>

ትግራይ እንዳትደመር ማስደንበር !! (እንግዳ ታደሰ - ኖርዌይ)

ትግራይ እንዳትደመር ማስደንበር !!

እንግዳ ታደሰ – ኖርዌይ

      እስራኤሎች ሲተርቱ እንዲህ ይላሉ፡፡ Beware of the person who gives you advice according to his own interests.ቦታ ለውጠው የመጡት አዳዳዲስ አማካሪዎች ሲያማክሩ ቢውሉ ያው የለመደባቸውን ነው ፡፡ ጠቅላይ ሚንስቴር አብይ አህመድ መገኛቸውና እናት ድርጅታቸው ኢህአዴግ ስለሆነ ሌላ ባዕድ አማካሪ ከውጭ ሊመድቡ የኢሃዴግ ውስጠ ደንብ አይፈቅድላቸውም ይሆናል አናውቅም፡፡ የቀነሷቸውን የቀድሞ ባለስልጣኖች እንደገና በአማካሪነት መድበዋል ፡፡ አጼ ምኒልክ ንጉስ ጦናን በጦርነት ካሸነፉ በኋላ ለመንግሥታቸው እንደሚገብሩ ሲያረጋግጡ እዛው ግዛታቸውን እንዲያስተዳድሩ ነው ትትውላቸው የወጡት ፡፡ የጅማውን አባ ጅፋርንም እንደዚያው ፡፡ የዚያ አይነት ስልት ዶክተር አቢይ አህመድ ተክትለው እንደሆን አናውቅም ፡፡ ተረቴ ከመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ በዛ መሰለኝ፡፡ ከአረቦች ብሂል ደግሞ አንድ ላክል  It’s better to have a thousand enemies outside of the tent than one inside the tent.  የውጭውን ጠላት በቅዳሜው የሚልዮኖች የድጋፍ ሰልፍ ላይ ፈንጂ አፈነዱ በተባሉ ግለሰቦች ላይ ህዝቡ የወሰደው ርምጃ ለተረቱ ምስክር ነው ፡፡ አስቸጋሪው የውስጡ ነው ፡፡ ከውጭው አንድ ሺህ ጠላት ፣ ድንኳኑ ውስጥ ያለው አንድ ጠላት ነው አደገኛው ፡፡

በቱርኩ መሪ ኤርዶጋን ላይ የተወሰደው መፈንቅለ መንግሥት እና በዶክተር አብይ ላይ የተሸረበው ሴራ ባንዳንድ ገጹ ተመሳሳይነት አያጣም ፡፡ ኤርዶጋን በዕረፍት ማርማሪስ በተባለ የመዘናኛ የባህር ዳርቻ ላይ በመዝናናት ላይ በነበሩበት ወቅት ነበር የተጠነሰሰላቸው ፡፡ በወቅቱ ስለ መፈንቅሉ መንግሥት ሲያወሱ  he made his getaway to a plane bound for Istanbul only minutes before the rebels entered the hotel. “Had I stayed 10, 15 additional minutes, I would have been killed or I would have been taken,” Mr Erdogan said. የደቂቃዎች ልዩነት ነው ኤርዶጋንን ያዳናቸው ፡፡ ትንሽ ቢቆዩ ኖሮ የዛሬው እጀ ብረቱ ኤርዶጋን የሉም ነበር ፡፡

ከግልበጣው ከዳኑ በኋላ ኤርዶጋን ከ85 በላይ ጄኔራሎችንና አድሚራሎችን ዘብጥያ አውርደዋል ፡፡ ከሃያ ሺህ በላይ በመንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ አገልጋይ የነበሩ ሲቪሎችን ከሥራ አባረዋል ፡፡ አረቦቹ እንደሚሉት ከውጭው አንድ ሺህ ጯሂ ጠላት ድንኳን ውስጥ ያለውን አንድ የጠላት ሰንኮፍ መንቀሉ ነው መንግሥት የሚያረጋው ፡፡ ኤርዶጋን ከመፈንቅሉ መንግስት ከዳኑ በኋላ ደጋፊዎቻቸውን ጠርተው አደባባይ ውጡና የኔ እንደሆናችሁ ለጦር ኃይሉ አሳዩት አሉ ፡፡ ህዝብ ከወታደራዊ አገዛዝ ለመዳን ሲል ፣ የኤርዶጋን ወዳጅም ሆነ ተቃዋሚ አደባባዩን አጥለቀለቅው ፡፡ ወታደሩም ሊመጣ የሚችለውን አደጋ በመረዳት ፍሬን ያዘ ፡፡

