>

ባንዲራ ፈፅሞ ሊያጋጨን አይችልም ትስሰራችን በደም ነዉ፤ ደም ከባዲራ ይበልጣል!!! (ታዬ ደንደአ)

ባንዲራ ፈፅሞ ሊያጋጨን አይችልም ትስሰራችን በደም ነዉ፤ ደም ከባዲራ ይበልጣል!!!
ታዬ ደንደአ
ጅብ እንደልቡ ግጦ የበላን በአቅሙ ሳይሆን አንዳችን በሌላችን ላይ ጅብ በመሆናችን ነው!
 
ከዝህ በፍት ብያለዉ። አሁንም ደግሜ እላለሁ። ኦሮሞ እና አማራ ከህዝብ ብዛትም ሆነ ከቆዳ ስፋት አንፃር የኢትዮጵያ መሠረት ናቸዉ። ታሪክም ይህንኑ ይመሰክራል። ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚፈልግ ጠላት ሁለቱን ህዝቦች ያጋጫል። ጅብ እንደልቡ ግጦ የበላን በአቅሙ ሳይሆን አንዳችን በሌላችን ላይ ጅብ በመሆናችን ነዉ።
አሁን የተለያዩ ሰበካዎች እየተሰሙ ነዉ። ኦሮሞ እና አማራ የተለያዩ ባንዲራዎችን ይዞ አደባባይ ሲለወጡ ነገ ጧት ሊዋጉ ነዉ በማለት ሟርት ጀምሯል። በሬዲዮና በቴሌቭዥን ራሳቸዉ ለራሳቸዉ ሲያወሩ ሰምተናል። ግን ባንዲራ ፈፅሞ ሊያጋጨን አይችልም። ትስሰራችን ከባንዲራ በላይ ነዉ። ደም ከባዲራ ይበልጣል። መተባበር ለኛ የህልዉና ጉዳይ ነዉ። ይህን በተግባር አይተናል። በተከፋፈልን ጊዜ የጅቦች መጫወቻ ሆንን። በተባበርን ጊዜ ደግሞ ከራሳችን አልፈን የምስራቅ አፍሪካ ዋስትና ሆንን። የነፃነት እና የአንድነት አየር መንፈስ የጀመረዉ ከህብረታችን ባህር ነዉ። ህብረታችን ገና ለአፍሪካ እና ለዓለምም ብርሃን ይሆናል።
በእርግጥ መንገዱ ሁሉ አሰፓልት አይደለም። በሁለቱም በኩል ፅንፈኛ ጫፎች አሉ ። ግን ይህ ተዓምር አይደለም። በመጠኑ ሁሌም ሊኖር ይችላል። ከነበረዉ የጅቦች ሴራ አንፃር ፅንፈኛ ባይኖር ነዉ የሚገርመዉ። “እሳት እና ጭድ፣ አህያና ጅብ ..” ወዘተ ተብለናል እኮ። ስለዚህ ብዙም ማጋነን አይገባም። ዋናዉ ጉዳይ ፅንፍ የወጡ አስተሳሰቦችን በጊዜ መግራት ነዉ። የሚጠቅመንን እና የሚጎዳንን በደንብ እናዉቃለን። ብንተባበር እንቆማለን። ብንከፋፈል እንወድቃለን። ክፍፍል የጠላታችን አጀንዳ ነዉ። ስለዝህ በባንዲራ አንጣላም። ብዙ የጋራ ጉዳዮች አሉን። ያንን እያደር እናጎለብታለን። ልዩነቶችም እንዳሉን አንክድም። የግል ጉዳዮቻችንን በግል እና የጋራ ጉዳዮቻችንን በአንድነት ይዘን በፍቅር ተደምረናል! ይህን የሚጠላ ጅብ ብቻ ነዉ። ሀገር የሁላችን መሆኑን እንስማማለን። ጎንደር ሀገሬ ነዉ! አዳማ ወይም አምቦ ደግሞ የገደኛዬ ዉብሸት ሙላት ሀገር ነዉ!
አይደለም እንዴ? ሠላም እደሩ!
Filed in: Amharic