>

"ይሄ ክስተት እጅግ በጣም ታሪካዊ ነው!!!" (ቬሮኒካ መላኩ)

“ይሄ ክስተት እጅግ በጣም ታሪካዊ ነው!!!”
ቬሮኒካ መላኩ
 መለስ ዜናዊ ራሱ እንደተናገረው ከ100 ጊዜ በላይ ለመገናኘትና ለመነጋገር ቢሞክር አልተሳካለትም።  ከኢሳያስ ጋር መገናኘት እንደናፈቀው ለዘላለሙ አሸልቧል።
የታመመ ሰሞን እንኳን ዶክተሮቹ በህይወት ብዙ ቀናት የመቆየት እድል እንደሌለው ሲነግሩት በህይወት ለመቆየት የነበረውን አጭር ጊዜ በመጥቀስ በሳኡዲ በኩል ለኢሳያስ የእንገናኝ መልእክት በከፍተኛ ሚስጥር ቢልክም አልተሳካለትም።
ሀይለማሪያም ደሳለኝም  ገና ወደ ስልጣን ከመምጣቱ ለአልጄዚራዋ  ጋዜጠኛ ጃኔ ዱተን… “If you ask me ‘Do you want to go to Asmara [the Eritrean capital] and sit down and negotiate with Isaias Afewerki right now ?’, then I will say ‘yes ”  ” አሁን ኢሳያስ እንነጋገር ብሎ ቢጠይቀኝ አሁኑኑ በርሬ አስመራ እሄዳለሁ ብሎ ቢለምንም ሳይሳካለት ከስልጣኑ ወርዷል።
ጠ/ሚ አቢይ አህመድ መለስ ዜናዊ ለ 10 አመታት ጠይቆ ያልተሳካለትን ። ሀይለማሪያም ደሳለኝ ለ5 አመታት ለምኖ የተዘጋበትን በር  በ80 ቀናት ብቻ አስከፍቶታል ። ጠ/ሚ አቢይ አህመድ ይሄን ስኬት ለማግኘት መለስ ዜናዊና ሀይለማሪያም ከገቡት ቃል ትርፍ ቃል ሳይገባ ተሳክቶለታል ። ይሄ የስኬታማ መሪ አንድ መመዘኛ ነው።
 አሁን መለስ ዜናዊ አልጄርስ ላይ በፈረመው መሰረት ። ሄግ ኔዘርላንድ  የሚገኘው አለም አቀፍ የግልግል ፍርድቤት በወሰነው መሰረት አሁን ባድሜ መሄዷ ተረጋግጧል ። ባድሜ የራሳችሁ ናትና ውሰዷት።
በዚች ታሪካዊ ቀን ግን  ዶ/ር አቢይ አህመድ የኤርትራ ልኡካን ቡድንን እንድጠይቁ አንድ ጥያቄ እወረውራለሁኝ ይሄውም በኤርትራዋ የድንበር ከተማ በሆነችው ባድመ እንብርት ላይ ፍትሃዊ ባልሆነ ጦርነት ተማግደው ህይወታቸው ላለፈ ጀግና ኢትዮጵያውያን ሀውልት ይሰራላቸው ዘንድ እንድነጋገሩ ነው።
በተረፈ ዶ/ር አቢይ አህመድ ዛሬም እንደገና ላስመዘገበው  ድፕሎማሲያዊ ድል እንኳን ደስ አለህ እላለሁኝ።
Filed in: Amharic