ዶክተር አብይ ደግሞ እርሳቸው ሰልፍ ሳይጠሩ ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ያልታየ ህዝብ በራሱ አነሳሽነት በጠራው ሰልፍ ታዳሚ ሆነው እንዲገኙ ተጋበዙ ፡፡ ከሶስት ሚልዮን ህዝብ በላይ ተገኝቶ አከበራቸው ፡፡ ከኤርዶጋን የሚለዩት እዚያ ላይ ነው ፡፡ ኤርዶጋን ህዝቡን ሰልፍ ጠራ አዳኑት ፡፡ አብይ ግን ህዝብ ጠራቸው አከበራቸው ፡፡ ያን ዕለት በዶክተር አብይ ላይ ጭረት ቢደርስ ሊከተል የሚችለውን አደጋ ህወሃቶች አልተረዱትም ፡፡ ቢረዱትም ከነሱ ስልጣን በላይ የትግራይ ህዝብ ቢያልቅ ደንታቸውም አልነበረም ፡፡ ሁሌም የትግራይ ህዝብና ህወሃት አንድ ነው እያሉ እንደሚያላዝኑበት የጭዳ ዶሮ ሊያደርጉት ሲሉ አልሰቀጠጣቸውም ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ በመሆኑ የቀን ጅቦቹን ከትግራይ ህዝብ ስለለየ በዚያን ዕለት በአንድ ትግራዋይ ህይወትም ሆነ ንብረት ላይ ጥቃት አልተፈጸመም ፡፡ የፌስ ቡክ ቅጥረኞቻቸው ገና ፖሊስ አጣርቶ የፈንጅውን አይነት ሳይናገር እነርሱ የቦንቡን የጾታ እና ሳይዝ ቁጥር ሳይቀር ቀድመው በገጾቻቸው ለጠፉ ፣ ቆየት ብለውም አነሱት ፡፡

የህወሃትን መንግሥት እቅድና ተንኮል ፣ ምን ሊሰሩ እንዳሰቡ ጭምር ለማወቅ ፣ አይጋ ድረ ገጽ ላይና ትግራይ ኦን ላይን በተባሉ ድረ ገጾች በግለሰቦች ስም የሚጻፉ ጽሁፎችን ማንበቡ ይጠቅማል፡፡ ጥላቻቸውን ፣ ትዕቢታቸውን ፣ በቀጣይ ሊሰሩ ያሰቡትን ድርጊት ሁሉ ከነአቅዳቸው ማረጋገጥ ይቻላል ፡፡ |« እውን ኢህሃዴግ አለ ወይ » በሚል ርዕስ ሰኔ 12 ቀን 2010 በአሉላ ዮሃንስ የተጻፈውን ጽሁፍ ከማስፈንጠሪያው ላይ ታገኙታላችሁ ፡፡ ሲጀመር ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ስልጣን የመጡበት አካሄድ መሠረታዊ ስህተትና የህግ ጥሰት እንዳለበት እየታወቀ መመረጣቸው አጠቃላይ የኢህአዴግን ውድቀት የሚያሳይ ነው ይለናል ፡፡ http://www.tigraionline.com/is-eprdf-alive.pdf

አዛውንቶቹ የህወሃት ተርኪስ ባቡሮች ማሰቢያቸው ዝጎ የትግራይን ህዝብ ከሌላው ወገኑ ነጥለው እንዳይደመር በማስደንበር ላይ ሌት ተቀን ትግራይ ላይ ከትመው እያሴሩ እንደሆነ እየተነገረ ነው ፡፡   በጃጀ አስተሳሰብ አዲሱን የትግራይ ትውልድ የጦስ ዶሮ ከማድረግ አይመለሱም ፡፡ አልሰማ ብለው ነው እንጂ በአንድ ወቅት የባለ ራዕዩ መሪያቸው ልጅ ሰምሃል መለስ እነ አቦይ ስብሃትን ፊት ለፊት አዳራሽ ውስጥ ወደሱ እየጠቆመች ለኛ ለወጣቶቹ ልቀቁልን እስከማለት ነግራው ነበር ፡፡

ያረጡት ህወሃቶች አንዴ ኪዊ ቀለም ሽበታቸውን ተቀብተው ቢመጡ ፣ ወይ ጆንትራ ቮልታ ቁርጥ ጸጉራቸውን ተሸልተው ቢንጎማለሉ የአካል ጅማቶቻቸው አልታዘዝ ካላቸው ፣ አንጎላቸው መሽናታቸውንና መጸዳዳታቸውን መንገር ካቆመ ከርሞባቸዋል ፡፡ በፖለቲካ ሽሙጥ ወደ ሜቄዶንያ ማገገሚያ ላኩልን የሚሉ ድምጾች በርግጥ ከአንዳንድ ትግራውያን ይሰማል ፡፡ በውጭ አገር የትግራይ ሚዲያ ኔት ዎርክ ባለቤት ፣ ናትናኤል አስመላሽ እባክህ ዶክተር አብይ አባይ ጸሃዬን ፣ ስዩም መስፍንን ፣ አቦይ ስብሃትን ብታስርልን ቀሪዎቹን የትግራይ ህዝብ ያስራቸዋል ሲል ተማጽኗል፡፡ ዶክተር አብይ በአስቸኳይ የድንኳኖቹን ጠላቶች በፍጥነት ርምጃ ካልወሰዱባቸው አደጋው ሰፊ ነው ፡፡ትግራይ ሳትደመር እንደደነበረች ከወገኖቿ እየተናቆረች ልትቀር ነው ፡፡

Filed in: Amharic