>

ጠ/ምሩ የተሳሳቱት ዛሬ ሳይሆን ጌታቸው አምባዬን የህግ አማካሪ ያደረጉ እለት ነው!!! (ውብሸት ሙላት)

ከትላንቱ ከዶ/ር ዐቢይ ንግግር ላይ መስተካከል ያለበት አንድ ነጥብ ብቻ አለ። ስለ ይቅርታ አሰጣጥና ውጤቱ የተናገሩት። እሳቸው ሲናገሩ ይቅርታ የሚሰጠው ጉዳያቸው ገና በክስ ሒደት ላይ ያለውን ነው።  በቂ ማስረጃ ከሌለ ቀድሞውንም ክስ አለመመሥረት ነው። በቂ ማስረጃ ሳይኖር መክሰስ ተገቢ አይደለም።
ይሁን እንጂ በቂ ማረስጃ ሳይኖር የተያዘ እና በምርመራ በተለይም የዋስትና መብት ተነፍጎት በእስር ላይ ያለን ሰው በሚመለከት ምርመራውን በማቋረጥ ከእስር እንዲለቀቅ በማድረግ ከእንደገና ማስረጃ ሲገኝ ምርመራውን መቀጠል መክሰስም ይልላል።
በቂ ማስረጃ ኖሮ ክስ ከተመሰረተ በኋላም በተለያዩ ምክንያቶች ለምሳሌ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ክስ ሊቋረጥ ይችላል። ክስ ማቋረጥ ግን ይቅርታ አይደለም። ዶክተር ዐቢይ ትላንትና በይቅርታ የተፈታ ሰው ማስረጃ ሲሟላ ድጋሜ ሊከሰስ ይችላል ያሉት ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ክሳቸው የተቋረጠውን (በቂ ማስረጃ እያለ ማለት ነው) በይቅርታ የተፈታውንም አይጨምርም።
ይቅርታ የሚሰጠው ለተፈረደበት ሰው ነው። የተፈረደበት ሰው ደግሞ ድጋሜ አይከሰስም። ምናልባት ይቅርታውን የሚያስነሱ ድርጊቶች ከፈጸመ ቀድሞ የተፈረደበትን እና ያልጨረሰውን ቅጣት መልሶ ያጠናቅቃል።
እንግዲህ ያው የዶክተር ዐቢይ የሕግ አማካሪ አቶ ጌታቸው አምባዬ ስለሆኑ እንጂ ይችን ቀላል ስህተት አትነካቸውም ነበር።
Filed in: Amharic