>

ህወሓቶች ንግሥናቸውን ጌትነታቸውን  ስላጡ  ተበሳጭተዋል፤ ሰልፍም ጠርተዋል!!! (እየሩስ ተስፋዬ)

ህወሓቶች ንግሥናቸውን ጌትነታቸውን  ስላጡ  ተበሳጭተዋል፤ ሰልፍም ጠርተዋል!!!

እየሩስ ተስፋዬ
ምክንያቱም በኢትዮጵያ ምድር ላይ እንደ ሮያል ፋሚሊ እራሳቸውን ቆጥረው የፈለጉትን በፈለጉት  ጊዜ ሲያገኙ ኖረዋል:: ትግርኛ ቁዋንቁዋ  የማንኛውም ነገር ቁልፍ መክፈቻ ሆኖ ለሩብ ምእተ ዓመት ገዝቶአል::  ህወሓት ባለ ሰማያዊ ደም ሆኖ ገራፊ: ገፋፊ  እና ዘራፊ ሆኖ ቆይቶአል:: በሙስና ጣሪያ ነክተዋል::  የኢትዮጵያን እልፍ አእላፍ  ዜጎችን ሕይወት ቀጥፈዋል:: አካል አጉድለዋል:: ዘር አመክነዋል:: አኮላሽተዋል::  ያልሰሩት  ግፍ የለም::
   በዚህም ለፍርድ ሳይቀርቡ ተሸልመው: ተመስግነው  ተሸኝተዋል:: ይህንን የኢትዮጵያ ሕዝብ ይቃወማል:: ዶር አቢይን ተጠያቂ የሚያደርገው ጉዳይ ነፍሰ ገዳዮችን ወደ ፍርድ ከማቅረብ ይልቅ መልካም አከልግሎት እንዳቀረቡ ተቆጥረው የጡረታ መብታቸውን አስከብሮ በመሸቱ ብሄራዊ ስህተት ብቻ ሳይሆን ብሄራዊ ጥፋት ነው::
ስለዚህ የወያኔዎችን  የንግሥና ጥያቄ  ለመቃወም  ብቻ ሳይሆን ለማክሸፍ ትግል ያስፈልጋል::  ግፈኞች:  ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ እንላለን::
ዋናው ጉዳይ   የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው  መሠረታዊ ነገር “ሥር ነቀል ለውጥ” ነው::
በተያያዝ:- 

‘ያፈጠጠው ተቃውሞና የፈጠነው ድጋፍ

የህወሓት ካድሬወች ዛሬ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እኔ በምኖርበት ቀበሌ(በሌሎች ቀበሌዎችም ላይ ቅስቀሳው አለ) እየዞሩ ነገ ዶክተር አብይን ለመቃወም የትግርኛ ተናጋሪዎችን ቤት ለቤት እየዞሩ ነገ ሰልፍ መውጣት አለብን ተደፍረናል አያለቀልን ነው ነገ የተቃውሞ ሰልፍ እንውጣ እያሉ ትግርኛ ተናጋሪዎችን እየወተወቱ ነው !!
በኔ እምነት በዚህ ሰአት የደጋፍም የተቃውሞም ሰልፍ ቅንጦት ነው የትህነግ ደጋፊዎች ሰልፍ የሚወጡት መግደል, ማሰር, መንጠቅ ,ማዘዝ ስላልቻሉ ነው፡፡
በተቃዋሚው በኩልም የሚያስፈልገው ስትራቴጂካዊ ድጋፍ እንጂ ዶክተር አብይ በሰልፍ ማድነቅና መደገፍ ሰአቱና ጊዜው አሁን አይመስለኝም፡፡
በዚህ ሰአት በጉራጌ ክልል እየሞቱ ላሉ በደቡብ ክልል በነ ሽፈራው ሽጉጤ በሚቀነባበረው ጭፍጨፋ ነው ልንጮህ ነው የሚገባው፡፡
Filed in: Amharic