>
5:13 pm - Friday April 19, 4424

ህውሃትና አቢይ አህመድ የተሳሰሩባት የከረረችዋ ክር!!!  (ቬሮኒካ መላኩ)

ሀ~ ህውሃትና አቢይ አህመድ የተሳሰሩበት በጣም ስስ ክር የተበጠሰችው ጠቅላይ ሚኒስቴር አቢይ አህመድ ጎንደር በመሄድ ከወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ ከሆኑት ከእነአታላይ ዛፌ ጋር የተነጋገረ ቀን ነው።  አቢይ እንደ አንድ ከኢህአዴግ ውስጥ እንደወጣ መሪ የማይቻል የማይመስለውን እንደሚቻል አሳይቷል።
ለ~ ህውሃት እጅግ በጣም በቁጭት ከሚያንገበግባት ነገሮች ውስጥ ዋናው በጎንደር በኩል ያለውን የኢትዮጵያ መሬት በአሻንጉሊቷ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ዘመን ለሱዳን እንድሰጥ አለማድረጓ ነው።  አቢይ አህመድ ስልጣን ላይ  ከወጣ ጀምሮ በፊት በሳምንት 7ቱንም ቀናት በሱዳን ወታደር የሚደፈረው በጎንደር ያለው የኢትዮጵያ መሬት እፎይታ አግኝቷል። ሱዳንም እጇንም እግሯንም ሰብስባለች።
ሐ~ አቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጣ ወደ 70 ቀናት ተቆጠሩ ። በዚህ ወቅት ብዙ ሰላምና መረጋጋት ብዙም ረብሻና ብጥብጥ ተመልክተናል ነገር ግን በአጋዚ ጥይት የሞተ የንፁሃን ሬሳ አንድም እንኳን አልቆጠርንም። አንዳንድ ሰዎች በአጋዚ ጥይት የተመቱ ሙታንን ፌስቡክ ላይ ተለጥፎ ስላልተመለከቱ ዶ/ር አቢይ አህመድን ቃላት ቆጥበን ስናመሰግን በንደት አረፋ ይደፍቃሉ።
መ~ ማይክል ዋልዘር እንደሚለው ጥሩ የሰራ ሰው ሊገፈተር፣ ከራሱ ማኅበረሰብ ጋራ ሊጣላ፣ እንደ ነቢይ ባገሩ ላይከበር እና ሊንገላታ ይችላል። አቢይ አህመድም ይሄን መጠበቅ አለበት ።
ሠ~ አቢይ አህመድ ሥር ነቀል በኾነ መንገድ  አውሬ መሪዎችን ከሚወልደው ኢህአዴግ የተነጠለ (radical detachment)  ያደረገ መሪ ነው።
ረ~ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ   ቶታሊቴሪያን አምባገነን መሪዎች የሚጠቀሙትን  “ካሮት እና ልምጭ”  ሳይጠቀም በፍቅርና በይቅርታ እመራለሁ ብሎ ጉዞ ጀምሯል ።  ብዙ ጠላቶችም ተነስተውበታል በይፋም ከህውሃት የተቃውሞ መግለጫ ወጥቶበታል። በዚህ ክፉ  ወቅት  ከእኔ ምን ይጠበቃል ?
ተራ የፖለቲካ ቼዙን ተወት አድርጌ አቢይ አህመድ ጠላቶቹን እስኪያሸንፍ መደገፍ ብቻ ነው።

የአቢይ አህመድ መንግስት በመፈንቅለ መንግስት አዙሪት እየገባ ነው!!!

ቬሮኒካ መላኩ
1~ ያው እንግድህ አሜሪካም በገደምዳሜ እየመጣ ያለውን አደጋ ህዝቡ ይወቀው ብላ Tweet አድርጋለች።
2~የአቢይ አህመድ መንግስት በመፈንቅለ መንግስት አዙሪት እየገባ ነው እንበል።
3~ የደህንነቱ ሀላፊ ጌታቸው አሰፋም ቢሮዬን ለአዲሱ ተሿሚ አላስረክብም  ብሎ አንቆ ይዟል አሉ።
4~ ጠ/ሚ አቢይ አህመድም ቃል በቃል  የሚመራውን መንግስት ሽባ ለማድረግ እየወሰደ ባለው እርምጃ  በአኮረፉ ሀይሎች ኢኮኖሚያዊ  ሳቦታጅ (የኢኮኖሚ አሻጥር)  እየተደረገበት እንሆነ ገልፇል።
5~ መከላከያ  ሰራዊት በባድመ ሰበብ የሴራው  ቁልፍ ተሳታፊ እየሆነ መምጣት የአብይ  መንግስት ህልውና በጠመንጃ ያዡ ሰር እንዲወድቅ ሊያደርገው ይችላል። ድርጅታዊ ድስፕሊን የሌለውና ማፊያው ገዢው  ህውሃትም ለህልውናው ሲል ሰራዊቱን ” ጃስ” እያለ እየኮደኮደው ይገኛል።
………
እንደ መውጫ 
መጭው ጊዜ ደስ አይልም።  የኢትዮጵያ ህዝብ ደሞ ህውሃት እንደ በፊቱ ሙሉ በሙሉ ይቅርና  በግማሽ እንኳን ወደ መንበሩ  ከምትመጣ ሞቱን ይመርጣል ። ህውሃት ይሄን ካደረገች አናርኪ ተፈጥሮ የማታ ማታ የሚለበልበው  ራሷንና ራሷን ብቻ ነው።
Filed in: Amharic