>

ስለ ዜግነት እናንሳማ ካላችሁ.....!????! (ሚኪ አምሀራ)

በነገራችን ላይ አይደለም ኢትዮጵያ ዉስጥ መኖር ሳይሆን የኢትዮጵያ ዜጋ ሳይሆኑ ስንቱ የመንግስት ስራ ይሰራሉ፡፡ አብዛኛዉ ህወሃቶች በተለይም በኤጀንሲዎች አካባቢ የተሰገሰጉት የአሜሪካ እና አዉሮፓ ዜግነት አይደል እንዴ ያላቸዉ፡፡ እነ ኢለኒ ገብረእግዛብሄር፤ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ሃላፊ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገዱ ሰዉየ እና ሌሎችም የአሜሪካ ዜግነት ነዉ ያላቸዉ፡፡
የደብረጺወን ሚስት እስከ ልጁ አሜሪካዊ ናቸዉ፤ ደብረጺወን እራሱ ጣሊያናዊ ነዉ ይባላል፤ ዶ/ር ቴወድሮስ አድሃኖም ተወልዶ ያደገዉ ኤርትራ ነዉ ስለዚህ ኤርትራዊ ነዉ፡፡ አዜብ መስፍን አሜሪካዊ ናት፡፡ እሷ እንዲያዉም በእናቷ በኩል ነዉ ዜግነቷነን የያገኘችዉ፡፡የአዜብ እናት ቆንጅት ጎላ እድሜ ልካቸዉን አሜሪካ/ኦሃዮ-ኮሎምበስ ነዉ ኑረዉ አሁን ሲጃጁ አዲስ አበባ የተመለሱት፡፡ ልጆቿን በሙሉ አሜሪካዊ አድርገዉ ነዉ የተመለሱት፡፡ኧረ እህቶቻቸዉን እነ ማናህሎሽ ጎላ ሁሉ ሳይቀሩ ኢትዮጵያዊ አይመስሉኝም፡፡ ምናልባት አንዷ ጎንደር የሚኖሩት እንጉዳይ ጎላ ብቻ ኢትዮጵያዊ ይመስሉኛል፡፡ እና አሁን ሜቴክ በአሜሪካዊ ነዉ እኮ የሚመራዉ፡፡ ስንቱን ካደችዉ እሷስ፡፡ መጀመሪያ የወልቃይት አማራነቷን፤ ኢትዮጵያዊነቷን..፡፡ በነገራችን ላይ አንድም ህወሃት ንጹህ ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ ወይ እራሱ ወይ ባሏ ወይ ሚስቱ ወይ ልጆቹ ኢትዮጵያዊ አይደሉም፡፡ አቦይ ስብሃት ኤርትራዊ ነዉ፡፡ እነ መለስ ዜናዊ በትግሉ ወቅት ሶማሊያዊ ነበሩ፡፡ ጌታቸዉ አሰፋ እስከ ልጆቹ ሚስቶቹ አሜሪካዊ ነዉ፡፡ፓትሪያሪኩ እራሱ አሜሪካዊ ናቸዉ፡፡
ህወሃት ዉስጥ ሙሉ ለሙሉ ኢትጵያዊ ዜግነት ያለዉ የክለተ አዉላሎ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ ብቻ ይመስለኛል፡፡
ብአዴኖች እንኳን የሌላ አገር ዜግነት ሊያገኙ ህወሃት የኢትዮጵያ ፓስፖርት እራሱ አይሰጣቸዉም የሰጣቸዉንም አንዳንዶቹን መጥፎ ተናገራችሁ ብሎ ቀምቷቸዋል፡፡  ለምሳሌ ጀኔራል አበባዉ ታደሰ፤ ሻምበል እና የመሳሰሉት ፓስፖርታቸዉን ተቀምተዋል፡፡ ከነ በረከት ዉጭ ያለዉ ብአዴን ለነገሩ የዉጪ ሃገር ዜጋ እንኳን ሊሆኑ ዉጪ ሃገር ሄደዉም አያዉቁ፡፡ ገንዘብ እንኳን ሲሰርቁ እኮ በዉጭ ባንክ ሳይሆን እዚሁ አገር ቤት ከአማራ ክልል ዉጪ ሄዴዉ አካዉንት ከፍተዉ ነዉ የሚያስቀምጡት፡፡ ለምሳሌ እነ ዝማም (የብአዴን ከፍተኛ አመራር) ጅማ ሄደዉ በስማቸዉ በንግድ ባንክ ቅርንጫፉ ገንዘብ አስቀምጠዉ ይመጣሉ፡፡ ገነት ገብረእግዛብሄር ደግሞ መቀሌ ነዉ የባንክ አካዉንት ያላት፡፡ ጅማ ወይም መቀሌ ያለዉ የንግድ ባንክ አካዉንታቸዉ ባህርዳር ተሁኖ የሚታወቅ አይመስላቸዉም፡፡ ምስኪን ብአዴን፡፡ ገንዘቡን ሲፈልጉት እራሱ በቡሬ በኩል የመንግስት መኪና ነድተዉ ጅማ ሄደዉ ነዉ የሚያወጡት፡፡ ጅማ ያለዉን የንግድ ባንክ አካዉንት ባህርዳር ላይ ሁኖ መጠቀም የሚቻል አይመስላቸዉም፡፡ አይ እነዝማም፡፡ እንዲያዉ ገዱ ምኑን ጉድ ነዉ ይዞት የኖረዉ፡፡ ኦህዴድ እንኳን አንዳንዶቹ አልፎ አልፎ ዱባይ እና ታይዋንን ያዉቁታል፡፡ ደሚቱ እና አባዱላ ለምሳሌ የሆነ ጊዜ ላይ ወደ ዱባይ ሲበሩ አይቻለዉ፡፡ በተረፈ በአንዱ የገጠር ዘመዳቸዉ ስም አዲስ አበባ ላይ ፎቅ ይሰሩበታል፡፡ወይ ገንዘቡን በኬሻ ቋጥረዉ አመድ ቀብተዉ እቤታቸዉ ነዉ የሚያስቀምጡት፡፡ኦህዴዶች ደግሞ ዶላር ሳይሆን የኢትዮጵያ ብር ነዉ ገንዘብ የሚመስላቸዉ፡፡ እና ዶላር ሲያገኙ ከህወሃቶች ወደ ብር ይቀይሩታል፡፡ አይ እነ ደሚቱ እና አባዱላ!
መልካም ቀን ይሁንላችሁ እቴ
Filed in: Amharic