>
5:13 pm - Sunday April 18, 5554

ስለ አንዳርጋቸው ጽጌ- ስለሆነ ፦ ተፈትቶ ማየት እንሻለን !! (ዳንኤል ሺበሺ)

♥ ከምንም፤ ከምንም እና ከምንም በላይ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ መሰጠት በሰው’ነት ከፍታ የሚያኖረን ስለሆነ፤
♥ በዚህች ሀገር እውነተኛ መግባባትና እርቅ ካስፈለገን የእሱ አካላዊ ነፃነት ወሳኝ ስለሆነ ፡፡
♥ የኢትዮጵያዊያንን ስም በሽብር/በአሸባሪነት ማንሳት የሚያሳፍረንና ራሳችንን ማራከስ ስለሆነ ፡፡
♥ እሱ ስለታሰረ የረገበ/የተሻሻለ የፀጥታ ሁኔታ፤ የምጣኔ-ሀብት ዕድገት እና የተቀየረ የትግል ስልት ወዘተ ያልያልታየ ስለሆነ፤
♥ በሀገራችንና በሕዝባችን ታሪክ፤ ሕዝብ/ዜጋ በመንግሥት ሲሸበር የመጣ በመሆኑ፤ አሁን ይህን መጥፎ ገፅታ ተቀይሮ ማሳየት ፋይዳው ብዙ ስለሆነ፤
♥ አንዳርጋቸው፦ ለሀገሩ፣ ለዜጎች፣ ድፍን ለሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ ፍትህ የሚመኝ ቅን ሰው ስለሆነ ፤
♥ አንዳርጋቸው! ባለ ምጡቅ አእምሮ ባለቤት ስለሆነ ፡፡
♥ አንዳርጋቸው! እንደ ማንም ተራ ዜጋ ሳይሆን ለሀገር፣ ለወገኑ፣ ለቤተሰቡ እጅግ አስፈላጊ ሰው ስለሆነ፤
♥ ከእሱ ጀርባ ለተሰለፈው ለሚሊዮኖቹ ድምፅ ሲባል ወይም እሱን መፍታት ሚሊዮኖችን ማክበር ስለሆነ፤
♥ አንደርጋቸው በመታሰሩ ምክንያት ጀግንነቱን፣ ሕዝባዊ ድጋፉን መሸርሸር፤ ከሕዝብ ልብ መፋቅ ሲላልተቻለ፤
♥ የአንደርጋቸው አካሉን እንጂ ዓላማውን ማሰር ፈጽሞ ሲላልተቻለ፤
♥ አንዳርጋቸው ጽጌ ይፈታ አልልም!! አልታሰረምና፡፡ አንዳርጋቸው ይፈታ ሲል አካላዊ ነፃነቱ ያግኝ ነው እንጂ፡፡ ሀሳቡ፣ ሞራሉ፣ ወኔውና ክብሩ ያልታሰረለትን ሰው ታስሯል ብዬ ስለማላምን፡፡ አንዳርጋቸው የቆመበት የትግል ዘዴው አሁን በሥራ ላይ ያለውን የአገዛዙን ሕግን ይፃረራል ከተባለም መነጋገር የሚቻለው እሱ ታስሮ ሳይሆን እሱ ከተፈታ በኀላ መሆኑ አማራጭ የሌለው ጥያቄ ስለሆነ፡፡
                         ስለዚህ <ተፈትቶ ማየት እንሻለን !!>
Filed in: Amharic