>

የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ  ነገር....... (አቻምየለህ ታምሩ)

የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ  ነገር. . … [ክፍል ፩]  
አቻምየለህ ታምሩ
ከሰሞኑ በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ላይ የተደረተውን የወያኔ አርማ በሕዝቡ ተቀዶ መውጣትን  አስመልክቶ የተሳሳተ አስተያየት ተሰጥቶ አንብቤያለሁ።
ስህተቱ ወያኔ የጨመረውን አርማ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አካል አድርጎ በመቁጠሩ ወይንም ሰንደቅ አላማና አርማን መለየት ባለመቻሉ ነው። የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሐል ቢጫ ከታች ቀይ ሆኖ  ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም የተቀመጡ እንደሆነ የወያኔ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ሶስት  እንኳ ሳይቀር ያትታል።
በሌላ አነጋገር ዮናታን  ወያኔ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ሶስት መሰረትም እንኳ ብንሄድ  የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ  ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሐል ቢጫ ከታች ቀይ ሆኖ  ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም የተቀመጡበት ነው። የወያኔ ሕገ መንግሥት ያደረገው ነገር ቢኖር ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሐል ቢጫ ከታች ቀይ ሆኖ  ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም የተቀመጡ ቀለሞች ባሉት  የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ላይ አርማ ጨመረበት። ልብ በሉ አርማው በሰንደቅ አላማው ላይ የተጨመረ እንጂ የሰንደቅ አላማው አካል እንዳልሆነ የወያኔ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ሶስት ራሱ  ያስረዳል።
ስለዚህ የወያኔ አርማ ተቀዶ ቢወጣ በወያኔ ሕገ መንግሥት መሰረት  እንኳ ብንሄድ  የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በተባለው ላይ የሚደርስ አንዳች የክብር መጓደል የለም። ምክንያቱም የወያኔ ሕገ መንግሥት ራሱ  የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሐል ቢጫ ከታች ቀይ ሆኖ  ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም የተቀመጡ  ይላል እንጂ  አርማውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አካል አያደርገውምና።
ለዚህም ነው ወያኔ ራሱ  የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሐል ቢጫ ከታች ቀይ ሆኖ  ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም የተቀመጡ ቀለማት ያሉት  እንደሆነ እየነገረን  ዮናታን  ወያኔ  በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ  ላይ  የጨመረው  አርማ  ተቀዶ መውጣቱ  disfiguring  the other [flag] that many still belive  የሚያስብልና የሌሎች መብት እንደተነካ ተደርጎ ሊቀርብ የሚችል ነገር የለውምና  አንሳሳት።
በጣም የሚገርመው ነገር ግን ወያኔ ራሱ  የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሐል ቢጫ ከታች ቀይ ሆኖ  ሦስቱም ቀለማት እኩል ሆነው በአግድም የተቀመጡ እንደሆነ በጻፈው ሕገ መንግሥት  ካስቀመጠ በኋላ  በሰንደቅ አላማው ላይ ያስቀመጠውን  አርማ ትርጉም  ሲዘረዝር «የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች እና ሃይማኖቶች በእኩልነት የሚያንጸባርቅ ነው» እያለ  እየነገረን በወያኔ ዘመን  «እኩልነት የለም» ብሎ  የሚታገለው ዮናታን ወያኔ እኩልነት እንዳመጣ ለማሳየት በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ላይ የደረተው አርማ ለምን ተቀዶ ወጣ ብሎ መከራከሩና የቀደዱት የሌሎችን መብት እንደጣሱ አድርጎ  ለማሳጣት መሞከሩ ነው።
ወያኔ እኩልነት እንዳመጣ  ለማሳየት በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ላይ ያስቀመጠውን አርማ ጭምር እያውለበለቡ በሌላ በኩል ደግሞ  እኩልነት የለም ብሎ መታገል እንዴት አብረው  ይሄዳሉ? እኩልነት የለም ብሎ መቃወም እንዴት የሌላውን መብት መጋፋት ሆናል?  ወያኔዎች በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ላይ የጨመሩትን አርማ ጭምር ቢያውለበልቡ ከኛ በላይ እኩል ስለሆኑ ቢያምኑበት ተገቢ ሊሆን ይችላል። እኩልነት የለም ብሎ የሚታገል ግን ወያኔ እኩልነት እንዳመጣ ለማሳየት በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ላይ  የጨመረውን አርማ  ጭምር እያውለበለቡ «እኩልነት የለም!» ማለቱ ነገር አለሙ ካልተምታታብ ነገር አብረው ሊሄዱ የሚችሉ ነገሮች አይደሉም!
የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ነገር… [ክፍል ፪]  
«ሞአ አንበሳ» ያለበት  ሰንደቅ አላማ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ በግዳጅ የሚያውለበልበው አልነበረም። ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያውለበልበት የነበራው የሕዝብ ሰንደቅ አላማ  ልሙጡ አረንጓዴ፣ ቡጫ፣ ቀይ ሰንደቅ አላማን ነው። አንዳንዶች አንበሳውን  ከሰንደቅ አላማው ላይ አውርዶ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ልሙጥ ያደረገው ደርግ ነው ይላሉ። ይህ የተሳሳተ ነው።  እንዴውም  ደርግ እንኳን አንበሳው ቀርቶ     መንግሥት ሲሆን ለመጀመሪያ  ይጠቀምበት የነበረው አርማው አንበሳ ነበር።
ምንም እንኳ  የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት  ሞአ አንበሳ ያለበትን ሰንደቅ አላማ  ባንዳንድ የመንግሥት መሥሪያቤዎች  ቢሰቅልም  ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ  ጨምሮ  በውጭ አገርም ሆነ በአገር ውስጥ  ያውለበልቡት የነበረው ልሙጡን አረንጓዴ ቢጫ፣ ቀይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ አላማ ነው። በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በተጻፈ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ሕገ መንግሥት ላይ የተደነገገው  የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማም  ልሙጡ  አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀዩ እንጂ ሞአ አንበሳ ያለበት አይደለም።  ከወያኔ ዘመን በፊት በመቼም ዘመን  ቢሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን እንዳያውለበልብ  አልተከለከለም።  ከፍ ሲል እንዳልሁት  በንጉሠ ነገሥት መንግሥቱም ቢሆን በሕግ  የሚታወቀው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ልሙጡ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይን እንጂ አንዳንዶች እንደሚሉት የሞአ አንበሳ አርማ  ያለበት አይደለም። ለዚህ ማስረጃ ለሚፈልግ  እነሆ!
Filed in: Amharic