>

"የአሁኖቹ አመራሮች የ97ቱ ጋዜጦችና መፅሔቶች ውጤቶች ናቸው!!!" (ሜጀር ጀነራል ተ/ብርሀን አርአያ)

“የአሁኖቹ አመራሮች የ97ቱ ጋዜጦችና መፅሔቶች ውጤቶች ናቸው!!!”
ሜጀር ጀነራል ተ/ብርሀን አርአያ
#ህወሓት በዛሬው ዕለት የትግራይ ቴሌቭዥን ከምሽቱ 1-3 ሠዓት በቀጥታ ስርጭት የቀድሞውን የመረጃ መረብና ደህንነት ኤጄንሲ ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ተ/ብርሀን አርአያ እና ገ/መድህን ገ/ሚካዔል የሚባል የዩንቨርስቲ መምህር ጋብዘው የሰሞኑን የጠሚ ዓቢይ የድጋፍ ስልፍ በተመለከተ ሲያወያዩ ያነሱትን አሳፋሪም ሆነ አስገራሚ ሀሣቦችን  ከትግርኛ ወደ አማርኛ አጠር አድርገን ተርጉመነዋል።
.
<<…ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የፓንዶራ ሣጥን ተከፍቷል። በፓንዶራ ቦክስ የተለያዩ አውሬወች ሠይጣናት ነበሩ። አሁንም አዲሡ መንግስት እንደዛ ነው። አሸባሪወችን ከውጭ ጠርቷል። አሸባሪወችን ፈቷል። ይህ ኢ ሕገ መንግስታዊ ነው።…>>
.
<<ዓብይ አዲስ አበባ ላይ ገዱ ባህር ዳር ላይ የቀን ጅብ የሚል ቃል ተጠቅመዋል። ይህ ፋሽዝም ነው። ….>>
<<ባህር ዳር ላይ ዓብይ ሙሴ ነው ነፃ አውጥቶናል ያለው እሱን ከእስር ስላስፈታው ሊሆን ይችላል (ብ/ጀነራል አሳምነው ጽጌን)። ይሄ ዓብይን ከሠው በላይ መስቀል የፋሽዝም አጀማመር ነው። ደርግም እንደዚህ ነው የጀመረው … ሠውየው ጀግናው እየተባለ ነው ቀይ ሽብር የተጀመረው።…ጭራሽ ወያኔ የለፋበትን የሶማሌ ነዳጅ “ነዳጅን የደፈረ መሪ” ብለው ባህርዳር ላይ አይቻለሁ፤ ያስቃል።…>>
.
<<የአሁኖቹ አመራሮች የ97ቱ ጋዜጦችና መፅሔቶች ውጤቶች ናቸው።…ኦህዴድና ብአዴን ህወሀትን ለማጥፋት ነው አንድ የሆኑት እንጂ በኋላ ላይ ይፋጃሉ። ዓላማቸው ትግራይን ከሠሜን በሻቢያ ከደቡብ በራሣቸው አጣብቀው ማንበርከክ ነው የፈለገው።>>
.
<<የትግራይ ህዝብ ግን እንደማይንበረከክ ሊያቁት ይገባል።
ህወሀትና የትግራይ ህዝብ የተዋሀዱት በኬሚስትሪ ውህደት ነው። ህወሀት ያልሆነ ትገሬ የለም። ሁሉም ትገረዋይ ህወሀት ነው። >>
.
<<ዓብይ ግን እኛን ለማዳከም ፓርላማ ገብቶ “ህወሀትና የትግራይ ህዝብ ይለያያሉ” አለ። ይህ ትልቅ ስህተት ነው።
ገዱና ኢሣያስ አንድ ናቸው። …>>
.
<<በአሁኑ ሰአት የጠባቡ ሀይል ልገንጠል ይላል የትምክህቱ ሀይል አሀዳዊ መንግስት ይላል ከዛም ይባላሉ። አ.አ ላይ የኦነግ ባንድራን አየን …ባህርዳር ልሙጡን ይዘው ወጡ። ይሄ ደሞ እንደማይሥማሙ ያስታውቃል። መቼም አይስማሙም።>>
.
<<የዓብይ አካሄድ ፕሬዝደንታዊ አይነት ነው። ህግ ይጥሣል፣ እስረኛ ይፈታል፣ አሸባሪ ይጠራል፣ ባድመን ህግ ተላልፎ ያለ ቅድመ ሁኔታ ሰጥቷል… ። እየተመራን ያለነው በጁንታ ነው። የሆነ ቡድን ነው።>>
.
<<የአማራ ክልል ላይ ያለው የ27 ዓመት አፍራሽ ነገር ጠጣርና የደደረ ነው። የኦሮሞ ተቃውሞ ግን ስስ ነበር የእነሡን[የብዐዴን] ያክል አይደለም። ትልቅ ችግር አለባቸው። >>
.
<<…ትናንት የመከላከያ ሄሊኮፕተር ልሙጥ ባንድራ ይዛ ታይታለች። ያደረገው አካል በፍጥነት መያዝና እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል።>> (ሄሊኮፕተሯ የግለሠብ መሆኗን አላወቁም)
.
<<…ራያ ወልቃይት የሚባሉትን መጠየቅ ጦርነት በኛ ላይ እንደማወጅ ይቆጠራል። ልክ ሱዳኖች የኢትዮጵያን መሬት እንውሰድ እንደሚሉት።>>
.
<<በዚህ አካሄድ ከማንም ጋር የመኖር አካሄዳችን ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።>>
.
<<ኦህዴድና ብአዴን 4 ዓመት ወጣቱን ከአነሣሡ በኋላ አሁን ወደሚፈልጉት እየጠመዘዙት ነው። ዓብይም ትልልቅ ጥያቄወችን ላለመመለስ ወጣቱን እየተጠቀሙበት ነው። …..>>
.
ትህነግ እንደዚህ ይደነብራል ብየ ዓልሜም አስቤም አላውቅም። የቀድሞውን ጠሚ መለስን ቃል ልጠቀምና እንደዚህ ከሚያለቅሱ ወንድ ከሆኑ ለምን በሊማሊሞ አያቋርጡም?
Filed in: Amharic