>
5:13 pm - Friday April 19, 5157

ሌላ ፈተና- የነገውን ስብሰባ ማን ጠራው? ብአዴኖች በረከትን አባረሩ ወይስ….? (ደረጄ ደስታ)

ሌላ ፈተና- የነገውን ስብሰባ ማን ጠራው?

ብአዴኖች በረከትን አባረሩ ወይስ….?

ደረጄ ደስታ
ይህ ሌላኛው የአብይ ፈተና መሆኑ ነው። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት ስብሰባውን እንደሚያካሄድ ተነግሯል። የስብሰባው ዓይነት መደበኛ ይሁን አስቸኳይ አልተገለጸም። የነበረው ደንብ ወይም ልማድ በየሶስት ወሩ እንደሆነ ነው እሚታወቀው። አብይ ከተመረጡበት ወዲህ ያለው ቀን ገና ስድሳ ቀኑ ነው። ቢያንስ ከአንድ ወር በፊት ቀድሞ የተጠራ ስብሰባ ይመስላል። እንደተሰማው ስብሰባው አብይ የፈለጉት ስብሰባ ሳይሆን በጥያቄና በብዙ ጭቅጭቅ የተጠራ ስብሰባ ነው። የኢህአዴግ ጽ/ቤት የስብሰባው አጀንዳ “ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የ2 ዓመት ተኩል አፈፃፀም ይገመግማል።” የሚል ቢሆንም እውነታው ግን “ኢህአዴግ መስመሩን ስቷል የሚሉት የህወሓት/ኢህአዴግ ሥራ አፈጻሚ አባላት ቀስቅሰው የጠሩት ነው።” እየተባለ ነው። ለህዝብ ይፋ ከተደረገው አጀንዳ ውጭ የራሳቸውን አጀንዳ ሸርበው “ያልተጠበቁ” ጥያቄዎችን ለማንሳት የተሰናዱ መኖራቸው ተሰምቷል። በፖለቲካ እስረኞች አፈታት ያልተደሰቱ ከሥልጣንና ከጥቅም የተገለሉ አኩራፊዎች የፈለጉት ስብሰባ መሆኑም እየተነገረ ነው። አስገራሚው ነገር ግን እሱ ብቻ ሳይሆን የሥራ አስፈጻሚ አባል ያልሆኑ ድምጽ የማይሰጡ ሰዎች በስብሰባው ላይ ይገኙ ወይስ አይገኙ እሚለው ጥያቄ መነሳቱ ነው። የዶ/ር አብይ አቋም መገኘት አይኖባቸውም የሚል መሆኑን ቢሰማም ድንኳን ሰባሪዎቹ የነገር አዛውንቶች ለመግባት ግብግብ መያዛቸው እየተሰማ ነው። ስብሐት ነጋ አባይ ፀሐዬ ስዩም መስፍን የመሳሰሉት እንደሆኑም ተነግሯል። አቶ በረከት ከዚህ መጨመር አለመጨመራቸው ገና አልተለየም። ምክንያቱም ከጥቂት ሳምንታት በፊት ባህር ዳር ላይ በተደረገው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከተሰብሳቢዎቹ ከባድ ውግዘት ገጥሟቸዋል። “የህወሓት ተላላኪ ነህ የአማራን መብት እምታስጠብቅ አይደለህም” የመሳሰሉት ውርጅብኞችን ከብአዴን አባላት የዘነበባቸው አቶ በረከት ከስብሰባው ለምሳ እንደወጡ ሳይመለሱ በዚያው መቅረታቸው ተወርቷል። ከባህርዳር ቢባረሩም የተመለሱት ወደ አዲስ አበባ ነው። አዲስ አበባ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ታጥባ ገና ከእድፏ አልነጻችም።
Filed in: Amharic