>

"ዲሞክራሲ በወሬ ብቻ አይመጣም - የሚሰባበረውን መሰባበር የሚነቀለውን መነቃቀል ያስፈልጋል!!!" (ኦቦ ለማ መገርሳ) 

ኦቦ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት የግንቦት 20 ክብረበዓልን አስመልክቶ ካደረጉት ንግግር በወፍ በረር  ተመርጦ የተተረጎመ ሀሳብ
(ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ)
1/ዲሞክራሲ በወሬ ብቻ አይመጣም፡፡ የሚሰባበረውን መሰባበር የሚነቀለውን መንቀል ያስፈልጋል፡፡
2/ባህላችንም ዲሞክራሲን እንዲሰፋ የሚያግዝ ሳይሆን በተቃራኒው እንዲቀጭጭ የሚያደረግ ስለሆነ እሱ ላይም መስራት አለብን፡፡
3/እስረኛውን እንደወራጅ ወንዝ እየለቀቅን ያለነው እስርቤት ለመዝጋት እቅድ ስላለን ሳይሆን አዲስ የፓለቲካ አየር ለመፍጠር ስለምንፈልግ ነው፡፡
4/..በኦሮሚያ በአንድ አመት ውስጥ 40ሺ እስረኛ  በላይ የለቀቅነው ግለሰብን ብቻ ነፃ ለማውጣት ስለምንፈልግ እንዲሁም ለመወደድ ወይም እንዲጨበጨብልን ስለፈለግን ሳይሆን  የመጠላለፍ እና የመጠፋፋት ባህላችንን ለመቀየር ነው  ፡፡
5/ሰዎችን ከእስርቤት  አይደለም  ነጻ ያወጣነው..ተሰደው የዜግነት መብታቸውንም ካጡት የስደት ኑሮ ነው..ከባዕድ ሀገር እስር ቤት ጭምርም ነው ፡፡
6/ታሪክ እየቀየርን ነው.. ሁሉንም የፓለቲካ ፓርቲ ከያሉበት ግቡና አብረን እንስራ የምንለው የፓለቲካ ገበያ  ለመክፈት ሳይሆን በእውነት እና በሀቅ የሀገሪቱን ታሪክ ለመቀየር ስለምንፈልግ ነው፡፡በስደት በባረና በኩል ተሰደደው ኃይል ቦሌ በኩል እንዲገባ ያደረግነው ሞተው እሬሳቸው ተጭኖ ከሚመጣልን ይልቅ በህይወት መጥተው ለህዝባቸው እንዲሰሩ እና  እንዲያገለግሉ ነው፡፡ የሀገሪቱ ዜጋ መሆናቸው እንዲረጋገጥላቸውት ነው፡፡እነዚህ አካላት ሀገር ውስጥ ሆነው በህዝባቸው መሀከል ሆነው ሲሰሩ ነው ሚያወሩትን ለውጥ በተግባር ሊያመጡ ሚችሉት፡፡
7..ኦፒዲዬ ስለሆን ለዘመናት ይጠየፍን እና ይንቁን የነበሩትን እና ከእናንተ በላይ ነን የሚሉትንም  ነፃ አውጥተን ለሀገራቸው አብቅተናቸዋል፡፡
8/..እኔ ምኞቴን ነግራችሁለው..እዚህ  ወንበር ላይ ለመቆየት አይደለም ዕቅዴ ለዚህ ህዝብ ነፃነት ማምጣት ከቻልን ድላችን ወደሃላ የማይመለስበት ደራጃ መድረሱን ካረጋገጥን ለመልቀቅ   ደስተኞች ነን፡፡
9/ከአሁን ወዲህ ተገቢውን የህዝብ ድምጽ ሳያገኙ እዚህ ወንበር ላይ መቀመጥ አይቻልም፡፡
10/3 ሰዓት አንብቤ 30 ደቂቃ ድንቅ ንግግር  ማድረግ ቀላል ነው……፡፡ መስራት ነው የሚከብደው.. ጥሮ ግሮ ትንሽም ሆን ትልቅ ውጤት ማምጣት ነው ከባዱ..ማውራትም ሺ ዋች አሳምረው ያወራሉ….
11/እኛ የተሰደደውን ብቻ ነፃ ማውጣት ሳይሆን ሀገሩቱንም ከመበተን አድነናታል..እኛ ወደ ስልጣን ስንመጣ ብዙዎቹ አሳንሰው እንዳዩን ሳይሆን  ከኦሮሞ ህዝብ የወጣን ቢሆንም ለመላው ኢትዬጵያ የምንተርፍ መሆናችንን አረጋግጠናል፡፡በዳቦ ከሆነ ወደስልጣ በመምጣታችን አንድ ዳቦ እንኳን ለኦሮሞ የጨመርነው የለም፣ሀገራችን እንድትከበር ግን ማድረግ ችለናል፡፡ ክብር ደግሞ  ከዳቦ ይበጣል፡፡በቀጣይ ዳቦውን በላባችን ሰርተን እናገኘዋለን፡፡
12/አሁን ተንሰንሰፍስፈው የሚያናግሩን እና በአጀብ አቀባበል ሚያደርጉልን  የአለም ሀገራት  ከወራት በፊት በአማላጅ አንኳን ለማናገርም ተጠይፈውን  እና እንቢ ብለውን ነበር…በአንድነታችን  ኦሮሞን ብቻ ሳይሆን ኢትዬጵያንም ነው ያስከበርነው በቀጣይም አፍሪካንም ጭምር ለማስከበር ነው የምንሰራው
አሁንም ህዝባችን ብዙ መካራ አለበት፡፡ ዋናው ሰንሰለት ግን ከላያችን ላይ መበጣጠስ ችለናል፡፡
13/ዛሬም በሀሳብ ልዩነትን ተቻችለን አብረን  ለህዝባችን መስራት የማንችል እና ልክ እንደትናንቱ በመሳሪያ የምንጫረስ ከሆን ምንም ያልተማርን መሀይሞች ነን ማለት ነው፡፡
14/ወንበርን ሀብትን ለማፍሪያነት  ፈልገነው የተቀመጥንበት ሲሆን ብቻ ነው ለመልቀቅ የምናንገራግረው..ለመቆየትም ስንል ሌላውን የምናጠፋው…ፍላጎታችን  የህዝባችንን ኑሮ ለመቀየር ከሆነ ግን ወንበር ላይ ውሎ ለማደር የምንጫረስበት ምክንያት አይኖርም፡፡
15/በየፌስ ብኩ እከሌን ያስፈታነው እኛ ነን ብለው የሚፎክሩ አሉ.. ይፎክሩ ለህዝብ እስከጠቀመ ድረስ ይሁን ክሬዲቱን   ለመውሰድ ሚሰጠው ሰርተፍኬቱ አያልቅም.. ግን የዛሬ ሶስት አመት ለምን አላሰፈቱም …?የዛሬ አራት አመትስ..?
ዛሬም ሁኑ ነገር አልተፈታም ..ብዙ ችግሮቻችን ገና በሂደት ላይ ናቸው፡፡ ግን በመደማመጥ መስራት አለብን…ነገም ተነስተን  በገጀራ ምንጨፋጨፍ ከሆነ እና በዱላ ምንደባደብ ከሆነ  ብዙም ሳይቆይ በቅርብ ህዝባችንን መልሰን ወደባርነት እንመልሰወለን ማለት ነው፡፡ በንግግር የምንስማማበት የመቻቻልና የአንድነት ዘመን ይሁንን፡፡
አሜን ብያለው
Filed in: Amharic