>

በትግራይ  የአቶ መለስ ዜናዊ ቤተክርስቲያን ይታነጻል!?! በአዲስ አበባ  የእመቤታችን ቤተክርስቲያን በፖሊስ ይፈርሳል?!? (ዘመድኩን በቀለ)

 በምሪ ትግራይ ሰውየው አይተ መለስ ዜናዊ ከቅዱሳን እንደአንዱ ተቆጥረዋል። ወዳጄ በትግራይ ምድር ድፍረት እዚህ ጥግ ደርሷል።
~ በቀደመ ጊዜ ቤተክርስቲያን ያሳነጹ ኢትዮጵያውያን ነገሥታት በቤተክርስቲያን ውስጥ የመታሰቢያ ሥዕል ይሳልላቸው ነበር ። ልማድም ነው ። ታዲያ ጋሼ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምን ስላደረጉ ነው እንዲህ በምሥላቸው የተንቆጠቆጠ ቤተክርስቲያን የታነጸላቸው ? ይኼኔ እኮ በሩቅ ቆሞ በቅርብም ሔዶ የሚሳለምም ፣ የሚሰግድላቸውም አይጠፋም።
~ የፈለገው ጥግ ድረስ ቢወዷቸው በቅድስት ቤተክርስቲያን ማላገጥና ማሾፍ አግባብ አይደለም። ነውርም ፣ ኃጢአትም፣ ወንጀልም ነው። ራሳቸው አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት ቢኖሩ እንዲህ ያደረጉትን አመራሮች ሰብስበው ቂሊንጦ ነበር የሚያወርዷቸው። እንዴት ለአልባንያ ኮሚንስቱ አፍቃሪ ቤተመቅደስ ይታነፃል ???
~ ቤተክርስቲያን በዚህ መልኩ ስትደፈር ቅዱስ ፓትሪያርኩም ፣ ሀገረ ስብከቱም ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱም ዝም ብሎ ያያሉ። የጉድ ዘመንና ለጉድ የጎለተን ፍጥረቶች ተገጣጥመን አረፍነው።
በሌላ ዜና ደግሞ ፦
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ስሙ ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የምትገኘውን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ መስተዳድር በግሬደር ፍርስርሷን አውጥቶታል ። ንዋያተ ቅዱሳቱም ሜዳ ላይ ተበትኗል ።
~ አዲዮስ ኦርቶዶክስ አዲዮስ ተዋሕዶ ! 
~ ቅዱስነታቸው ሩሲያ ነው የሚገኙት ። ጠቅላዩ ደግሞ ሳዑዲ አረቢያ። ከግብጽ ጋር ያለው ነገር አላምር ያለው መንግሥታችን ሩሲያን በፓትሪያርኩ በኩል ደጅ እየጠና ነው የሚሉም አሉ።
~ በምሥራቅ አፍሪካማ የሆነ ነገር ይሸታል ። ጠሚዶ ያለ ነገር ሱዳን ፣ ጅቡቲ ፣ ኬንያ ፣ አሁን ደግሞ ሳዑዲ አረቢያ አይንከራተቱም። ደግሞ እኮ በሔዱበት ሁሉ ሀገራቱ እስከዛሬ ያሰሩአቸውን ኢትዮጵያውያን በመፍታት ነው ገጸ በረከት የሚያቀርቡላቸው።
~ በሉ ክፉ አታናግሩኝ ። ደኽና እደሩ ።
~ ነገር ግን የአቶ መለስ ዜናዊን ወርሃዊ ክብረ በዓሉን የምታውቁ ግን አደራ ንገሩኝ። ጧፍ ምናምን ለመላክ ሳይሆ ለጠቅላላ እውቀት ነው ። ስንክሳሩም ውስጥ ገብቶ እንደሁ እባካችሁ አጣሩልኝ አደራ !  አደራ !።
ሻሎም !  ሰላም !
Filed in: Amharic