>

ጥያቄያችሁ ምላሽ አግኝቷል ጫጫታችሁ ግን በርክቷል ለምን ይሆን!???! (ቬሮኒካ መላኩ)

በጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማሪያም ደሳለኝ የስልጣን ዘመን ሁሉ የትግራይ ፖለቲከኞች ዋና ጥያቄና እስከ ፓርላማ ድረስ ሲጠይቁት የነበረው ጥያቄ  ” ላለፉት አመታት ከኤርትራ ጋር ያለው    ” No War NO Peace ” ምክንያት  ትግራይ በኢኮኖሚ እየተጎዳች ስለሆነ መፍትሄ ስጡን?  ” የሚል ነበር። በዚህ አሰልች ጥያቄ ሀይለማሪያም ደሳለኝን የውቂያኖስ ሞገድ እንደሚንጣት አሮጌ ጀልባ ከወዲያ ወድህ ሲያላጉት ከረሙ።
የትግራይ ፖለቲከኞች ይዘውት የመጡት አማራጭ ሁለት ብቻ ነበር
1~ጦርነት ( War) ወይም
2~ “ሰላም ” ( Peace)
ይሄው “No war No Peace ” ያብቃልን  የሚል  ተመሳሳይ የትግራይ ፖለቲከኞች አሰልች ጥያቄ ጠ/ሚ አቢይ አህመድን ገና ከመምጣቱ ማሰልቼት ጀመረ። አብይ አህመድ ትግራይ ክልል ለጉብኝት በሄደም ጊዜ የጠየቁት ጥያቄ ” No war No peace ”  ያብቃልን የሚል  ነበር  ።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ይሄ ጥያቄ ከህውሃት ባለስልጣናት ጭምር ገፍቶ ሲመጣ መለስ ዜናዊ የፈረመውን የአልጄርስ ውልና ኔዘርላንድ ዘሄግ ያስቻለው የግልግል ፍርድ ቤት ውሳኔ ከመሳቢያ ውስጥ አውጥቶ  “የሚያዋጣችሁን ወስኑ !!” ብሎ አቀረበላቸው።
ለእኔ ” No War No Peace ሌላ ሰምና ወርቅ ሳይጨመርበት  ጦርነት ከመረጡ ትግራዮች ብቻ ከኤርትራ ጋር ለውጊያ መዘጋጀት ፣ ሰላም ከፈለጉ ደሞ ባድሜን ሰጥቶ መገላገል   የሚል ነው።
መለስ ዜናዊ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ህውሃት ያለበት  ኢህአድግ ባድመን ሰጥቼ  ሰላም እፈልጋለሁ ብሎ ወሰነ ።  ይሄ ሲወሰን የትግራይ ፖለቲከኞች የበለጠ አየሩን በጩህት አደበላለቁት።
አሃ ለካ እነሱ “No war No Peace ” ማለታቸው ጦርነት  በኤርትራ ላይ ታውጆ በአማራና በኦሮሞ ወታደር ደም ኢሳያስን አስወግዶ  ጉዳዩን መጨረስ ማለታቸው ነበር።
እረ ጄለሴ ምን ነካችሁ?  የሞኝነት አመታት እኮ ላይመለሱ ጥለውን ነጎዱ እኮ  ። በቅንጭላትና በእውቀት እንኳን ሳትበልጡን እንደት  ነው ይችን ጌም ያሰባችኋት  ?
አሁንም ያለህ አማራጭ ሁለት ብቻ ነው ሰላም ከፈለክ ባድመን  መስጠት (እሱም ራሱ ሰላም አያስገኝም)  ጦርነት ከፈለክ ደሞ ከተከዜ ማዶ ወታደርህን መልምለህ መዋጋት ። አበቃ ሌላ ፌሎዞፊ አያስፈልገውም እኮ ።
Filed in: Amharic