>

የመለስ ራዕይ ፈፃሚ አግኝቷል!!! (ብርሀኑ ተክለ ያሬድ)

ያለ ህዝብ ምክክር ያለ ህግ ባለሙያዎች ሙያዊ ድጋፍ ያለማንም ተጠያቂነት በደላላና ሀገር ሻጭ ስራ አስፈፃሚዎች ውሳኔ ብቻ ባድመ ሄደች
ባድመ ለኢትዮጵያውያን ከቁራጭ መሬትነት አልፋለች የወጣቶቻችን ደም የእኩዮቻችን አፅመ ርስት የመስዋዕትነት ሀውልት ናት “ለሰላም ሲባል”ቢሆን እንኳን ልጆቹን ለሀገር ሉአላዊነት የገበረው ህዝብ መወያየት አልነበረበትም?
ለባድመ ሲባል እድሜያቸው ያልደረሰ ህፃናት ሌላ ሰው ኪሎ እየተለካላቸው ወደ ጦርነቱ ገስግሰዋል ተከብረሽ የኖርሽው…… እየተዘመረ ወጣት የጥይት ማብረጃ ሆኗል ጉዳዩ የእነዚህ ልጆች መስዋዕትነት ጉዳይ ነው
ጭብጨባ ለዘላለም ይኑርና የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አጨብጫቢዎች የተሳሳተው መለስ እንደሆነና አሁን ምንም አማራጭ እንደሌለ ሊነግሩን ይፈልጋሉ መለስማ የስህተት አባት ነበር ብዙ አውቆ የተሳሳታቸውን የስህተት ውሳኔዎች አሸክሞን ሔዷል ታዲያ የለውጥ ሀይል ነው የሚባልለት የአብይ ቲም  የክፉው መለስ ስህተቶችን እያፀደቀ ነው ለውጡን የሚያሳልጠው??
መለስ ባድመን ፈርሟል አሰብን ሸጧል ለሱዳን መሬት ቆርሶ ሰጥቷል የቅኝ ግዛት ውሎችን ፈርሟል እድሜ ለጭብጨባና አጨብጫቢዎች ይሁንና የመለስ ራዕይ አስፈፃሚ አግኝቷል የምርኮኛ ወታደሮቻችን ጉዳይ እንኳን ተረስቶ የ70.000 ወጣቶች አስከሬን ለድርጅት ህልውና ሲባል ይቸበቸባል የነበዛብህ ጴጥሮስ ወገኖች እርማችንን እናውጣ ብራቮ አብይ!!!!
Filed in: Amharic