>

ሕገ-መንግስቱን የመሻሻያ አዋጅ ሮድ ማፕ ወጣ !!! (ዮናታን ከተማ)

ሕገ-መንግስቱን የመሻሻያ አዋጅ ሮድ ማፕ ወጣ !!!
ዮናታን ከተማ
– ከ105 የሕገ መንግስቱ አንቀጾች 77ቱ አንቀጾች መሻሻል አያስፈልጋቸውም። እንዳለ ይቀጥላሉ።
 – 25 አንቀጾች በከፊል ወይም እንዳለ የተሻሻሉ ሲሆን፣
– 3 አንቀጾች ( አንቀጽ 82፣ 83 እና 84) ተሰረዝዋል። ይህ አማራጭ የሕገ መንስግቱ ሰነድ በዋናነት ማሻሻያ ያደረገባቸው ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡
– የኢትዮጵያ ባለቤትነትን ለ”ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች” ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሰጣል።
“ብሄር ብሄረሰብና ሕዝብ” በሚለው ምትክ ብሄረሰብ የሚለዉን አባባል ተጠቅሟል።
የብሄረሰቦችን ሆነ ማናቸዉንም የቡድን መብቶች ፣ የግለሰብ መብቶችን ባልደፈረ መልኩ ሙሉ ለሙሉ ያረጋግጣል።
ከግለሰብ መብቶች ጋር የሚጋጩ ከሆነ ቅድሚያ ለግለሰብ መብት ይሰጣል።“ክልል” የሚለው ቃል ክፍለ ሃገር በሚለው ይተካል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አመራረጥና የሥራ ሃላፊነት በተሻለ መልኩ ተለዉጧል። ሕገ መንግስቱን የመተርጎም ሃላፊነት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ወደ ዳኞች ተወስዷል።ፕሬዘዳንቱ ተጨማሪ ስልጣኖች እንዲያገኙ ተደርጓል።
መሬት መሸጥና መለወጥ እንደሚያስፈልግ የሚደነግጉ አንቀጾች ተቀምጠዋል።ፌዴራሊዝም ስልጣን ከማእከላዊ መንግስት ወደ ህዝብ የሚያወርድና ለአገሪቷ ጠቃሚነቱን ታሳቢ በማረግ በኢትዮጵያ የፌዴራል ስርዓት ይቀጥላል። ሆኖም አሁን ያለውን “ፌዴራል” የሚባለው ግን ፌዴራል ያልሆነ አወቃቀር በመጠኑም ሆነ ስር ነቀል በሆነ መልኩ መሻሻያ የሚያደርጉ አምስት የፌዴራል አወቃቀር አማራጮች ቀርበዋል።በአማራጭ 1 ፣ ሶስቱ ትላልቅ ክልሎች (አማራ፣ ኦሮሚያና ደቡብ) ከቋንቋ በተጨማሪ ሌሎች መስፈርቶችን በማካተት፣ አነስ ወዳሉ በርካታ ክፍለ ሃገሮች ተሸንሽነዋል። የሃረሪ ክልል፣ የድሬደዋን አስተዳደር፣ ጅቡቲን የሚያዋስነው የሶማሌ ክልልን ጨምሮ ሰፋ ያለች ክፍለ ሃገር ትሆናለች። የቤኔሻንጉል ክልል አይኖርም። ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ወደ በጌምድር ክፍለ ሃገር ይጠቃለላሉ።
በአማራጭ 2  በአጼ ሃይለስላሴ ጊዜና በኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም አስተዳደር መጀመሪያ አመታት ወቅት የነበሩ ክፍለ ሃገራትን ያካተተ ፌዴራል አወቃቀር ነው።
በአማራጭ 3  በክሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም አስተዳደር ወቅት የነበሩትን የአስተዳደር መዋቅሮች እንዳለ ወስዶ፣ የኦጋዴን ክልል ከድሬደዋ/ሽንሌ ጋር ያገናኘዋል።
በአማራጭ 4  አገሪቷን ለአምስት ተመጣጣኝ ክፍለ ሃገራት የሸነሸነ የፌዴራል አወቃቀር ነው።
በአማራጭ 5 ከሞላ ጎደል ለአዲስ አበባ ለድሬዳዋ ከተሞች ዘላቂ መፍትሄ በሰጠ መልኩ አሁን ያለው የፌዴራል አወቃቀር ያስቀጥላል። የወልቃይት ጥያቄ በትግራይ አማርኛም የስራ ቋንቋ በማድረግና ትግራይ አሁን ባለው አሰራር የተጋሩዎች ብቻ ሳትሆን የሁሉም ዜጎች የሆነች ክፍለ ሃገር ከተደረገች ሊፈታ ይችላል በሚል ታሳቢ ያደረገ አማራጭ ነው።
በአምስቱም አማራጮች አማርኛ የሁሉም ክፍለሃገራት የስራ ቋንቋ ሲሆን፣ በሁሉም ክፍለሃገራት ዜጎች የመኖር፣ የመስራት፣ የመነገድ፣ የመመረጥ፣ የመመረጥ፣ የመግባት፣የመዉጣት . .መብታቸውን ያለምንም መሸራረፍ የሚያስከበር ነው።ይህ አማራጭ ሰነድ የተዘጋጀው ኢትዮጵያዉያን በዚህ ጉዳይ እንዲነጋገሩበት ሲሆን፣ ገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ሆነ ተቃዋሚዎች ጠቃሚ መስሎ ካገኙትም ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
መግቢያ
በሕግ መንግስቱ መግቢያው ላይ የተቀመጠው በሙሉ በሚከተለው ተለዉጧል፡
