>

የሰኔው ሰላማዊ ሰልፍ (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም)

የሰኔው ሰላማዊ ሰልፍ

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም
እግዚአብሔር የኢትዮጵያን ሕዝብ ስቃይና መከራ አይቶ ዓቢይ አህመድን ፈጠረውና ወደኢትዮጵያ ላከው፤ ስለዚህም እንደአንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ኑሮውን አደላድሎ በመኖር ፋንታ ከተሰየመበት ቀን ጀምሮ ሳያርፍ በየቦታው እየዞረ ፍቅርን ሲሰብክና እስረኞችን ሲያስፈታ ቆየ፤ ከዚያም በላይ ከጎረቤት አገሮች ጋርም በመወዳጀት እስረኞች ሁሉ እንዲፈቱ አደረገ፤ በቴሌቪዥንና በራድዮ ሕዘብ ነጻ አስተያየቱን እንዲገልጽ አደረገ፤ ከኤርትራ ጋር የእርቅ በር ከፈተ፤ ለግንቦት 7 እንዲሁ የእርቅ በር ከፈተ፤ የሕዝብን ኑሮ ለማሻሻል ውጥኖችን ነግሮናል፤ በየቀበሌውና በየፖሊስ ጣቢያው ንጹሓን የኢትዮጵያን ሕዝብ እያሰሩ ማሳቃየቱ እንዲቆም አድርጓል፤ በሦስት ወር ያህል ጊዜ ከዚህ በላይ እንዲሠራ ለመጠበቅ አንችልም፡፡
የፊታችን ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትርን ለመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል፤በሰልፉ የሚሳተፍ እያንዳንዱ ሰው በጎኑ ያለው  የሚያደርገውን ማየትና መቆጣጠር የሰልፉን ጤንነት ይሆናል፤ በሚያዝያው 30 1997 ቅንጅት የተጠቀመበት ዘዴ ነው፡፡
Filed in: Amharic