>

ከፖለቲካው አልያም ከኢኮኖሚው ተጠቃሚ ለመሆን ብሔር እስከ መቀየር የተደረሰባት አገር!?! (ሚኪ አምሀራ)

1. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ በቁጥር ቀዳሚ የሆኑ ሶስቱ ብሔሮች በርታ፣ አማራና ጉሙዝ ናቸው፡፡ ራስን በራስ የማስተዳደር ስልጣን ያላቸው በርታ፣ ጉሙዝ፣ሽናሻ፣ ማኦና ኮሞ ናቸው፡፡
2. በጋምቤላ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሶስቱ ብሔሮች ኑዌር፣ አማራና አኙዋሃ ናቸው፡፡ ራስን በራስ የማስተዳደር ስልጣን ያላቸው ኑዌር፣ አኙዋሃ፣ መዣንግ ናቸው
3. በሐረሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ኦሮሞ፣ አማራና ሐረሪ ናቸው፡፡ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ያላቸው ሐረሪና ኦሮሞ ናቸው፡፡
4. በድሬዳዋ በርካታ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ኦሮሞ፣ አማራና ሶማሊ ናቸው፡፡ 80 ፐርሰንት ስልጣኑ ለኦሮሞና ሶማሊ ሲሰጥ ቀሪ 20 ፐርሰንት አማራ ከደቡብና ህወሓትና ሀረሪ ጋር የሚቃመሳት ናት፡፡
5. በኦሮሚያ በርካታ ቁጥር ያላቸው ነዋሪዎች ኦሮሞ፣(ከ80 ፐርሰንት በላይ)አማራና ጉራጌ ናቸው፡፡ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቱ የተከበረው ለኦሮሞ ብቻ ነው፡፡
6. በአዲስአበባ ግማሽ ገደማ ነዋሪው አማራ ነው፡፡ የፖለቲካና ስልጣን ውክልናው ግን ሩብ ነው፡፡
7. በደቡብ ያለው አማራም በክልሉ ካሉ አብዛኞቹ ብሔሮች የበለጠ ቁጥር ያለው ነው፡፡ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት ግን የለውም፡፡
(በአማራ ቀዳሚ ቁጥር ያላቸው ብሔሮች አማራ፣ አገውና ኦሮሞ ናቸው ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ያላቸው፣ አማራ፣ አገው፣ ኦሮሞ፣ ቅማንት፣ አርጎባ ናቸው)፡፡
ብዙ ቦታዎች ፖለቲካዊ ተሳትፎ ወይም እንደአቅሚቲ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ አማሮች ብሔራቸውን ቀይረው መንቀሳቀስ፣ አንዳንዴም በሀይማኖትም በብሔርም ከማይመስሏቸው ጋር የልጆቻቸውን ሀይማኖትና ብሔር እያስቀየሩ በማጋባት መዛመድን እንደመፍትሔ የሚያዩ ሆነዋል፡፡
በሁሉም ቦታዎች የአማራን መብት እና እኩልነት አለማክበር፣ በኢኮኖሚም በፖለቲካም ማግለል፣ በመጥፎ መፈረጅ፣. . . . ወዘተ ቅቡል ታሪክ ሆኖ ቆይቷል፡፡
አማራ ከብዙ ክልሎች በተደጋጋሚ በገፍ ሲፈናቀል ማንም አይሞቀውም አይበርደውም፡፡ አማራው ራሱ ለምዶት ብዙ አይቆጣም፡፡
አምና ትግሬ ሲፈናቀል ግን የፌደራልና የክልል ፖለቲከኞቻችን ሁሉ እንደእንዝርት ነበር የሾሩት፡፡
ኦሮሞ ሲፈናቀል ድፍን ኦሮሚያ በአንድ እግሯ ቆማለች፡፡ መንግስትም ደንግጧል፡፡ የክልል ብሎም የፌደራል ስልጣን እስከመቀየርም ተደርሷል፡፡
የሌሎች መከበር፣ የሌሎች አልደፈር ባይነት ለአማራ ችግር አይደለም፡፡ ግን አማራም እኩል ይሁን፤ እኩል ይታይ፤ የአማራ መብቶችም እኩል ይከበሩ፤ በአራቱም አቅጣጫዎች አማራን ከሌላው በታች የማድረግ የመለስ ሌጋሲ ይብቃው፡፡ አማራነት ይከበር!!!
ብአዴን ይሄንን ማስከበር ካልቻለ የአማራ ፓርቲ ነኝ እንዳይል፡፡ ጠሚ አብይ ይሄንን ሳያረጋግጡ ስለእኩልነትና አንድነት እንዳይዘምሩ፡፡
Addis Chekol
cc//
ANDM CC office ANRS Communication Affairs OfficeBahirdar city Communication
Filed in: Amharic