም ላይ የተገኘው ህዝብ መቶ ሚሊዮን የሚሆነውን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀርቶ የአማራውን ህዝብ አይወክልም
~~~~
 ይህ ፅሁፍ ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 30/10/2010 ዓ.ም ከወጣው “ግዮን” መፅሔት ጋር በባንዲራው ጉዳይ ቃለ-ምልልስ ያደረጉት የቀድሞ የኢ.ፌ.ዲ.ሬ ኘሬዛዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ናቸው። አንብቡና ሚዛናዊ አስተያየት ስጡበት!! 
~~~~
#ግዮን:- ሰሞኑን ለጠ/ሚኒስተር ዐብይ አህመድ በተዘጋጀ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ፣ ህዝብ በነፃነት ሀሳቡን ሲገልፅ ነበር። የነፃነት ታጋዮች ተወድሰዋል ፤ ኮኮብ አልባው ሰንደቅ ዓላማ ተውለብልቧል። ኮኮብ ያለበት ባንድራ አለመፈለጉን ይህ አያሳይም?
~~~~
ዶ/ር ነጋሶ:- በእኔ በኩል ግለሰቦች እና ፓርቲዎች የሚወክሏቸው አመለካከቶች አሉ። የፓርቲዎችና የግለሰቦችን መብት ማክበር በጣምአስፈላጊነው። በሌላ መልኩ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት ማክበር አለብን። ሕገ-መንግስቱን ተመርኩዘው የወጡ ህጎችን ማክበር አለብን። በእኔ እይታ አዲስ አበባ ላይ በተደረገው የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ የተለያዩ ዓይነት ባንዳራዎች ይታዩ ነበር። ከላይ እንደገለፅኩት ይህ የተለያዩ አካላት ሰሜት ነው። በተለያየ አቅጣጫ የሚነቀሳቀሱ አካሎች በአንድነት የጠ/ሚኒስትሩን እንቅስቃሴ መደገፋቸው ጥሩ ነው። ሁሉም የራሳቸውን አመለካከት ይዘው ማለት ነው።…..የባህር ዳር የድጋፍ ሰልፍ ግን ሙሉ በሙሉ ከአዲስ አበባው የድጋፍ ሰልፍ ይለያል።  *በእኔ እይታ ሕገ-መንግስቱ መፃረር ነው ማለት ይቻላል። ለሕግ ተገዢ ያለመሆን ነገር የተነፀባረቀበት ነው ብዬ ነው የማምነው።
~~~~
#ግዮን:-በምን መልኩ ነው ሕገ-መንግስቱን የሚፃረረው?
~~~~
 ዶ/ር ነጋሶ:- ሁላችንም እንዳየነው አንድ ወይም ሁለት ካልሆነ በስተቀር ፤ የአማራ ክልልን ባንዲራም ሆነ የፌደራል መንግስቱን ሰንደቃለማ በድጋፍ ሰልፉ አላየሁም። ሕግ የሚከለክለው አረንጓዴ ፣ ቢጫ፣ ቀይ ባንዳራ ነበር በብዛት የታየው። ስታዲየሙን ሙሉ በሙሉ የሸፈነው የድሮ የኢትዮጵያ ባንዲራ ነው። ይህ በሕግ ተከልክሏል።
*እነዚያ ባንድራዎች አንድ ሊያደርጉን እንደማይችሉ አይተን ፤ በ1987 ዓ.ም የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ የሚደመር፣ ሃይማኖታችንን በሙሉ የሚደምር፣የተለያዩ ግለሰቦችንነና ቡድኖችን የሚያግባባና ሁላችንም አንድ የሚያደርግ ባንድራ የቱ ነው? ብለን በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ ሦስት ላይ አስቀምጦበባህር ዳር የታየው ግን ይሄንን የሚቃረን ነው። በእርግጥ የመቃወም መብት የሁሉም ነው፤ ይህንን መከልከል አያስፈልግም።…ነገር ግን ሕገ-መንግስት  ሳይሻሻል ‘እኛ የምንፈልገው የድሮውን ፣ የነገስታቱን ባንድራ ፣ የእነ አፄ ኃይለ ሥላሴን ባንዲራ ፣ የእነ ምንሊክን ባንድራ ነው የምንጸልገው’ የሚሉ ሰዎች ሀሳባቸውን በዲሞክራሲያዊ መንገድ አቅርበው ሕገ መንግስቱ የሚሻሻልበት መንገድ አለ።
