>

ባድመን ለኤርትራ ማን ሰጠ ?  (ቬሮኒካ መላኩ)

በአቢይ አህመድ ዘመን ባድመ ተሸጠች የሚሉ የዋሆችን እየተመለከትኩኝ ነው። በለው  !!!
ባድመን ለኤርትራ ማን ሰጠ ? 
ሄደህ ስላሴ ጓሮ ውስጥ  በወታደር እየተጠበቀ የተጋደመውን ሰው ጠይቀው ።
በአልጀሪያው ፕሬዚደንት  ቡቴፊሊካ እና በአሜሪካው ተወካይ  ፊት በ10 ጣቱ ግጥም አድርጎ የፈረመው እሱ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ባድመ የኤርትራ ነው ብሎ ይግባኝ የሌለው የመጨረሻ ፍርድ የፈረደውን ሄግ የሚገኘውን አለምአቀፍ ፍርድ ቤት በር አንኳኩተህ  ጠይቅ ። አቢይን በብዙ ነገር መውቀስ ይቻላል አብይን  በባድመ  መውቀስ ግን አይነፋም።
አሁን አብይ አህመድን የህዝብ ድጋፍ ለማሣጣትና  የከንስፓይሬሲ ቪክቲም  ለማድረግ ከህውሃት ጋር ሴራ የምትጠነስሱ ሰዎች የደብረፂዮን አይነት ወይም የሽፈራው ሽጉጤ አይነት መሪ የናፈቃችሁ ትመስላላችሁ። አሁን አቢይ ከነችግሩ ለኢትዮጵያ የሚያስፈልግ መሪ ነው ብዬ አምናለሁኝ።
ህውሃቶች ባድመን ለመስጠት መቀሌ በር ዘግተው ከወሰኑ በኋላ   ” በአቢይ አህመድ  ዘመን ባድሜ ተሽጠች ” በማለት ሰውዬውን ቁርስ ለማድረግ ሲሯሯጡ እናንተ ደሞ እንደ ስካቬንጀር ትርፍራፊ ለመልቀም ባትሮጡ ጥሩ ነው።
በተረፈ እኔን የሚያሳስበኝ በጃንሆይ ዘመን የተቋቋመውና የአፍሪካ ኩራት የሆነው የወርቅ እንቁላል የሚጥለው በራሪ አየርመንገድ በአክሲዮን ስም ወደ እነ ኢፈርት እንዳይገባ  እና የወተት ላም የሆነችውን ቴሌን  ባለፉት  27 አመታት  ኢትዮጵያን ያለቧት ሰዎች በአክሲዮን ስም እንዳይሰገሰጉ ጫና መፍጠሩ ላይ ነው እንጅ ከ20 አመታት በፊት  በተበላ እቁብ  አቢይን መነዝነዙ አያዋጣም።
Filed in: Amharic