>

በኦህዴድ ኮንፈረንስ የዜጎች መፈናቀልም ሌላኛው አጀንዳ ነው ተብሏል መፍትሄ ይገኝበት ይሆን? (ደረጄ ደስታ)

ኦህዴድ በመግለጫው፥ በ8ኛው የኦህዴድ ድርጅታዊ ኮንፍረንስ ከነገ ሰኔ 3 2010 ዓ.ም ጀምሮ በአዳማ ከተማ ይካሄዳል ብሏል። እነኚህ ፍሬ ነገሮቹ ናቸው-
1.በክልሉ እየተካሄደ የሚገኘው የጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴ ያለበት ደረጃ ይገመገማል።
2.መስተካከል ያለባቸው ጉድለቶችን በግልፅ በማንሳት ውይይት ይካሄድባቸዋል ።
3.ከድርጅቱ ውስጣዊ ችግር የሚመነጩና አንድነትን የሚከፋፍሉ አመለካከቶች እንዴት እየተፈጠሩ እንደሆነ እና መፍትሄዎቹ ላይ ውይይት ይደረጋል።
4. በክልሉ የህግ የበላይነትን ማስከበር በምን ደረጃ ላይ ይገኛል የሚለው እና አሁንም ድረስ በአንዳንድ አካባቢዎች እያጋጠሙ ያሉ የዜጎች መፈናቀልም ሌላኛው የኮንፍረንሱ አጀንዳ ይሆናል።
5. ከቀበሌ እስከ ክልል ደረጃ ያሉ የድርጅቱ የአመራሮች ብቃት የሚገኝበት ደረጃም ተገምግሞ ሊወሰዱ የሚገቡ ማስተካከያዎች ላይ መመሪያ ይሰጣል።
ኮንፈረንሱ የተፈናቃዮችን ጉዳይ ማንሳት ብቻ ሳይሆን ፍትህና መፍትሔ የሰጠ መሆኑን ማሳየት ይኖርበታል። በተፈረ ግን ሊቀመንበሩ ዶ/ር አብይ ዛሬና ነገን ግብጽን ጎብኘተው ነገውኑ ሮጠው ይመለሳሉ ተብሎ ይሆን? ኮንፈረንሱን ከድንኳን ሰባሪዎች ካልተጠነቀቁ ..”አንድ ቀን ቀልጣፎች ባሏን ይነጥቋታል/” እሚለውን ዘፈን አለመዘንጋት ነው። ለነገሩ ለካ ኦቦ ለማ መገርሳ አሉ። እንግዲያውስ ችግር አይኖርም። ቢሆንም ቢሆንም ግን ሥልጣን ብቻ ሳይሆን እዳና የታሪክ እከኩን ያወረሱት ተሰናባቾች ማንዣበባቸው አይቀር ይሆናል። እኝህ ለማ መገርሳ እሚባሉ ሰው ግን ባንድ ወቅት አቶ መለስ ዜናዊ ራሳቸውን “አታፍነን እንጂ እንናገርበት!” ብለው ስብሰባ ላይ በድፍረት መናገራቸው ይወራል። እውነት ይሆን? እስኪ እምታውቁ ስብሰባውንና ሁኔታውን ጠቅሳችሁ አካፍሉን።
Filed in: Amharic