>

በደቡብ ክልል ሁከትና ብጥብጥ ያስነሳው ህወሓት መሆኑን “Tigrayoline” አረጋገጠ

by Seyoum Teshome

Tigrayoline የሚባለው የህወሓቶች ድህረገፅ የካቲት 07/2010 ዓ.ም ላይ ኢትዮጱያ መንግስት የዜጎቹን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር ለቀጣይ ሦስት አመታት የሚቆይ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ማወጅ እንዳለበት የሚል ፅሁፍ አውጥቶ ስመለከት በዕለቱ የለየለት እብደት መስሎኝ ነበር። ምክንያቱም ከየካቲት 05 – 7/2010 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ እነ በቀለ ግርባ እና እስክንድር ነጋ የመሳሰሉት የፖለቲካ እስረኞች በመፈታታቸው ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ደስታውን እየገለፀ ነበር። ይህ ድህረ-ገፅ ግን በተጠቀሰው ዕለት በተለያዩ አከባቢዎች ከፍተኛ ሁከትና ብጥብጥ መከሰቱን በመጥቀስ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጅ እንዳለበት ሲወተውት ነበር። ከሦስት ቀን በኋላ የካቲት 09/2010 ዓ.ም የአስቸኳይ ግዜ ሲታወጅ ከድረገፁ ፀኃፊዎች ይልቅ የራሴን አዕምሮ ጤንነት ተጠራጠርኩ። ፍፁም እብደት የመሰለኝ ነገር እውነት ሆኖ ሳገኘው ለምን ራሴን አልጠራጠር?

“When the state of emergency was in place the country was becoming peaceful, then the government lifted the state of emergency prematurely and we are back to square one. If the government is serious about maintaining peace and security in Ethiopia, they should reinstate the state of emergency throughout the country for three years. Meanwhile they should work to address all the issues raised by citizens and implement the so called deep renewal ideas announced after the meeting.”

ከሦስት ወር በኋላ ሰሞኑን Tigrayoline ተመሳሳይ መረጃ ይዞ መጥቷል። ከአስር ቀናት በፊት ይህ ድረገፅ ከዚህ በኋላ በሀገሪቱ አመፅና አለመረጋጋት ከተቀሰቀሰ እንደ ከዚህ ቀደሙ ኦሮሚያና አማራ ውስጥ ብቻ ተወስኖ እንደማይቀርና መላ ሀገሪቱ በሁከትና ብጥብጥ ልትታመስ እንደምትችል ይገልፃል። በዚህ ምክንያት የምናውቃት ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ልትቀየር እንደምትችል ይጠቁማል። ለዚህ ዋናው ምክንያት የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ሥራና ተግባር አፍራሽና ሀገሪቱ ውስጥ ቅሬታ ስለፈጠረ እንደሆነ ድህረገፁ ይጠቅሳል።

“If the unrest restarts again it would not be confined to Amhara and Oromos regions, it will engulf the entire country because this time every region and every ethnic is boiling with anger. Unleashing public unrest will lead to the demise of Ethiopia as we know it.…From what we have seen so far the new Ethiopian Prime Minister’s actions are counterproductive and creating more discontent in the country”

በእርግጥ የካቲት ላይ የተሳሳትነው እኛ እንጂ Tigrayoline ትክክል ነበር። ምክንያቱም በወቅቱ እኛ እስረኞች ስለተፈቱ ደስታና ፈንጠዚያ ላይ ሳለን የድረገፁ ፀኃፊዎች በኢሉአባቦራ ዞን፥ በኖ በደሌ አከባቢ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ምን እየተሰራ እንደሆነ ያውቃሉ። ከዚህ በተጨማሪ በቤኒሻንጉል፥ ጋምቤላና የተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ውስጥ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በግፍ ተፈናቅለዋል፥ ተገድለዋል። አብዛኞቻችን የካቲት 07/2010 ዓ.ም ስለተፈፀመው ግጭትና ማፈናቀል በትክክል ያወቅነው ከሦስት ወር በኋላ በባህር ዳር እና ወልዲያ አከባቢ አሉ ሲባል ነው። እነዚህን ተፈናቃዮችን በአካልና በስልክ በማነጋገር ያረጋገጥነው ነገር በኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰው ግድያና መፈናቀል ሆን ተብሎ በህወሓት የደህንነት ሰዎችና ተላላኪዎቻቸው አማካኝነት የተፈፀመ መሆኑን ነው።

ባለፈው የሰራነው ስህተት Tigrayoline ከማንም ቀድሞ ሁከትና ብጥብጥ እንደተከሰተና የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እንዲታወጅ ሲወተውት እንደ እብደት ወስደን ንቀን መተዋችን ነው። ምክንያቱም ይህ ድህረ ገፅ መረጃውን የሚያገኘው ከተጎጂዎች ሳይሆን ከገዳዮቹ አንደበት ነው። ስለዚህ በድህረ-ገፁ የወጣው መረጃ ከሞላ ጎደል የህወሓት ዕቅድና ዝርዝር መርሃ-ግብር ነው። በተመሳሳይ ከአስር ቀናት በፊት Tigrayoline ከአማራና ኦሮሚያ ውጪ ባሉት ክልሎች ሁከትና ብጥብጥ እንደሚነሳ በግልፅ ነግሮናል። ይኸው ሰሞኑን በዕቅዱ መሰረት ደቡብ ክልል በሁከትና ብጥብጥ እየታመሰ ይገኛል። ይህን መሰረት በማድረግ ተግባራዊ ሊደረግ የታቀደው መርሃ-ግብር ደግሞ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ነው። እንደተለመደው ሁከትና ብጥብጡ ሆነ የአዋጁ ባለቤት ደግሞ ህወሓት ነው። በአጠቃላይ የTigrayoline ዘገባ የሚያስረዳው ህወሓት ከአስር ቀን በፊት በደቡብ ክልል ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት አቅዶ የተግባር እንቅስቃሴ መጀመሩን ነው።

Filed in: Amharic