“ኢትዮጵያ ሀገራችን የየራሳቸው አኩሪ ባሕል ያላችው፣ የየራሳቸው መልክዓ ምድር አሰፋፈር የነበራቸውና ያላቸው፣
ብሄረሰቦች በተለያዩ መስኮችና የግንኙነት ደረጃዎች
ተሳስረው አብረው የኖሩባትና የሚኖሩባት ሀገር በመሆንዋ፤ የብሄረሰቦቿ ልዩነት ዉበቷ ፣ትስስራቸውና አንድነታንቸው
ደግሞ ጥንካሬው ሆኖ፣ በተለያዩ ዘመናት የተቃጣባትን የውጭ ወራር መክታ የቆየች አገር ናት።
ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች መጪው የጋራ እድላችውን
በመመስረት ፣ በታሪካችን የነበሩ ድክመቶችን በማረም፣ የጋራ ጥቅማቸዉን በማሳደግ ፣ ሁሉም ዜጎች በቋንቋ፣ በባህል በሃይማኖት በጾታ ፣ በእድሜና በመደብ ልዩነት ሳይደረግባቸው በሰላምና በፍቅፍ፣ በብልጽግና የሚኖሩባት አንዲት ዴሞክራሲያዊት አገር እንድትሆን የሚያረጋግጥ ሕግ
መንግስት ነው።”
አንቀጽ 3
የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ
ንዑስ አንቀጽ 2
«ከሰንደቅ ዓላማዉ ላይ የሚቀመጠው ብሄራዊ ዓርማ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች፣ ሕዝቦች እና ኃይማኖቶች በእኩልነትና በአንድነት ለመኖር ያላቸውን ተስፋ የሚያንጸባርቅ
ይሆናል።» የሚለው ይሰረዛል።
ሰንደቅ ዓላማዉ አርማ አይኖረዉም።
አንቀጽ 4
የኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር
«የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር የሕገ መንግስቱን
ዓላማዎችና የኢትዮጵያን ሕዝቦች በዴሞክራሲ ሥርዓት አብረው ለመኖር ያላቸውን እምነት፣ እንዲሁም የወደፊት የጋራ ዕድላቸውን የሚያንጸባርቅ ሆኖ በሕግ ይወሰናል።»
የሚለው «የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር የሕገ መንግስቱን ዓላማዎችና ዜጎች በዴሞክራሲ ሥርዓት አብረው ለመኖር ያላቸውን እምነት፣ እንዲሁም የወደፊት የጋራ ዕድላቸውን የሚያንጸባርቅ ሆኖ በሕግ ይወሰናል።» በሚለው ይተካል።
አንቀጽ 5
ስለ ቋንቋ
ንዑስ አንቀጽ 2
«አማርኛ የፌዴራሉ መንግስት የሥራ ቋንቋ ይሆናል»
የሚለው «አማርኛ የፌዴራል መንግስትና የክልሎች ሁሉ የስራ ቋንቋ ይሆናል” በሚለው ይተካል።
ንዑስ አንቀጽ 3
«የፌዴሬሽኑ አባላት የየራሳቸውን የሥራ ቋንቋ በሕግ
ይወስናሉ» የሚለው «የፌዴሬሽኑ አባላት ከአማርኛ
በተጨማሪ የየራሳቸው ሌላ የሥራ ቋንቋ በሕግ ሊደነግጉ ይችላሉ። በሚለው ይቀየራል።
አንቀጽ 8
የሕዝቡ ሉዓላዊነት
ንዑስ አንቀጽ 8
«የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ስልጣን ባለቤቶች ናቸው።» የሚለው «የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤት ነው» በሚለው ይተካል።
አንቀጽ 33
የዜግነት መብቶች
ንዑስ አንቀጽ 3
«ማንኛዉም ዜጋ ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን የመለወጥ መብት አለው» የሚለው «ማንም ዜጋ ከኢትዮጵያዊነት ዜግነት በተጨማሪ የሌሎች አገሮች ድርብ ዜግነት መያዝ ይችላል»
በሚል ይሻሻላል።
አንቀጽ 34
የጋብቻ፣ የግልና የቤተሰብ መብቶች
«ጋብቻ በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት መካከል ብቻ የሚደረግ ይሆናል» የሚል አምስተኛ ንዑስ አንቀጽ ይጨመራል።
አንቀጽ 39
‹የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች ሕዝቦች መብት» የሚለው
“የብሄረሰብ መብት” በሚለው ይተካል።
«ማንኛዉም የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን እስከመገንጠል ያለው መብቱ በማናቸውም መልኩ ያለ ገደብ የተጠበቀ ነው» የሚለው ንዑስ አንቀጽ 1 ይሰረዛል።
«የብሔር፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የራስን እድል በራስ
የመወሰን እስከ መገንጠል መብት ከሥራ ላይ የሚዉለው» ብሎ የሚጀመረው ንኡስ አንቀጽ 4 ይሰረዛል።
« የብሄረሰብ መብቶች ከግለሰብ መብቶች ጋር የሚጋጩ ከሆነ ቅድሚያ ለግለሰብ መብት ይሰጣል» የሚል አንቀጽ ይጨመራል።
Filed in: Amharic