*ሰዎች በባንዲራው ላይ ተቃውሞ ሊኖራቸው ይችላል። ግን ይሄንን ሕገ-መንግስቱ እንዲሻሻል መጠየቅ ነው እንጂ የድሮ ባንድራ ይዘው በመውጣት ሀሳባቸውን በሌሎች ላይ መጫን አይችሉም። እኔ እነደሚመስለኝ ባህር ዳር ላይ የታየው ሰንደቅ ዓላማ ኢትዮጵያን አንድ የሚያደርግ አይደለም። ሰዎች ትክክል ነን ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፤ ግን ያ ባንድራ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን አንድ ያደርጋል ተብሎ አይታመንም።
~~~~
#ግዮን :-ሕዝቡ ግን ” አንድነታችንን ይገልፃል ሁሉንም ህዝብ ያግባባል” ብሎ ኮኮቡን ለኢህአዴግ ትቶ ንፁሁን ሰንደቅ ዓላማ ራሱ ያውለበለበው፤
~~~~
 ዶ/ር ነጋሶ:- ሰዎች ትክክል ነው ብለው ካመኑ የድሮውን ሰንደቅ አላማ መሸከም ይችላሉ። የሚሸከሙት መብታቸው ቢሆንም፤ በይፋ ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ባንዲራ ይህ ነው ብለው የሚከራከሩ ሰዎች ካሉ ስህተት ነው ብዬ ነው የማምነው።
ኮኮቡ እንዲነሳ የሚፈልጉ ሰዎች ካሉ ፣ መጠየቅ መብታቸው ነው፤ ሕገ-መንግስቱ ላይ አንቀፅ ሦስት እንዲሻሻል ሕጋዊ አካሔድን መከተል ነው ያለባቸው እንጂ በእንዲህ አይነት ሰልፍ ላይ አይደለም ሌላ ነገር የሚያስተጋባው።
~~~~
#ግዮን:- ሰልፉ ላይ የታየው የሰንደቅ አላማ ለውጥ በራሱ እኮ ግልፅ ነው ማለት ይቻላል። መንግስት ከዚህ ተነሥቶ የባንዲራውን ጉዳይ መልስ ሊሰጥበት አይገባም?
~~~~
 ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ:- በባህር ዳር ስታዲየም ላይ የተገኘው ህዝብ መቶ ሚሊዮን የሚሆነውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ቀርቶ ጠቅላላ የአማራ ክልልን አይወክልም። የተወሰኑ ግለሰቦች ናቸው በስታዲየም የተገኙት ፤ እነዚያ ሰዎች በዚያ መንገድ ሀሳባቸውን ሊያቀርቡ ይችላሉ።
* ግን ቀድም ሲል እንደገለፅኩት ፤ ሕገ-መንግስቱ በግልፅ የሀገሬቱን ህዝቦች እኩልነት የሚያረጋግጥ ነው ያለውን ባንዲራ ይፋ አድርጓል። በሕግ ፀድቋል። በ1993 ዓ.ም ሕገ-መንግስቱ ሲረቅ  እኔ ኦህዴድን ፣ ዳዊት ዮሐንስ ኢህዴን (ብአዴንን) ወክለን ተግኝተናል። ያኔ ኢህአዴግን አይደለም የወከልነው ፤ በሕገ-መንግስቱ ላይ ስንወያይ ከሁለታችን ውጪ ሃያ ሰባት የሌላ ፓርቲ ተወካዮች ነበሩ። አጠቃላይ 29 ሰዎች ነን የተወያየንበት፤ እኛ ተነጋግረን ነው ሕገ-መንግስቱን ወደ ሽግግር መንግስት ተወካዮች ም/ቤት ያቀረብነው።
*ስለዚህ ያኔ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረን ፣ ተከራክረን ሕግ አውጥተናል። የሰንደቅ አላማው ጉዳይም በዚያ መንገድ የራሱ ሕግ በሕገ-መንግስቱ ተቀሞጦለታል። በእርግጥ እነደሚባለው ሕዝብ የድሮውን ሰንደቅ ዓላማ የሚናፍቅና የሚደግፍ ከሆነ ፣ በቀጥታ ሕጋዊ መንገድ ነው መከተል ያለበት። ግን እኔ እንደሚገባኝ በባህር ዳር ላይ የታየው ነገር የሁሉንም ኢትዮጵያ ሕዝብ አይወክልም።
Filed in: Amharic