>

ህዝቡ ዛሬ ላይ አብይን ለመደገፍ ከበቂ በላይ ምክንያት አለው!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ጎንደር ላይ ከነገሱት ነገስታት አንዱ የነበረውን ዮሀንስ 1ኛን ህዝቡም የውጭ ፀሃፊዎችም  “ዮሀንስ ፃድቁ  ” በማለት ይጠሩት ነበር ። “ፃድቁ ዮሀንስ” በስልጣን ዘመኑ  ህዝቡ አቤቱታ ለማሰማት ወደ ቤተ መንግስት ሲሄድ የቤተመንግስት ጠባቂዎች አላስገባ እያሉ ስለከለከሉና ሲያጉላሉት በመመልከት መፍትሄ ይሆን ዘንድ ከቤተመንግስቱ ውጭ አደባባዩ ላይ ትልቅ ደወል እንድሰቀል አደረገ ። ከዚያ በኋላ ለንጉሱ የማቀርበው አቤቱታ አለኝ ያለ ማንኛውም ደሃ ሰው ደወሉን ብቻ መደወል በቂው ነበር።  ከዛማ በኋላ ህዝቡ በፍትህ መጓደል እና በበደል ሳይንገላታ ብዙ አመታት በሰላም እንደኖረ እነ ጄምስ ብሩስም እነተክለ ፃድቅ መኩሪያም ፅፈውልናል።
እዚህ ላይ ዶ/ር አቢይ አህመድን ከፃድቁ ዮሃንስ ጋር ለማወዳደር እየደፈርኩ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ ነገር ግን እውነት እውነት እላችዋለሁኝ  ዶ/ር  አቢይ አህመድ  ፌክ አይደለም ። አቢይ ጂኒዩን ነው። ስሙ ከለማ መገርሳ ጋር ብቅ ብቅ ማለት ከጀመረበት ከአመት በፊት ጀምሮ  ለመከታተል ሞክሪያለሁኝ በዚህም ኮንሲስተንት የሆነ ሰው እንደሆነ ፊል አደርጋለሁኝ።
ይሄን ሰው መደገፍ ህውሃት የምትባልን የህዝብ ጠላት ፣ የቶርቼር ስፔሻሊስት፣የመሬትና የተራራ ሌባ መደቆስ ማለት ነው። በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መምታት ነው ።  አቢይን ደግፈን ፣ወያኔን አዳክመን ፣ እኛም ጠንክረን የተዘረፈብንን ማንነት ፣ መሬት ፣የደሞክረሲ መብትና እና ቁሳዊ ሀብት ሁሉ ለማስመለስ ቀላል ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። ያ ስትራቴጅ ካልሰራም ፖለቲካ ነውና ወደሚያዋጣው ስልት ለመዞር  የፖለቲካ ሳይንስ ጌሙ ስለሚፈቅድልን ወደፊት የምንመለከተው ይሆናል።
ጠ/ሚ አቢይን አለመደገፍ መብት ነው ፣ በሁለት ወር ውስጥ ያሳየውንና  ያመጣውን  ለውጥ ማራከስ ግን ተገቢ ነው ብዬ አላምንም። ጉዳዩን ከግል ምልከታዬ ሰፋ አድርጌም ልየው ብል ህዝቡ ዛሬ ላይ አብይን ለመደገፍ ከበቂ በላይ ምክንያት አለው!!!
ግባችን አንድ ነው ። እናንተም በሚያዋጣችሁ ሂዱ ፣ እኛም ያዋጣል ብለን ካልኩሌት ባደረግነው ስትራቴጅና ታክቲክ እንድንሄድ ፍቀዱልን። እኔ በሄድኩበት መንገድ ሌላው ካልሄደ እያሉ ሲያሽሟጥጡና ሲያረክሱ መዋል ግን ረክሶና በዜሮ ተባዝቶ መቅረት ነው።
Filed in: Amharic