የባህርዳር ሰልፍ በኔ በአንድ ትግራዋይ እይታ!
(ናትናኤል አስመላሽ)
እኔ እንደ ትግራዋይ ግን፣ ሰልፉ ባየሁ ቁጥር የትግራይ ህዝብ ለዚህ አለመታደሉ ውስጤ ያለቅሳል”የኣሮጌ ዘመን ቁማርተኞች”(ህውሓቶች) የትግራይ ህዝብ ከሌላው ህዝብ ነጥለው፣ ለማጣላት፣ ለማዋጋት የሚያደርጉትን ጉዞ ሳይ ከዚህ ቦሃላም የትግራይ ህዝብ ለኣሮጌ ዘመን ቁማርተኞች ብሎ ገና ብዙ ዕዳ እንደሚከፍል ይታየኛል። ለኣሮጌ ዘመን ቁማርተኞች ስልጣን ላይ ለመቆየት ተብሎ የትግራይ ተወላጆች በወሎ በባቲ የማይገባ መስዋእትነት እየከፈሉ ይገኛሉ። የኣሮጌ ዘመን ቁማርተኞች የትግራይ ህዝብ ጸረ ኢትዮጲያ ህዝብ ለማሰለፍ በአማራ ክልል፣ በደቡብ ክልል ገንዘባቸውን አፍስሰው ትናንት ደደቢት በነበሩበት ጊዜ የቀለባቸውን ህዝብ እንዲገደል፣ ንብረቱ እንዲወድም እና ሌላውን ቢሄር እንዲጠላ እያደረጉ ነው!
ህውሓቶች ቂመኞች! እባቦች! ከመሆናቸውም ጭምር፣ልባቸው ለፍቅር ሳይሆን ለቂም ብቻ የተፈጠረ ስለሆነ፣ ገዱ ለወ/ሮ እማዋይሽ፣ ጀነራል አሳምነው ሲያቅፍ፣የኣሮጌ ዘመን ቁማርተኞች ለአቶ ገብሩ አስራት፣ ለወ/ሮ አረጋሽ አዳነ፣ ለዶ/ር አረጋዊ በርሀ የፍቅር፣ የይቅርታ ልባቸውን እስካሁንዋ ሳአት ድረስ ክፍት አይደለም። ወ/ሮ እማዋይሽ ከገዱ አንዳርጋቸው ጎን ተቀምጠው ሳይ፣ የዓረናዋ የሽብርተኛ እስረኛ አደይ አልጋነሽ እና የአስራሰባት አመት ፍርደኛ (እስረኛ) ወጣት ፍስሃጽዮን ተኽለሃይማኖት ከደብረጽዮን፣ከስብሓት ጎን አለማየቴ አዝናለሁኝ ውስጤም ያለቅሳል። ጀነራል አሳምነው ከም/ል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ጎን ሳይ፣ እድሜ ልክ የተፈረደበትን የዓረና ትግራይ እስረኛ(ፍርደኛ) አቶ ገብረእግዝአብሄር ታደሰ ከስዩም መስፍን ጎን አለማየቴ አዝናለሁኝ አለቅሳለሁኝም።.
በፎቶ የምትመለከቷቸው ፣ የዓረና ትግራይ አባል በመሆናቸው ብቻ; የእድሜ ልክ ፍርደኛ (እስረኛ) አቶ ገብርእግዝአብሄር ታደሰ እና የአስራሰባት አመት ፍርደኛ (እስረኛ) ወጣት ፍስሃጽዮን ተኽለሃይማኖት።